MINILIK SALSAWI

Ethiopia My Mother

ጠቅላይ ሚንስትሩ የትራንስፎርሜሽ እቅዱ እንዳልተሳካ እቅጩን ነግረውናል!!!

ጠቅላይ ሚንስትሩ በድፍረትየእድገት እና ትራንስፎርሜሽን እቅዱ ያህል አልተሳካም:;መንግስት ያሰባቸው እና ያቀዳቸው ከግማሽ በታች እንኳን አልተሳኩም አሉ: ለጀሌዎቻቸው...


 ጠቅላይ ሚኒስትሩ በባህር ዳር ካሉት በመነሳት ነገሮች ሲወቀጡ በ1ለ5 እየሰበሰቡ የልማታዊ የፖለቲካ ሠራዊት ማደራጀት የተፈጥሮ ሃብት ልማት እያሉ ገበሬዎችን በዘመቻ ለፖለቲካ ፍጆታመጥመድ ልማት የሚባለው አልተሳካም። ትልልቅ ፕሮጀክቶች ተጓተዋል የገበሬዎች የእርሻ ምርት፣ የእቅዱን ግማሽ ያህል እንኳ አልተሳካም፣ የእድገትና የትራንስፎርሜሽ እቅዱ የታሰበውን ያህል እየተሳካ እንዳልሆነና፣ በታለመለት መጠን እንዳልተሳካ እቅጩን ነግረውናል እርማችንን እንድናወጣ በሚል ።

 ግዙፎቹን ፕሮጀክቶች ተመልከቱ። ከሁሉም በላይ ትልቅ ትኩረት የተሰጠው የህዳሴ ግድብን መጥቀስ ይቻላል። በአምስት አመት ይጠናቀቃል የተባለው የህዳሴ ግድብ፣ አሁን በሚታየው ሁኔታ ከቀጠለ አስር አመት ሊፈጅ ይችላል። በሁለት አመት ውስጥ የተከናወነው ስራ 18 በመቶ ያህል ነውና። ሌሎቹ ትልልቅ ፕሮጀክቶችም ብንመለከት ከዚህ የተሻለ ውጤት አናገኝም። በአምስት አመቱ እቅድ ተገንብተው ስራ ይጀምራሉ የተባሉት 10 የስኳር ፋብሪካዎች፣ ገና በጣም ገና ናቸው። 10 አዳዲስ ፋብሪካዎችን ገንብቶ ለማጠናቀቅ ይቅርና፤ ከሰባትና ከስምንት አመት በፊት እቅድ ወጥቶላቸው ቢበዛ ቢበዛ በሶስት አመት ይጠናቀቃሉ ተብለው የነበሩት የስኳር ፋብሪካ ግንባታዎችና የማስፋፊያ ፕሮጀክቶችም እስካሁን ስራ አልጀመሩም።

በ1997ቱ የአምስት አመት እቅድ ውስጥ የተጀመረው የተንዳሆ ፕሮጀክት፣ የሸንኮራ ልማቱም ሆነ የስኳር ፋብሪካው ግንባታው ይሄው፣ ለ2002ቱ የአምስት አመት እቅድ ተሸጋግሮ አሁንም አልተጠናቀቀም። የመተሃራና የከሰም ፕሮጀክቶችም እንዲሁ እየተጓተቱና እየተሸጋገሩ የመጡ ነባር ፕሮጀክቶች ናቸው - በመጪው አመትም ስራ ይጀምራሉ ተብሎ አይጠበቅም። ሊጠናቀቅ ተቃርቧል የተባለው ነባሩ የወንጂ ስኳር ፋብሪካ ማስፋፊያ ፕሮጀክት እንኳ፤ በሚቀጥለው ወር፣ በሚቀጥለው የመንፈቅ አመት እየተባለ ስንት አመት አስቆጠረ? ይሄው ዘንድሮም፤ በጥቅምት ወር ስራ ይጀምራል ከተባለ በኋላ፤ ስራው ተጓትቶ ለጥር ይደርሳል ተባለ። ከዚያ ወደ መጋቢት ተሸጋገረ።

አሁን ደግሞ ወደ ሰኔ ወይም ወደ ሃምሌ። መንግስት እነዚህ ነባር ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅ ሳይችል፤ ተጨማሪ 10 አዳዲስ የስኳር ፋብሪካዎችን መገንባት ይችላል ብላችሁ የምታስቡ ከሆነ፤ “ተአምር” የማየት ረሃብ ይዟችኋል ማለት ነው። ሌላኛው ትልቅ ፕሮጀክት የባቡር ሃዲድ ግንባታ ነው። ይሄኛውም ፈቅ አላለም። ከሁሉም በላይ፣ በጣም ተስፋ አስቆራጭ የሆነው ደግሞ የእርሻ ምርት ብዙም ሲያድግ አለመታየቱ ነው። በአማካይ በነፍስ ወከፍ ሲሰላ፣ የእርሻ ምርት በየአመቱ በ6% እንዲያድግ ነበር የታቀደው - በእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ። የአምናው እድገት ግን፤ 2.5% ገደማ ብቻ ነው። የእቅዱ ግማሽ ያህል እንኳ አልተሳካም። መንግስትና ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ፣ ይህንን ያውቃሉ። በአምስት አመት ውስጥ ይተገበራል ተብሎ የወጣው “የእድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ”፣ የታሰበውን ያህል እየተሳካ እንዳልሆነ ኢህአደግ በግልፅ ባይናገርም፣ የገበሬዎች ምርት የታሰበውን ያህል እያደገ እንዳልሆነ የሚክደው አይመስለኝም።

እንዲያውም፤ የኢህአዴግ ድርጅቶች ሰሞኑን ባካሄዷቸው ጉባኤዎች ጉዳዩ ተነስቷል። የእርሻ ምርት ላይ የሚታየው እድገት ዝቅተኛ እንደሆነ በኢህአዴግ ጉባኤዎች በየጣልቃው ጠቀስቀስ ተደርጎ ሲታለፍ ታዝባችሁ ይሆናል። ለምሳሌ ብአዴን በባህርዳር ባካሄደው ጉባኤ ላይ፤ “የአምናው የእርሻ ምርት እንደተጠበቀው አይደለም” ተብሏል። በሃዋሳው ጉባኤ ደግሞ፣ “የሰብል ምርት ላይ ድክመት አለ” ተብሏል። አሳሳቢነቱ፣ የአምና ምርት ከጠበቀው በታች መሆኑ ብቻ አይደለም። የዘንድሮው የመኸር ምርትም እንደተጠበቀው እንዳልሆነ የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ጥናት ያረጋግጣል።

እናም፣ በነፍስ ወከፍ ሲሰላ፣ የዘንድሮ የግብርና ምርት እድገትም እንደአምናው 2.5 በመቶ ገደማ ብቻ እንደሚሆን ይገመታል። ምን ለማለት ፈልጌ ነው? እንደሌሎቹ ዋና ዋና የእድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅዶች ሁሉ፣ የእርሻ ምርትም የታቀደለትን ያህል እያደገ እንዳልሆነ ሊካድ አይችልም ለማለት ነው። በእርግጥ፣ ታዲያ በኢህአዴግ ጉባኤዎች ላይ ለምን በጨረፍታ ብቻ ተጠቅሶ ታለፈ? “አልተሳካልኝም” ብሎ መናገር አስጠልቶት ሊሆን ይችላል። በአራቱም ጉባኤዎች ላይ እጅግ ሲበዛ ተደጋግሞ የተነገረውስ ምንድነው? የኢህአዴግ ድርጅቶች በሙሉ በየፊናቸው ባካሄዱት ጉባኤ፤ በገጠርና በገበሬዎች ላይ ስኬታማ ውጤት እንዳስመዘገቡ ደጋግመው ገልፀዋል። የተመዘገበው ውጤት ግን የምርት እድገት አይደለም። እናስ ምንድነው? “በልማት ሠራዊት ግንባታ” እና “በተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ” ዙሪያ እጅግ “አስደናቂ ውጤት” መመዝገቡን ነዋ የገለፁት።

አስደናቂውን ውጤት የሚያብራሩ “ድንቅ” መረጃዎችና ሪፖርቶችም ቀርበዋል። በመቶ ሺ እና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ገበሬዎችን በ1ለ5 አደራጅተን ሰፊ “የልማት ሠራዊት” ገንብተናል ብለዋል የኢህአዴግ ድርጅቶች። በመቶ ሺ እና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ገበሬዎችን ለ”ተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ” በዘመቻ አሰልፈናል ተብሏል። በእርግጥም “የልማት ሠራዊት” ተገንብቶ፤ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ገበሬዎች “ለተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ” ለበርካታ ቀናት በዘመቻ ሲሰማሩና በየእለቱ እየጨፈሩ ሲመለሱ የሚያሳዩ የኢቲቪ ዘገባዎችን ተመልክተናል። ግን ምን ዋጋ አለው? የ“ልማት” እና የ“ሃብት” ውጤት አልተመዘገበም። የኢህአዴግ ድርጅቶች የሚያቀርቡት፣ ያ ሁሉ አስደናቂ ውጤትና ሪፖርት፤ በገበሬዎች የእርሻ ወይም የሰብል ምርት ላይ ከወትሮው የተለየ ቅንጣት ለውጥ አላመጣም።

ምን አስታወስኩ መሰላችሁ? ከአምስት አመት በፊት ነጋ ጠባ እንሰማው የነበር የ“ውሃ ማቆር” መፈክር። በ“ውሃ ማቆር” ምን ያህል አስደናቂ ውጤት እንደተመዘገ ለማስረዳት ይቀርቡ የነበሩ ድንቅ ሪፖርቶችን አታስታውሱም? በየክልሉ ምን ያህል እልፍ አእላፍ ገበሬዎች፣ ውሃ ማቆሪያ ጉድጓድ እንደቆፈሩ፣ በላስቲክና በሲሚንቶ ጉድጉዱን እያበጃጁ እንደሆነ በዝርዝር የሚተነትኑ እልፍ ዘገባዎችና ሪፖርቶች ቀርበዋል - ያኔ ከአምስት አመት በፊት። ለውሃ ማቆር ዘመቻ ስንትና ስንት ሚሊዮን ብር እንደተመደበ፣ በመቶ ሺ እና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ገበሬዎችም በዘመቻው እንደተሳተፉ… የሚያብራሩና የሚዘረዝሩ ሪፖርቶች ትዝ አይሏችሁም? ምን ያደርጋል! አገሪቱ በ’ውሃ ማቆር’ ዘመቻ እንደምትለወጥ የሚያበስሩ ድንቅ ሪፖርቶች ሲቀርቡና ሲደመጡ ከርመው፣ ወራት አልፈው አመታት ተተክተው… መጨረሻ ላይ ሲታይ፤ ምንም ጠብ የሚል ውጤት ጠፋ።

በቃ፤ በገበሬዎች ምርት ላይ ምንም የመጣ ለውጥ የለም ተባለ። የኋላ ኋላ፣ የፌደራል ባለስልጣናትና ከየክልሉ የመጡ ርዕሰ መስተዳድሮችና ከፍተኛ መሪዎች በተሰበሰቡበት ነው ፍርጥርጡ የወጣው። በእርግጥ በስብሰባው ላይ፣ እንደወትሮው ድንቅ የውሃ ማቆር ሪፖርቶችና ማብራሪያዎች ቀርበዋል። በዚህ መሃል ነው፣ አንድ ቀላል ጥያቄ ዱብ ያለው… “ግን በገበሬዎች ምርት ላይ ያመጣው ለውጥ ምንድነው?” የሚል ጥያቄ። ጥያቄውን ለፌደራልና ለክልል ከፍተኛ መሪዎችና ባለስልጣናት በአፅንኦት ያቀረቡት ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ ነበሩ። ከመነሻው “ውሃ ማቆር” የሚለው ሃሳብ የመጣው፤ የገበሬዎችን ምርት የማሳደግ አላማን ለማሳካት ነበር።

አሁን ግን፣ የተነሳንበት አላማ እየተረሳ፣ የውሃ ማቆሪያ ጉድጓዶችን የመቁጠርና የመደመር ነገር… ራሱን የቻለ አላማ እየሆነ መጥቷል ያሉት አቶ መለስ፤ ሥራው የገበሬዎችን ምርት ለማሳደግ በሚጠቅም መንገድ እየተሰራ ነው ወይ? የውሃ ማቆር ዘመቻው ወደ ገበሬው ኪስ ተጨማሪ ገቢ በሚያመጣ መንገድ እየተሰራ ነው ወይ? በማለት አጥብቀው ጠይቀዋል። በእርግጥ፤ የውሃ ማቆር ዘመቻውን በቀዳሚነት ያቀነቀኑት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሊሆኑ እንደሚችሉ የሚገምቱ ሰዎች አሉ። ነገር ግን፤ እዚህ ላይ ዋናው ቁምነገር፣ የሆነ እቅድ የታሰበለትን ውጤት እያስገኘ እንዳልሆነ በተግባር ሲታይ፣ ሳይረፍድበት ቆም ብሎ ማሰብ ማስፈለጉ ነው።

አለበለዚያ፣ ያሸበረቀ ሪፖርት ማዘጋጀትና የተንቆጠቆጠ መግለጫ ማቅረብ፤ በአንዳች ተአምር ወደ ምርት እድገትና ወደ ኢኮኖሚ እድገት እንዲቀየር እየተቁለጨለጩ መጠበቅ ይሆናል። የሆነ ሆኖ፤ “የውሃ ማቆር ዘመቻው ምን አይነት ተጨባጭ ውጤት አስገኘ?” በሚለው ጥያቄ አማካኝነት ነገሩ መቋጫ አገኘ። ከዚያ በኋላማ በየእለቱና በየሰዓቱ በሬድዮና በቲቪ ሲያሰለቸን የነበረው የውሃ ማቆር ነገር ድምፁ ጠፋ። በውሃ ማቆር ፋንታ፤ ባለፉት ሁለት አመታት በመንግስት ሚዲያ የሚቀርብልን የዘወትር ቁርስና እራት፤ “የልማት ሠራዊት ግንባታ” እና “የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ” በሚሉ ሃረጎች የተጥለቀለቁ “ድንቅ ሪፖርቶችና መግለጫዎች” ናቸው - የገበሬዎችን ምርት ለማሳደግ ይጠቅማሉ እየተባለ። ነገር ግን፣ የአምናውና የዘንድሮው ተጨባጭ የምርት መጠን ሲታይ፣ እነዚያ ድንቅ ሪፖርቶች፣ የገበሬዎችን ምርት ለማሳደግ እየጠቀሙ አለመሆናቸውን መገንዘብ ይቻላል።

በ1ለ5 የተደራጀ ገበሬና በየቀበሌው ለስራ ዘመቻ የተጠራ ገበሬ ምን ያህል እንደሆነ እየቆጠሩ “ድንቅ ሪፖርት” ማቅረብ… ራሱን የቻለ ትልቅ አላማ እየሆነ መጥቷል። ይሄ ግን አያዛልቅም። ገበሬዎችን በተፅእኖ አደራጅቶ በዘመቻ እንዲሰሩ ማድረግ፤ ወደ ገበሬዎቹ ኪስ ተጨማሪ ገቢ አያመጣም። እፍኝ የእህል ምርት ለማሳደግም አይጠቅምም፤ ገበሬዎችን ከእውነተኛው የምርት ስራ ከማስተጓጎል ያለፈ ጥቅም አያስገኝም። አሁን ያለው አንዱ አማራጭ፤ “የሠራዊት ግንባታ” እና “የሥራ ዘመቻ” ሪፖርቶችን እያሳመሩ በመጓዝ ያለመፍትሄ ውድቀትን መደገስ ነው። ሌላኛው አማራጭ ደግሞ፤ የአምስት አመቱ እቅድ እየተሳካ እንዳልሆነ በግልፅ ተናግሮ፤ በሌሎች የኢኮኖሚ መስኮች ላይ እንደሚታየው የመንግስት ገናናነት መልካም ውጤት እንደማያስገኝ ተገንዝቦ መፍትሄ መፈለግ ነው። ኢህአዴግ የትኛውን አቅጣጫ እንደሚመርጥ እስካሁን በግልፅ አይታወቅም።

 Written by  Super User

አገር ቤት ያሉ ተቃዋሚዎች “እንቅልፍን” በተመለከተ አማኑኤል ዘሰላም

«የተቃዋሚ ድርጅቶች ሰላማዊ ትግል ? ወይንስ ሰላማዊ እንቅልፍ ?» በሚል ርእስ፣ ስማቸዉን ያልጠቀሱ አንድ ኢትዮጵያዊ የጻፉትን ጽሁፍ አነበብኩ። አገር ቤት ባሉ «የተቃዋሚ ፓርቲዎች ነን» በሚሉ ድርጅቶች ላይ ያተኮረ ጽሁፍ ነዉ። አገር ቤት የሚንቀሳቀሱ በርካታ የፖለቲካ ድርጅቶች እያሉ፣ እስከመቼ ሕዝብ መብቱና ነጻነቱ ተረግጦ እንደሚኖር ያሳሰባቸው ይመስላል። ተቃዋሚዎች በሥራ ላይ ሳይሆን በእንቅፍል ላይ እንዳሉም በመግልጽ ተቃዋሚዎቹ ሊመስልሱት የሚገባ ጥያቄዎችን አስቀምጠዋል።

«የሕዝብ የበላይነትን ለማረጋገጥ እንታገላለን የሚሉ የተቃዋሚ ድርጅቶች ምን እየሰሩ ነው? ሕዝብን አስተባብረው ወደሚፈለገው ለውጥ መጓዝ ያልቻሉበትስ ምክንያት ምንድነው?» የሚሉት ጥያቄዎች በዋናነት የተቀመጡ ናቸዉ፡፡

ይመስለኛል እኝህ ጸሃፊ በዉጭ አገር የሚኖሩ፣ በሕዝባቸው ላይ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየደረሰ ባለዉ ግፍ ያዘኑና የተቆጡ፣ አገራቸዉን የሚወዱ ኢትዮጵያዊ መሰሉኝ። ጊዜ ወስደው፣ ካላቸው አገራዊ ተቆርቋሪነት የተነሳ፣ ይህን መልካም ጽሁፍ ስላበረከቱልን ምስጋናዬንና አክብሮቴን ላቀርብ እወዳለሁ።

ስለተቃዋሚዎች በምናነሳበት ጊዜ ተቃዋሚዎችን በተለያዩ ክፍሎች ልንመድባቸው እንችላለን። መስክረም 2005 ፕ/ር አል ማርያም “Ethiopia’s opposition at the dawn of democracy?” በሚል ጽሁፋቸዉ ተቃዋሚዎችን በአምስት ከፍለዋቸዋል። ታማኝ ተቃዋሚዎች፣ ዝምታን የመረጡ ወይም ዝም እንዲሉ የተገደዱ ተቃዋምዊዎች፣ ያልተደራጁ ተቃዋሚዎች፣ የተከፋፈሉ ተቃዋሚዎች፣ አንድ ሆነው መርህ ያላቸዉ ዴሞክራቲክ ተቃዋሚዎች። ፕ/ር አል ማሪያም ከዘረዘሩት አምስቱ በተጨማሪ፣ በስድስተኛነት ፣ በዉጭ አገር ያሉትን ተቃዋሚዎች እጨምራለሁ። እንግዲህ የትኛዉ አይነት ተቃዋሚች እንደሆኑ ሳንለይ፣ በጅምላ በተቃዋሚዎች ላይ ትችት ማቅረብ ትንሽ የሚያስቸግር ይመስለኛል።

በዉጭ አገር ያሉ ተቃዋሚዎች በዉጭ አገር ያሉ ተቃዋምዊች ናቸው። ከሕዝቡ እንደመራቃቸው፣ ሕዝብን መርተዉና አደራጀተዉ የሚፈለገዉን ዉጤት ማምጣት ይችላሉ ብሎ ማሰብ ትንሽ አሰቸጋሪ ነዉ። አንዱ ትግሉን የጎዳዉ ትልቁ ችግር፣ አገር ቤት የሚኖረዉ ሕዝብ፣ በነዚህ ዉጭ አገር ባሉ ድርጅቶች ላይ ብቻ ተስፋ ማድረጉ ነዉ። በስፋት ትግሉን በአገር ቤት ከመቀላቀል ይልቅ፣ ዉጭ ያሉ ድርጅቶች ታግለዉና ተዋግተዉ ነጻ እንዲያወጡት ይጠበቃል። ይህ ትልቅ ስህተት ነዉ።

 

 እዉነትን እና የተጨበጠ መረጃ ይዘን የምንነጋገር ከሆነ፣ እንኳን የሚጠበቀዉን ለዉጥ፣ ፈረንጆች እንደሚሉት በሪሞት ኮንትሮል ከሩቅ ሆኖ ሊያመጣ ቀርቶ፣ ጭላንጭል ተስፋ የሚሰጥ ድርጅት በዉጭ አገር አለ ለማለት ይቸግራል። (ከተሳሳትኩ ለመታረም ዝግጁ ነኝ ) መሰረቱን አሰመራ ያደረገዉ የግንቦት ሰባት እና የኦነግ ትብብር፣ እንደ ኢሕአፓ-ዴ ያሉ ድርጅቶችን ያቀፈው ሸንጎ፣ በነዶር እሸቱ የሚመራዉ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር መንግስት የመሳሰሉ በዉጭ አገር በርካታ ድርጅቶች አሉ። እናውቃቸዋለን። አብረዉን ነዉ ያሉት። ጥረታቸውን ድካማቸውን እናከብራለን። ነገር ግን እነዚህ ድርጅቶች ፍቃደኛ ሆነዉ፣ ከአገር ቤት የተነጠለ ትግል ምንም ሊያመጣ እንደማይችሉ ተረድተዉ፣ አገር ቤት የሚደረገዉን ሰላማዊ ትግል በማገዝ አስተዋጽኦ ሊያብረክቱ ይችላሉ እንጂ በራሳቸዉ ምንም ሊያመጡ አይችሉም። ይሄን ሐቅ ኢትዮጵያዉን በጥንቃቄ መገንዘብ ያለብን ይመስለኛል።

አገር ቤት ወዳሉት ተቃዋሚዎቾ ስንመለስ፣ ፕ/ር አል ማርያም እንዳሉት ታማኝ ተቃዋሚዎች አሉ። እነዚህ ለይስሙላ «ተቃዋሚዎች አሉ ለማስባል» በገዢዉ ፓርቲ የተጠፈጠፉ የዉሽት ተቃዋምዊች ናቸው። የአየለ ጫሚሶን ቅንጅት እንደምሳሌ መጥቀስ እንችላለን።

ታማኝ ተቃዋሚ ያልሆኑ፣ ነገር ግን እንደሚገባው ያልተደራጁ ፣ በመካከላቸው ክፍፍል የነበረባቸዉና ያለባቸዉ በርካታ የተቃዋሚ ድርጅቶች አሉ። የአንድነት ፓርቲ፣ የሰማያዊ ፓርቲ፣ የመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት፣ አረና ትግራይ የመሳሰሉ ፣ ከሰላሳ በላይ የሚሆኑ ድርጅቶች የመከፋፈሉን እና የመደራጀቱን ጉዳይ ትኩረት ሰጥተዉት በአንድ ላይ ለመስራት ጥረት እያደረጉ ነዉ። የጋራ የመግባቢያ ሰነድ ፈርመዉ፣ የዲሞክራሲ ተቋማት ጻና ገለልተኛ የሚሆኑበትን ሁኔታ ለማመቻቸት የጋራ ትግል ጀምረዋል። እንግዲህ ይህ በአንድነት ለመስራትና ለመንቀሳቀስ የሚደረገዉ ጥረት በራሱ ትልቅ ሥራ ነዉ።

እህል ሳይዘራ አይታጨድም። ሳይታጨድ አይወቃም። ሳይወቃ አይፈጭም። ሳይፈጭ አይቦካም። ሳይቦካም አይጋገርም። ብዙዎቻን የምንጠበቀው ዉጤት እንዲመጣ ከፈለገን፣ ብዙ መሰራት ያለብን ሥራ አለ። በአቋራጭና በአንዲት ጀንበር ድል አይገኝም። አገር ቤት ያሉ የተቃዋሚ ድርጅቶች አይመስለንም እንጂ፣ በዉጭ አገር ያሉ ሜዲያዎች እየተከታተሉ በስፋት አይዘግቡትም እንጂ፣ እጅግ በጣም ከባድና ዉስብስብ በሆነ ሁኔታ ሕዝቡን ለማደራጀትና ለማስተማር እየሞከሩ ነዉ። አቶ በቀለ ገርባ የኦፌኮ አመራር አባል ናቸዉ። በእሥር ቤት ይገኛሉ። አቶ አንዱዋለም አራጌ የአንድነት ፓርቲ አመራር አባል ናቸው። በእሥር ቤት ይገኛሉ። ወ/ት ርዮት አለሙ ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር ቅርበት ያላት ናት። በእሥር ቤት ትገኛለች።

«የተቃዋሚ ድርጅቶች አያሌ አባሎቻቸውና መሪዎቻቸውንም ጨምሮ በወያኔ የሃሰት ውንጀላ በየ እስር ቤቱ ውስጥ ታጉረው እየማቀቁ ቢሆኑም ድርጅቶቹ ህዝብን አስተባብረው ጫና በመፍጠር ለማስፈታት ያደረጉት ሙከራ የለም» ሲሉ ከላይ የጠቀስኳቸው ጸሐፊ ትችት አቅርበዋል። አንድ የዘነጉት ጉዳይ ቢኖር ግን ፣ እነዚህ ዜጎች መጀመሪያዉኑ የታሰሩት፣ ድርጅታቸው ሥራ እየሰራ ስለነበረና መታሰራቸውም ከሥራ የተነሳ እንደሆነ ነዉ። ጸሃፊዉ እንዳሉት፣ ሕዝብ ሆ ብሉ መሪዎችን ለማስፈታት እንዲነሳ ደግሞ መደራጀት አለበት። ህዝብን ለሰላማዊ ትግል ለማደረጀት መረጃ ቁልፍ ነዉ። ያለ መረጃ ፣ ያለ ንቃት ሕዝብን ማደራጀት አይቻልም። ሕዝብ ከፍርሃት እንዲላቀቅ፣ በራሱ እንዲተማመን ለማድረግ ሕዝብን ማስተማርና ማሳመን የግድ ነዉ። የአንድነት ልሳን የሆነችዉ የፍኖት ጋዜጣም በአገዝዙ እንዳትታተም እስከተደረገችበት ጊዜ ድረስ፣ በዚህ ረገድ ትልቅ ሚና ተጫዉታለች; የፍኖት ጋዜጣ አዘጋጆችም ሆነ የአንድነት ፖርቲ አመራር አባላት ፣ ሊታሰሩ እንደሚችሉ እያወቁም፣ ሳይፈሩ መረጃዎች ለሕዝብ ለማቅረብ ሞክረዋል። ይህ አይነቱ ሕዝብን የማስተማርና የማንቃት እንቅስቃሴ ሌላዉ ትልቅ ሥራ ነዉ።
ገዢዉ ፓርቲ ግን በብርሃነ ሰላም ማተሚያ ቤት ፍኖት እንዳትታተም አደረገ። የአንድነት ፓርቲ ግን ዝም ማለትን አልመረጠም። ጫና በበዛ ቁጥር ግፊቱን ቀጠለ። የፍኖት ማተሚያ ማሽንን ለመግዛት እንቅስቃሴ ላይ ይገኛል።

ከአንድነት ፓርቲ ጋር በቅርበት የሚሰራ አንድ የፖለቲካ ድርጅት አለ። ሰማያዊ ፓርቲ ይባላል። (በጣም ተስፋ አደርጋለሁ ሰማያዊ ፓርቲ ከአንድነት ፓርቲ ጋር እንደሚዋሃድ) ሰማያዊ ፓርቲ ፣ አገራዊ አጀንዳ አንግቦ ከ30000 ሺህ በላይ ለሆነው ወገናችን ደም መፍሰስ ምክንያት የነበረዉ፣ የግራዚያኒ ሓዉልትን በተመለከተ፣ በአዲስ አበበ ስድስት ኪሎ ሰላማዊ ሰልፍ ጠርቶ ነበር። የዜጎች የመሰብሰብ መብት በአገዛዙ ተረግጦ፣ ከአርባ በላይ ኢትዮጵያዉያን ታስረዉ ነበር። ዶር ያእቆብ ኃይለማሪያም እንዲሁም በርካታ የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አባላት ወህኒ በመውረድ የአገዛዙን አምባገነንነት አጋልጠዋል። ለካቴና እጆቻቸዉን በመስጠት ለሕዝቡ ድፍረትን በተግባር አስተምረዋል። ይሄ ትልቅ ሥራ ነዉ።

በዋቢ ሸበሌ በተደረገ ሥነ ስርዓት፣ ገንዘብ ከፍለዉ እንዳይገቡ የታገዱ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች፣ ከሆቴሉ አስተዳደር ጋር ሲከራከሩ የሚያሳይ ቪዲዮ በበርካታ ድህረ ገጾች ተለቆ አይተናል። የተወሰኑ ወደ ሆቴል ቤቱ ሲገቡ ፣ የተወሰኑቱ ግን እንዳይገቡ ሲከለከሉ ነዉ ያየነዉ። ምን ያህል የአፓርታይድ አይነት ሥርዓት በአገራችን እየተስፋፋ እንደሆነ ነዉ በይፋ ለማረጋገጥ የተቻለዉ። ኢትዮጵያ ለሁሉም ዜጎቿ እኩል የሆነች ሳይሆን፣ አንዱ የሌላዉ የበላይ ሆኖ፣ አንዱ ሌላዉን እየረገጠና እየጨቆነ የሚኖርባት አገር እንደሆነች ነዉ፣ የሰማያዎ ፓርቲ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ያስተማረዉ። ይሄም እራሱን የቻለ ትልቅ ሥራ ነዉ።

እንግዲህ እነዚህን ምሳሌ የምጠቀሰው «በአገር ቤት ያሉ የተቃዋሚ ድርጅቶች ያንቀላፉ ናቸዉ» ለሚለዉ የተሳሳተ አባባል እርማት ለመስጠት ነዉ። የድርጅቶች ልሳኖች እንዳይታተሙ እያታገዱ፣ ያን አልፎ በመሄድ የማተሚያ ማሽን ለመግዛት ጥረት እየተደረገ፣ ኢትዮያዊ አጀንዳዎች ተይዘው ተቃዉሞ ለማሰማት እየተሞከረ፣ በዚያም ምክንያት ዜጎች እየታሰሩ ምንም ነገር አልተሰራም ማለት ትንሽ ያስቸግራል። ያለ ማጋነን፣ በዉጭ አገር አለን ከሚሉና በብዙ ሺህ ዶላሮች ከሚደገፉ ድርጅቶ ጋር ሲነጻጻሩ፣ አገር ቤት ያሉ ደርጅቶች ከሃያ በላይ እጥፍ ትልቅ አስተዋጾ እያደረጉ ናቸዉ።

ይህን ስል መሰራት የነበረባቸውን ሥራዎች በብቃት ሰርተዋል ማለቴ አይደለም። ይህን ስል መተቸት የለባቸውም ማለቴ አይደለም። በቅርቡ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ያቀረባቸውን ጠንካራ ገንቢ ትችቶች መመልከት ይቻላል። በርግጥ አገር ቤት ያሉ ተቃዋሚዎች ብዙ ማስተካከል ያላባቸዉ አሰራሮች፣ መስራት ያላባቸዉ ተግባራት አሉ።በተለይም መድረክ የሚባለው ስብስብ ትልቅ ችግር አለበት።

ነገር ግን አልተሰሩም የምንላቸውን ተግባራት ለምን አልሰሩም ብለን ዳር ሆነን ከምንከስ፣ ለምን መሰራት ያላባቸውን እንዲሰሩ አናግዛቸውም ባይ ነኝ። አገር ቤት ያሉ የተቃዋሚ አመራር አባላት ብቻቸዉን ሁሉንም ሊሰሩ አይችሉም።

ሕዝቡን ለማደራጀት ከፍተኛ የሕዝብ ግንኙነት ሥራ መሥራት ይጠይቃል። ለዚህም ቴለቭዥን፣ ራዲዮ፣ ጋዜጣ፣ ኢንተርኔት የመሳሰሉ አስፈላጊ ናቸዉ። በአገራችን ቴሌቭዥኑን እና ራዲዮዉን እንርሳው ። ገዢዉ ፓርቲ ከቻይና ባገኘዉ ቴክኖሎጂ በቀላሉ አፈና በማድረግ መረጃዎች ለሕዝብ እንዳይደርሱ ማድረግ ይችላል። ኢንተርኔትን በተመለከተ ከሶማሊያና ከኬንያ በባሰ መልኩ ኢንተርኔት በኢትዮጵያ እንዳያድግ ተደርጓል። የብሮድ ባንድ ኢንተርኔት ተጠቃሚ ክፍል ከ0.1 % ያነሰ ነዉ። በመሆኑም በፌስቡክ በመሳሰሉ ሜዲያዎች በብቃት የሕዝብ ግንኙነት ሥራ ለመስራት ያስቸግራል።

የቀረዉ እንድ መንገድ ጋዜጣ ነዉ። ይችኑ የቀረችዋን ለማፈንም ገዢው ፖርቲ ማተሚያ ቤቶችን በመጠቀም ነጻ ጋዜጦች እንዳይወጡ እያደረገ ነዉ። ፍትህ ጋዜጣ ተዘግታለች። ፍኖት ጋዜጣ አትታተም።

የአንድነት ፓርቲ ግን ዝምታን አልመረጠም። እየተንቀሳቀሰ ነዉ። የማተሚያ ማሽን ገዝቶ ሕዝብን ለማስተማርና ለማደራጀት እየጣረ ነዉ። እንግዲህ ከኛ የሚጠበቀዉ የሥራዉ አካል መሆን ነዉ። የማተሚያ ማሽኑን ለመግዛት 50 ሺህ ዶላር አካባቢ ያስፈልጋል።በዉጭ አገር የሚኖረው ኢትዮጵያዊ 2 ሚሊዮን ይጠጋል። 50 ሺ የሚሆኑቱ አንድ ዶላር፣ 5 ሺህ የሚሆኑቱ አሥር ዶላር፣ 5 መቶ የሚሆኑቱ አንድ መቶ ዶላር፣ አምሳ የሚሆኑቱ አንድ ሺህ ዶላር ቢያዋጡ ይሄ ማሽን በቀላሉ ሊገዛና ለጥቅም ሊዉል ይችላል። አንድ ተብሎ ነዉ ወደ ሁለት የሚኬደው። መቶ ሜትር መሮጥ ሳንችል የማራቶን ወርቅ መጠበቅ የለብንም። መደመር ሳይቻል ማባዛቱ የማይሞከር ነዉ።
እንግዲህ አገር ቤት ያሉ ትግሉን ወደፊት እንዲወስዱ እንደምንጎተጎታቸው ሁሉ፣ እኛም የድርሻችንን ለመወጣት እንዘጋጅ። ኢትዮጵያ የሁላችንም ናት !

ህወሃት እንደፓርቲ---ግብጽ እንደሃገር---ካለፈው የቀጠለ ክፍል3

ህወሃት እንደፓርቲ---ግብጽ እንደሃገር---ካለፈው የቀጠለ ክፍል3
ባለፉት ሁለት ክፍሎችበ www.miniliksalsawi.blogspot.com ላይ ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ካለምንም ሃገራዊ ዉክልና እና ሞራል እንደኢትዮጵያ ሆኖ ከግብጽ ጋር ብሄራዊ ጥቅማችን ላይ እየተነጋገረ እንደሄደ እና በሃገር ቤት ያሉ ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴዎችን በፈጠራቸው ድህረገስኦቹ ላይ ራሱን ከዚህ ብሄራዊ ጥቅም የመሸጥ ወንጀል ለመደበቅ ግብጽ አገር ቤት ቅጥረኞችን አሰማርታለች ሲል እየከሰሰ ነው::
የግብጽ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በኢትዮጵያው ተዋህዶ ላይ ያላትን የበላይነት ለማረጋገጥ በአማካሪነት ስም ለማሽከርከር ያቀረበችውን ጥያቄ የወያኔ መንግስት ሳያንገራግር ጳጳሳቱ እንዲቀበሉት ግፊት ቢያደርግም አልተሳካለትም ነበር ::ቤተ ክርስቲያኗ የራሷ የሰለጠኑ እና የተማሩ ሊቃውንት አማካሪዎች እያሉ ከግብጽ ለምን ጥያቄ ቀረበ ለምንስ ላማስመጣት ተፈለገ?? አልተሳካም እንጂ ያልተመለሱ ጥያቄዎች ነበሩ በጊዜው::
File:Egyptian General Intelligence Service (GIS) headquarters in Hadaeq Al Qubbah.jpg
የወያኔ የደህንነት አባላት ወደ ግብጽ በሚያደርጉት በረራ የተለያዩ ስጦታዎች እና የግንዘብ ጉርሻዎች ስለሚሰጣቸው የተለያዩ ሃገራዊ ሰነዶችን እየሸጡ ነው:: በትግራይ ተወላጆች የተመራው ወያኔ መራሹ ወደ ግብጽ በራሪ የደህንነት ሹሞች ከህወሃት አባላት ዉጪ ለላው ኢትዮጵያዊ በዚህ ቡድን አልተካተተም :: የአባይ የሚሊኒየም እቅድ ዝርዝር በየቀኑ ሪፖርት የሚደረግላት ግብጽ አፏን ሞልታ የምትናገረው ይሀው የሚሰጣትን መረጃ ተገን በማድረግ ከሷም አልፎ የሳኡዲ እና የኳታር መንግስታት በገሃድም ይሁን በስውር በሃገራችን ደህንነት ላይ ዘምተው ይገኛሉ::
በእርግጥ ግብጽ ከኤርትራ ጋር በጸረ ኢትዮጵያ ጉዳዮች ሱዳንን ይዛ የተወዳጀች ቢሆንም ከኤርትራ ይልቅ በወያኔ የደህንነት መረጃዎች ላይ አትኩሮቷን አድርጋ እየተከታተለችን ነው::እነዚህ የነጻ አውጪነት አጉል አውሬያዊ ባህሪ ያለቀቃቸው አሁንም ትግራይ ሪፑብሊክን ለመመስረት ቋምጠው ያሉት የወያኔ አናቶች ለዚህ ጉዳይ ይረዳቸው ዘንድ ግብጽን እየተንከባከቧት ነው:: በዚህ ጉዳይ ለሁለት የተከፈለው የደህንነት ቡድን ካይሮ ላይ የጥቅም ግጭት አድርጎ እንደነበር ከዚህ በፊት የወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ :: የግብጽ መንግስት የሰጣቸውን 90.000 ዶላር በጋራ እኩል ነው የምንካፈለው በማለት የተበጣበጠው የደህንነት ቡድን ከመስከረም 2013 ጀምሮ ተኮራርፎ ይገኛል:: የቡድኑ ሁለት መሪዎች በጋራ 40.000 ዶላር ሲወስዱ ለሎቹ ቀሪውን 50.000 ዶላር ለ5 እንዲካፈሉት አዘው ነበር ይህ ጉዳይ የተከሰተው::
በአሁኑ በተገኘበት ሁሉ ብላ እንብላ የሚል አባዜ የያዛቸው ወያኔዎች እና ጀሌዎቻቸው ከመውደቃቸው በፊት በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ገንዘቦችን እያግበሰበሱ ሲሆን በበተሰቦቻቸው ስም በተለያዩ የሃገር ዉስጥ እና የውጪ ባንኮች እያስቀመጡት ይገኛሉ:: አፉን ለጎሞ ለምን ማለት የተሳነው ህዝብ እንዲሁም የፖለቲካ ብቃት ማነስ ያለበት ማህበረሰብ በጦር ሰራዊቱ እና በፖሊስ የማይተማመነው ኢትዮጵያዊ ካለምንም ትንፋሽ አገሪቷ ስትበዘበዝ እያየ ነው::በሃገር ውስጥ በተለያዩ ቦታዎውች በጎረቤት አገራት እና በተለያዩ የአውሮፓ አገራት በቤተሰቦቻቸው ስም የተገነቡ ህንጻዎች እና ሌሎች ንብረቶች ባለቤት የሆኑ ሃገር በዝባዥ ግለሰቦች እና ቡድኖች በሃገራችን ብሄራዊ ጥቅም ላይ ከግብጽ መንግስት ጋር እየተነጋገሩ መገኘቱ ምን ያህል ሞራላቸው እንደሚፈቅድላቸው እያጠያየቀ ነው:;

 “በራሳችን መሐንዲስ፣ በራሳችን ገንዘብ፣ በራሳችን የተባበረ ክንድ እንገነባዋለን” በማለት ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በመስቀል አደባባይ ታላቅ ህዝባዊ ድጋፍና “መዓበላዊ መነቃቃት” ፈጠሩበት የተባለለት የ”ህዳሴው” ግድብ 51 በመቶ ድርሻ የኢትዮጵያ እንዳልሆነ ነዋሪነታቸው በአውሮፓ የሆነ ዲፕሎማት በተለይ ለጎልጉል ገለጹ።

ስማቸው ምስጢር እንዲሆን የጠየቁት ዲፕሎማት እንዳሉት 51 በመቶ ባለድርሻ የሆነችው አገር አውሮፓ የምትገኝ የኢትዮጵያ አጋር አገር ናት። ለጊዜው የባለድርሻዋን አገር ስም መግለጽና የውሉን ዝርዝር ይፋ ማድረግ ያልፈለጉት ዲፕሎማት ኢትዮጵያ በግድቡ ላይ የፈለገችውን ውሳኔ በራስዋ ለማስተላለፍ እንደማትችል፤ ያላት ድርሻ 49 በመቶ ብቻ በመሆኑ ድምጽን በድምጽ በሚሽረው በአብላጫ ድምጽ ህግ መሰረት በግድቡ ላይ የሚወሰነው ውሳኔ 51 በመቶ ባለድርሻ በሆነችው አውሮፓዊቷ አገር መሆኑን አብራርተዋል።

49 በመቶ ተብሎ የተገለጸው የድርሻ መጠን ጅቡቲን ጨምሮ የተለያዩ አገሮች የተቀራመቱት መሆኑን ያመለከቱት የመረጃው ባለቤት፣ አገር ውስጥ ካሉት የንግድ ተቋማት መካከል ኤፈርት ትልቁን ድርሻ መውሰዱን እንደሚያውቁ ተናግረዋል።

የመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ የግል ባለሃብቶች፣ ማህበራት፣ ባንኮችና የተለያዩ ግለሰቦች በትዕዛዝ አክሲዮን መግዛታቸውን ያስታወሱት እኚሁ ዲፕሎማት “በግድቡ ዙሪያ ከሚፈራው የጸጥታ ችግር በላይ አስጊው ጉዳይ የባለድርሻዎች ምስጢር መሆን ነው” ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።

መንግስት ለግንባታው የሚሆን ከፍተኛ ገንዘብ ከአውሮፓዊቷ አገር ማግኘቱን ያመለከቱት የጎልጉል ምንጭ፣ “ከአገር ውስጥ በአክሲዮን ስም የሚሰበሰበው ገንዘብ ለአገር ውስጥ በጀት ማሟያና ለመንግስት የስራ ማከናወኛ የሚውል ነው” ብለዋል።

መንግስት በተለያየ መድረክ በተደጋጋሚ ፕሮጀክቱ “በአገር ውስጥ ባለሙያ፣ በአገር ውስጥ ሃብት፣ የሚከናወን የህዳሴ መገለጫ ነው” በሚል ብሄራዊ መነቃቃት የተፈጠረበት የአቶ መለስ ማስታወሻ እንደሆነ ከመግለጽ ውጪ ስለ አክሲዮን ድርሻና አክሲዮን ስለገዙ አገራት እስካሁን የተናገረው የለም።

ግድቡ በመጀመሪያው ምዕራፍ ሲጠናቀቅ 5 ቢሊዮን ዶላር እንደሚፈጅ መገለጹ ይታወሳል። የአባይ ግድብ ከሱዳን ድንበር 10 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ቤኒሻንጉል ክልል እንደሚገኝ መንግስት የግድቡን ሥራ ይፋ ሲያደርግ ማስታወቁ አይዘነጋም።

ይህ በእንዲህ እያለ ፋና በዛሬው እለት ባሰራጨው ዜና “የወንዙን ተፈጥሯዊ የፍሰት አቅጣጫ የማስቀየሩ ስራ እየተሰራ” መሆኑን የገለጸ ሲሆን፥ “ወንዙ ይሄድበት የነበረውን ቦታ 1780 ሜትር ከፍታ ያለው ግድብ የመካከለኛው ክፍል የሚያርፍበት እንደሚሆንም” የፕሮጀክቱ ሥራአስኪያጅ ኢንጅነር ስመኘው መናገራቸውን ጠቅሷል። “አቅጣጫውን የማስቀየሩ ስራ ከመጭው ክረምት በፊት” ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን መሃንዲሱ ጠቅሰው፥ በቅርቡም ዕውን ይሆናል ብለዋል። ግድቡ ግንባታው የተጀመረበት 1ኛ ዓመት በዓልም ከመጪው ረቡዕ ጀምሮ በአዲስ አበባ፥ እንዲሁም መጋቢት 24 ፕሮጀክቱ በሚገኝበት ስፍራ በተለያዩ ስነ ጥበባዊ ዝግጅቶችና ‘መለስ ቃልህ ይከበራል፤ ታላቁ የህዳሴ ግድብም በህዝባችን ተሳትፎ እውን ይሆናል’ በሚል መሪ ቃል ይከበራል” በማለት የዜናው ዘገባ ገልጾዋል።


ወያኔዎች በካይሮ እና በአሌክሳንደሪያ የተለያዩ የመኖሪያ ቤት ለመገንባት የሚያስችላቸውን መሬት ከግብጽ መንግስት ያገኙ ሲሆን በዚህ ላይ በፎቶ የተደገፈ ዝርዝር መረጃዎችን ለማቅረብ እየተዘጋጀን ነው:: እነዚሁ የደህንነት አባላት ከበላይ የወያኔ አካላት የሚሰጣቸውን መረጃ በመያዝ በጉርሻ ወደምታጠግባቸው ግብጽ ሲሄዱ በተመሳሳይ ወደ ግብጽ በዲፕሎማቲክነት ሽፋን የመጡ የግብጽ የስለላ ቡድን አባላትን የአባይን እና የግድቡን አከባቢ እያስገነቡ የካርታ እና የፎቶ መርጃ እየሰጡ ዳጎስ ያለ ገንዘብ ክርግብጽ የደህንነት ቢሮ ያገኛሉ::
በቅርቡ በግብጽ ወያኔዎች እያደረጉ የለውን ጥቅማዊ እንቅስቃሴ በተመለከተ በፎቶ የተደገፈ ማስረጃ ከነስም ዝርዝራቸው ይዘን እንመጣለን::

“ነብዩ ኤልያስ ወደ ኢትዮጵያ መጥቷል !!”የኤልያሳውያን አማኞች አዲስ አበባውያን

 

“ነብዩ ኤልያስ በአራት ኪሎ”በ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት
ከ አዲስ ጉዳይ መጽሔት

ተዋናይት ጀማነሽ ሰለሞን የካቲት 25 ቀን 2005 ዓ.ም ለአዲስ ጉዳይ መጽሔትና ለሌሎች ሚዲያዎች በበተነችው ጥሪ “የኢትዮጵያ ትንሳኤ ሊያረጋግጥ ኃያል ባለስልጣን ቅዱስ ኤልያስ ከብሔረ ሕያዋን መጥቷል” ብላለች፡፡ ጀማነሽ “ይህንን እጅግ ታላቅ አስፈሪና ጥልቅ ሃይማኖታዊ ምስጥር በተመለከተ ትንታኔና ትምህርት የሚሰጥበት ጉባኤ ከጽዋ ማኅበሬ ጋር በመሆን አዘጋጅቻለሁና በኢግዚቢሽን ማዕከል ተገኝታችሁ ተካፈሉልኝ” በማለት ነው ግብዣውን የላችው፡፡ በግዕዝ በአማርኛ እና በእንግሊዘኛ በተጻፈውና ማኅበረ ሥላሴ ዘደቂቀ ኤልያስ .. ብሎ የሚጀምረው የጽዋ ማኅበሯ አማካኝነት በበተነችው ጥሪዋ “በጉባኤው የኢትዮጵያ ትንሳኤ ይታወጃል” ብላለች፡፡ የተለያዩ አርቲስቶችና ሌሎች ታዋቂ ሰዎች እየተሳተፉበት መሆኑ የሚነገረው በዚህ ጉባኤ ላይ የተለያዩ ወገኖች ጥያቄ በማንሳት ላይ ይገኛሉ፡፡በብዙዎች ዘንድ ይህ እንቅስቃሴ ከዚህ ቀደም ተሐድሶ በሚል ስያሜ እንደተካሄደው ዓይነት በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ጥላ ስር አዲስ ሃይማኖት ፤ አዲስ አስተምህሮ የመመስረት አላማ ያለው ነው የሚል አስተያየት እየተሰነዘረበት ነው፡፡ ለመሆኑ ይህ “ተዋሕዶ” የሚል ስያሜ በመካሄድ ላይ ያለው እንቅስቃሴ ከኦርቶዶክስ እምነት አንጻር ምን ያህል ተቀባይነት አለው? የነብዩ ኤልያስ ወደ ኢትዮጵያ መምጣትስ ምን ያህል ተዓማኒ ነው? የዚህ እንቅስቃሴ መሰረታዊ ባህርያት ምን ምን ናቸው? እነዚህንና ሌሎች ጥያቄዎች እንዲመልስን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የእምነት መሰረቶችና ከኦርቶዶክስ ሃይማኖት ጋር የተያያዙ በርካታ መጽሀፍት ደራሲ የሆነው ዲያቆን ዳንኤል ክብረትን ጋብዘናል፡፡

ዲ/ን ዳንኤል ከላይ ያነሳናቸውን ጥያቄዎች ተንተርሶ በላከልን ጽሁፍ በርካታ ጉዳዮችን ይዳስሳል፡፡ “ነብዩ ኤልያስ ወደ ኢትዮጵያ መጥቷል የሚለው” ጉዳይን በመሰረቱ በመፈተሸ ሃይማኖታዊ ትንታኔ ሰጥቶበታል፡፡
ሰሞኑን በከተማችን አዲስ አበባ “ነብዩ ኤልያስ መጥቷል ፤ የአለም ፍጻሜ ቀርቧል” የሚሉ አካላት ተነስተዋል፡፡ እነሱ እንደሚሉት ነብዩ ኤልያስ መጥቶ አዲስ አበባ ይገኛል፡፡ ቤተመንግሥቱንና ቤተክህነቱን ለማጥራት ተዘጋጅቷል ፡፡ ከሚያጠራቸው የቤተክህነት ጉዳዮችም ሦስቱ ትኩረት አግኝተዋል ይላሉ፡፡ “የመጀመሪያው ኦርቶዶክስ የሚለው ስም ስህተት ነው ፤ ስማችን ተዋህዶ ነው ፤ መለበስ ያለበት ልብስ ነጭ ብቻ ነው ፤ እሱም ቢሆን ጥለቱ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ መሆን መቻል አለበት ፤ አሁን ያሰርነውን ክር በመበጠስ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ክር ማሰር አለብን” የሚል ነው፡፡ በየአጋጣሚው ቤተክህነቱንና ቤተ መንግሥትን በመንቀፍ አሁን የሚታዩትን ችግሮች መሰረት አድርጎ ህዝቡ መጥቷል የተባለው ኤልያስን መከተል እንጂ ወደ ቤተክርስቲያን መሄዱ ጥቅም እንደሌለው እየተነገረ ነው፡፡ የሚከናወኑ ማናቸውም የፖለቲካ እንቅስቃሴዎችም የኤልያስን መምጣት የሚያመላቱ እንጂ ምዕመና ሊሳተፍባቸው የሚገቡ አለመሆናቸው ይነገራል ፡፡ እስኪ እነዚህ ነገሮችን በዝርዝር እንመልከታቸው፡፡
ኤልያስ ማነው?
ኤልያስ ማለት “እግዚአብሔር አምላክ ነው” ማለት ነው፡፡ከክርስቶስ ልደት በፊት በስምንተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አካባቢ ከእስራኤል የተነሳ ነብይ ነው፡፡ኤልያስ የሚታወቀው በሶስት ሃይማኖታዊ ተግባሮች ነው፡፡የመጀመሪያው በእስራኤል ተንሰራፍቶ የነበረውን የባአድ አምልኮ ያጠፋና አምልኮተ እግዚአብሔርን ያጸና መሆኑ ሲሆን ፤ ሁለተኛው ደግሞ ንጉስ አክአብ አሕዛባዊት ኤልዛቤልን አግብቶ ይፈጽም የነበረውን ግፍና ጥፋት ሳይፈራና ሳያፍር ፊት ለፊት የገሰጸና ለእውነት ብቻ የቆመ ነብይ መሆኑ ነው፡፡ በዚህ አቋሙ ምክንያት በሰሜን እስራኤል በሚገኙ ሰንሰለታዊ ተራሮች ፈፋ ለፈፋ ሲንከራተት ኖሯል፡፡ መጀመሪያ ቁራዎች ሲመግቡት ቆይተው ከዚያ በሰራፕታ የምትገኝ አንዲት መበልት አገልግለዋለች፡፡
ይህ ቆራጥነቱና ለአምልኮተ እግዚአብሔር ቋሚ መሆኑ በእግዚአብሔር ዘንድ ባስገኝለት ሞገስ የተነሳ ኤልያስ ከኄኖክ ቀጥሎ ሳይሞት ወደ ብሔረ ሕያዋን በመወሰዱ ይታወቃል፡፡ ዮርዳኖስን ወንዝ ከደቀ መዝሙሩ ከኤልሳዕ ጋር ከተሻገረ በኋላ የእሳት ሰረገላ መጥቶ ኤልያስን ወስዶታል፡፡ ይህ ኤልያስ የሚታወቅበት ሦስኛው ነገር ነው፡፡
ኤልያስ ይመጣል ?
ከ470 እስከ 440 በኢየሩሳሌም ትንቢት የተናገረው ነብዩ ሚልኪያስ “የእግዚአብሔር ቀን ነብዩ ኤልያስን እልክላችኋለሁ” ብሎ ትንቢት ተናግሮ ነበር፡፡ (ሚል 4፤5) ይህንንም በመያዝ አይሁድ በፋሶች ፤ በግሪኮች ፤ በሶሪያውያንና በሮማውያን መከራ በተፈራረቁባቸው 400 ዓመታት ውስጥ ነብዩ ኤልያስን ሲጠባበቁት ነበር፡፡ በየምኩራባቸውም የኤልያስ መንበር የተባለ ከፍ ብሎ የተሰራ ባለ መከዳ ወንበር ያስቀምጡ ነበር፡፡ ከክርስቶስ ልደት 6 ወራት ቀድሞ ተወለደውና ከበረሀ የመጣው መጥምቁ ዮሐንስ በብዙ መልኩ ኤልያስን ይመስለው ስለነበረ የተወሰኑት የአይሁድ ክፍሎችና በኋላም ክርስቲያች ይመጣል የተባለው ነብዩ ኤልያስ እርሱ ነው ብለው ተቀብለውታል፡፡
ዮሐንስ መጥምቅ እንደ ኤልያስ ሁሉ በርኽኛ ባህታዊ ነው፡፡ እንደ ኤልያስ ሁሉ ጸጉር የለበሰ ነው ፤ እንደ ኤልያስ ሁሉ እስራኤል ተስፋ የቆረጠችበት ዘመን የመጣ ነው ፤ እንደ ኤልያስ ሁሉ ሄሮድስን ሳያፍርና ሳይፈራ የገሰጸ ነው ፡፡ በእነዚህ እና በሌሎች ምክንያቶች መጥምቁ ዮሐንስ ኤልያስን ይመስለው ነበር፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ይመጣል የተባለው ኤልያስ መጥምቁ ዮሐንስ መሆኑን መስክሮለታል፡፡(ማቴ 11፤14 17፤10-13 ፤ ሉቃ 1፤17)
ስለ ኤልያስ መምጣት የሚነግረን ሌላው መጽሀፍ የዮሐንስ ራዕይ ነው፡፡ ዮሐንስ ራዕይ በምዕራፍ 11 ላይ ዓለምን የሚያጠፋው ሀሳዊ መሲህ ከመጣ በኋላ ዙፋኑን አደላድሎ የዓለምን ክርስቲያኖች ሲጨርስና ምስክር ሲጠፋ ሁለት ምስክሮች መጥተው 1260 ቀናት ምስክርነት እንደሚሰጡና በመጨረሻም በሐሳዌ መሲህ እንደሚገደሉ ይገልጣል፡፡ ከሁለተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ የተነሱ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን እነዚህን ሁለት ምስክሮች ኄኖክና ኤልያስ መሆናቸውን ተርጉመዋል፡፡
ሐሳዊ መሲሕ ሲነሳና ሁሉንም እንደ ሰም አቅልጦ እንደ ገል ቀጥቅጦ ሲያጠፋ ፤ ለእውነት የሚመሰክርም ሲጠፋ ፤ ምዕመናንም በሚደርሰው መከራ ምክንያት የሚከተሉት የእምነት መንገድ “ስህተት ይሆን…” ብለው ሲጠራጠሩ እነዚህ ሁለቱ ሳይሞቱ ወደ ብሔረ ሕያዋን ያረጉ ነብያት መጥተው እውነትን በመመስከርና የሐሳዌ መሲሕን ነገር በማጋለጥ ምስክርነታቸውን በደም እንደሚያጸኑ የሊቃውንቱ ትርጓሜ ያብራራል፡፡
ዮሐንስ አፈወርቅ ፤ አቡሊዲስ ዘሮምና ቪክቶሪያንስ እንደሚገልጡት ኤልያስና ኄኖክ በኢየሩሳሌም ያስተምራሉ ፤ በኢየሩሳሌም ተዓምራት ያደርጋሉ ፤ በኢየሩሳሌም ይገደላሉ ፤ በኢየሩሳሌም ይነሳሉ ፤ በኢየሩሳሌም ያርጋሉ ፡፡ ይህም ለጌታችን መምጣት የመጨረሻው ምልክት ነው፡፡ ከኤልያስና ኄኖክ መምጣት በኋላ የሚጠበቀው የክርስቶስ ለፍርድ መምጣት ነው፡፡
ነብዩ ኤልያስ በአራት ኪሎ
በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ ውስጥ ነብዩ ኤልያስ መጥቷል ይባላል፡፡ የሚኖረው አራት ኪሎ ነው፡፡ አንዳንድ ታዋቂ የሆኑ ሰዎች በተለይም አርቲስቶች ተከታዮች ሆነናል ይላሉ፡፡ ይህንን ሁኔታ ከቅዱሳት መጻህፍትና ከሊቃውንት ትምህርት ጋር ስናነጻጽረው ትክክል ሆኖ አናገኝውም፡፡
መጀመሪያ ነገር ኤልያስ ብቻውን አይመጣም፡፡ በነብዩ ሚልኪያስ ለብቻው እንደሚመጣ የተነገረለት ኤልያስ መጥምቁ ዮሐንስ መሆኑን ራሱ ጌታችን ኢየሱስ ስለ መሰከረ ሌላ ምስክር ማምጣት አያስፈልግም፡፡ በሌላ በኩልም አሁን መጥቷል ተባለው በመጨረሻው ዘመን የሚመጣው ኤልያስ ከሆነ ደግሞ እንደ ሊቃውንቱ ትምህርት ብቻውን አይመጣም ፤ አብሮት ኄኖክም ይመጣል፡፡ አሁን ግን ኤልያስ ከኄኖክ ተነጥሎ ነው መጣ የተባለው፡፡
ይህ ብቻ አይደለም፡፡ ነብዩ ኤልያስ የሚመጣበት ጊዜ በራዕይ ዮሐንስ ላይ ምዕራፍ 11 ተገልጧል፡፡ አስቀድሞ ሐሳዊ መሲህ ይመጣል፡፡ ዙፋኑንም በተቀደሰችው ከተማ በኢየሩሳሌም ይዘረጋል፡፡ ምዕመናንም(በተለይም የስድስት ስድሳ ስድስትን አምልኮ ያልተቀበሉትን) በግፍ ይገድላቸዋል፡፡ በዚህም ጊዜ እውነት ትቀጥንና ምስክር ታጣለች ፤ ኤልያስና ኄኖክ የሚመጡትም እውነትን በአደባባይ ለመመስከር ነው፡
ይህ ከሆነና በአዲስ አበባ እየተባለ እንዳለው ኤልያስ ከመጣ ሐሳዊ መሲህ መጥቷል ማለት ነው፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን ምዕመናን በግፍ ተገድለዋል ፤ በዓለምም ላይ አማኞች በአብዛኛው አልቀዋል ማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ ሲፈጸም አላየነውም፡፡ በኢየሩሳሌምም ሐሳዊ መሲህ ገና አልነገሰም፡፡
ሌላም ሦስተኛ ነገር መነሳት አለበት፡፡ ሐሳዊ መሲሕ የሚነግሠው ፤ ኄኖክና ኤልያስም የሚገለጡት ‹በተቀደሰችው ከተማ” በኢየሩሳሌም ነው፡፡ የሚሠውትም እዚያ መሆኑን “እርስዋም በመንፈሳዊ ምሳሌ ሶዶምና ግብጽ የተባለችው ደግሞ ጌታችን የተሰቀለባት ናት› ብሎ ኢየሩሳሌም መሆኗን ነግሮናል(ራዕይ 11፤8) ፡፡ አሁን ግን ኤልያስ ተገለጠ የተባለው ያለው አዲስ አበባ አራት ኪሎ ላይ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ተልዕኮውም ከመጽሀፍት ጋር የሚጣረስ ነው፡፡ ጌታ የተሰቀለው አራት ኪሎ ነው ካላልን በቀር፡፡
ራዕይ ዮሐንስ እንደሚነግረን ኄኖክና ኤልያስ ምስክርነት የሚሰጡት ለ1260 ቀናት ወይም ለ42 ወራት ወይም ለሦስት ዓመት ከስድስት ወራት ነው፡፡ አሁን ግን አዲስ አበባ መጣ የተባለው ኤልያስ መጣ ከተባለ አራት ዓመት ሊያልፈው ነው፡፡
ምጽአትና መሲሕን መናፈቅ
በዓለም ሆነ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የምጽአትን ቀን የመናፈቅና የምጽአትን ምልክቶች ደርሰዋል ብሎ የመጨነቅ አዝማሚያ የሚከሰትባቸው ምክንያቶች አሉ፡፡ እነዚህም ኢኮኖሚያዊ ፤ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ቀውሶች ሲከሰቱና ሕዝብ ተስፋ ሲቆርጥ ነው፡፡
እስራኤራዊያን ከፋርሶችና ከግሪኮች ወረራ በኋላ ሀገራቸው ስትመሰቃቀል ፤ መንፈሳዊነት ሲጎድልና መንግሥታቸው ፈርሶ ተስፋ ወደ መቁረጥ ሲመጡ “መሲሕ እየመጣ ነው ፤ ኤልያስ እየደረሰ ነው” የሚል አስተምህሮ ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በ2ኛው መቶ ክፍተ ዘመን ጀምረው ነበር፡፡ በዚህ የተነሳ አንዳንድ ሰዎች ይመጣል የተባለው መሲሕና ኤልያስ እኛ ነን እያሉ አጋጣሚውን ሊጠቀሙበት ሞክረው ነበር፡፡ ከእነዚህ መካከል ከክርስቶስ ልደት በፊት በ2ኛውና አንደኛው መ.ክ.ዘ ላይ የተነሱ ቴዎዳስና ይሁዳ ይጠቀሳሉ፡፡ ቴዎዳስ አራት መቶ ሰዎችን አስከትሎ ነበር ፡፡ በኋላ ግን ሐሰተኛ መሆኑ ሲታወቅ ሕዝቡ ተወው ፡፡ ይሁዳም ሕዝቡን አስነስቶ እስከ ማሸፈት ደርሶ ነበር፡፡ መጨረሻው ግን አላማረም(የሐዋ 5፤37-39)
በቅርብ ጊዜ በኡጋንዳ ኢኮኖሚ ሰደቅና የእርስ በርስ ጦርነት ሲባባስ ይህም የሕዝቡ ማኅበራዊ ሕይወት ሲያቃውሰው “እኔ ክርስቶስ ነኝ” የሚል ሰው ተነስቶ በአንድ አዳራሽ ውስጥ የነበሩ ተከታዮች መንግሥተ ሰማያት ለመግባት ሲሉ በእሳት ተቃጥለው እንዲያልቁ አድርጓቸው ነበር፡፡ በአሜሪካ የደረሰው ኢኮኖሚ ድቀት ካስከተላቸው መዘዞች አንዱ በየአካባቢ “እኔ መሲሕ ነኝ” የሚሉ እና ሕዝቡ ችግሩን ከማሸነፍ ይልቅ ችግሩን እንዲረሳው የሚያደርጉ ሰዎች መከሰታቸው ነው፡፡ በ2012 የተደረሰ አንድ ጥናት ባለፉት 3 ዓመታት በአሜሪካ ውስጥ 132 ሰዎች መሲሕ ነን ብለው ተነስተው ወደ 4.5 ሚሊየን የሚደርስ ሕዝብ አስከትለዋል፡፡
በሀገራችን ታሪክ በ15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በተከሰተው የግራኝ ጦርነት በኋላ ሕዝቡ መንፈሳዊ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተስፋ መቁረጥ ደረጃ ደርሶ ነበር፡፡ አብያተ ክርስያናቱ ተቃጠሉ ፤ ኢኮኖሚው ወደመ ፤ መንግስት ተዳከመ ፤ ትዳና መስተጋብር የመሰሉ ማኅበራዊ ተቋማት ፈረሱ፡፡ ብዙ ሰዎች ሞቱ ፡፡ ይህ ሕዝቡ ላይ ባስከተለው ተስፋ መቁረጥ የተነሳ ከዚህ መከራ እና ስቃይ የሚያወጣውን አንዳች ሰማያዊ ኃይል ይጠብቅ ነበር፡፡
በሀገራችን ላይ የበልጥ ራዕይ ዮሐንስ የታወቀውና በገልባጮች እጅ በብዛት የተገለበጠው በዚህ ጊዜ ነው፡፡ በሚሰሩት አብያተ ክርስቲያናትም የሐሳዊ መሲህ ፤ የኤልያና የኄኖክ ፤ የአዲሲቱ ሰማይና ምድር ስዕሎች በብዛት ተሳሉ፡፡
ከግራኝ ጦርነት በኋላ በአጼ ሰርጸ ድንግል ወራሾች መካከል በተፈጠረው የርስ በርስ ውጊያ ሀገሪቱ ስትታመስና ሕዝቡ በተደጋጋሚ ጦርነትና የሕዝብ ፍልሰት ሲታወክ እኔ ክርስቶስ ነኝ ፤ ሕዝቡንም ከችግር ላወጣውና መንግሥተ ሰማያት ላወርሰው መጥቻለሁ የሚል ሐሳዊ መሲሕ በአማራ ሳይንት አካባቢ ተነስቶ ነበር ፡፡ አስራ ሁለት ሐዋርያት ፤ 72 አርእድትንና 36 ቅዱሳት አንስትንም መርጦ ነበር፡፡ ብዙውም ሕዝብ በተስፋ መቁረጥ ላይ ስለነበረ ተከትሎት ነበር፡፡ በኋላ ግን በሞት መቀጣቱን አቡነ ጎርጎርዮስ በኢትዮጰያ ቤተክርስቲያን ታሪክ መጽሐፋቸው ጠቅሰውታል፡፡
በቅርቡ በሀገራችን ታሪክ ዐጼ ምኒሊክ አርፈው ሞታቸው በተደበቀበት ጊዜ ፤ በታህሳስ ግርግር ጊዜ ፤ በአብዮቱ ዋዜማና ማግስት ፤ እንዲሁም ኢሕአዴግ አዲስ አበባ በገባበት ጊዜ አያሌ “ባሕታውያን” ተነስተው ነበር፡፡ ይህ ነገር መጣ ፤ ብላቴን ጌታ ኅሩይ ስለ ንግሥት ዘውዲቱ ዘመን በጻፉት የትዝታ መጽሀፋቸውም ይህንን ገልጠውታል፡ ይህም ያም ነገር ታየ ፤ ተገለጠ የሚለው ብሂልም ነባርና የሀገር አለመረጋጋትና በኑሮ ተስፋ መቁረጥ ተገን አድርገው የሚመጡ ናቸው፡፡
የኤልያሳውያን ሁለት አስተምህሮዎች
አሁን በዘመናችን የተከሰቱ ኤልያሳውያን ሁለት ነገሮች ላይ አተኩረው እየሰሩ ነው፡፡ የመጀመሪያው “ኦርቶዶክስ” ትክክለኛ ስም አይደለም የሚለው ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ሰንደቅ አላማን ከጽድቅና ከኩነኔ ጋር ማያያዛቸው ነው፡፡
ኦርቶዶክስ የሚለው ቃል የግሪክ ሲሆን “ኦርቶ” ርቱዕ “ዶክስ” ደግሞ እምነት ፤ መንገድ ፤ ጠባይ ፤ ባህል ማለት ነው፡፡ ይህንን ስም የክርስቲያን አብያ ክርስያናት መጠቀም የጀመሩት በ325 ዓ.ም በተደረገው ጉባኤ በኋላ ነው፡፡ ከጉባኤ ኬልቄዶን የ451 ዓ.ም ጉባኤ በኋላ ደግሞ የምዕራብ አብያተክርስቲያናት ካቶሊክ ሲባሉ ምስራቆቹ “ኦርቶዶክስ” የሚለውን ስም ይዘው ቀሩ ፡፡ በምስራቆቹ መካከል የጉባኤ ኬልቄዶንን ውሳኔ በመቀበልና ባለመቀበል መካከል ልዩነት ስላለ የግሪክ መሰል አብያተክርስቲያናት የምስራቅ ኦርቶዶክስ ሲባሉ ፤ አርመን ፤ ግብጽ ፤ ሕንድ ፤ ሶሪያና ኢትዮጵያ ደግሞ “ኦሪየንታል ኦርቶዶክስ” ተባሉ፡፡
ኦርቶዶክስ ፤ ኦርዶክሳዊ የሚለው ስም በሀገራችን ቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ በሁለት መንገድ ተገልጠዋል፡፡ በአንድ በኩል ጥሬ ቃሉ እንዳለ የተቀመጠ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ወደ ግዕዙ ተተርጉሞ “ርቱዕ ሃይማኖት” እየተባለ ተቀምጧል፡፡ ፍትሐ ነገስት ‹ይኩን ምእመነ ኦርቶዶክሳዌ ይላል› (42፤2) ያዕቆብ ዘእልበረዲም ‹ሃይማኖት ኦርዶክሳዊት› ሲል እምነቱን ይገልጣል፡፡ መጽሐፈ ቄርሎስም ‹ሃይማኖተ ርቱዕ› እያለ ተርጉሞ ይገልጠዋል፡፡
‹ተዋሕዶ› የሚለው ቃል ነጥሮ የወጣው በጉባኤ ኤፌሶን በ431 ዓ.ም ነው፡፡ በጉባኤው ንስጥሮስን ባሕል ለማየት የተሰበሰቡ አበው በእስክንድርያ ቄርሎስ የተሰጠውን ትምህርት በመቀበል ሁለት ባሕርይ የሚለውን አውግዘው መለኮት ከስጋ ተዋህዶ ሥግው ቃል ሆነ የሚለው ርቱዕ እምነት መሆኑን መሰከሩ፡፡ ይህ ቃል የእምነት ዶክትሪን መገለጫ ሆኖ ነው የኖረው ፡፡ በኬልቄዶን ጉባኤ በኋላም ይህ ስያሜ የኦርቶዶክሶቹ ዋና መጠሪያ እየሆነ መጣ፡፡ በኢትዮጵያ ጥንታዊ መጻሕፍት ላይ ተዋህዶ እምነት ሆኖ እንጂ የቤተክርስቲያ መጠሪያ ሆኖ አናገኝውም ‹ኦርቶዶክሳዊ› የሚለው ቃል የምናገኝውን ያህል ‹ተዋህዶ› የሚል መገለጫ አናገኝም ተዋሕዶ የሚለው ቃል በነገረ ሥጋዌ ትምህርት ላይ በሀገር ውስጥ የተነሳ የተለየ አስተያየት ስላልነበረ መጠሪያነቱ አልጎላም፡፡
በ17ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከአውሮፓ በመጡ ካቶሊካውያን ምክንያት የተፈጠረውን የእምነት ክፍፍል ተከትሎ ይህ የእምት መጠሪያ የአማያንና የወገን መጠሪያ እየሆነ መጣ፡፡ በ17ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ቅባትና ጸጋ የሚባሉ ባሕሎች መጥተው ነበር፡፡ እነዚህን ባሕሎች የሚቃወሙትና ኢየሱስ ክርስስ መለኮት ከስጋ በተዋሕዶ ሥግው ቃል እንጂ እንደ ነገስታትና ነቢያት በመቀባት አይደለም ያሉት ደግሞ መጠሪያቸው ከእምነታቸው ተወስዶ “ተዋሕዶዎች” ተባሉ፡፡ ከቦሩ ሜዳ ጉባኤ በኋላም የቤተክርስቲያኒቱ ሕጋዊ ስም ‹‹ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ›› የሚለው ጎላ፡፡
ኦርቶዶክስ የሚለው ስም ቤተክርስቲያኒቱ በዓለም የምትታወቅበት የወገን ስሟ ነው፡፡ ሌሎችም ‹የግብጽ ኦርቶዶክስ› ፤ ‹ የሕንድ ኦርቶዶክስ› ብለው ይጠሩ እና ከአካባቢያቸው ራሳቸውን ለመለየት ደግሞ ‹የግብጽ ኮፕት ኦርቶዶክስ› ፤ ‹የሶርያ ያዕቆባዊት ኦርቶዶክስ› እያሉ ይጠራሉ፡፡ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንም ‹ኦርዶክስ ተዋሕዶ› ትባላለች ፡፡
አንዳንድ ሰዎች በዘመናውያን መዛግብት ቃላት ስለ ‹ኦርቶዶክስ› የተሰጡ ፍቺዎችን ይዘው ይሞግታሉ፡፡ ኦርቶዶክስን ‹ከአክራሪነትና ከለውጥ አለመቀበል› ጋር እያዛመዱ ይፈቱታል፡፡ በዚህ ምክንያት ኦርቶዶክስ የሚለው ቃል ለኮንሰርቫቲቭ ፓርቲዎችና ለአይሁድ ሲሰጡት ይታያሉ፡፡ ይህ ግን ኦርቶዶክስ የሚለው ስም ከመነጨበት ጠባይ በእጅጉ የራቀ ነው፡፡
አሁን ወደ ሁለተኛ ነጥብ እንመለስና ሰንደቅ አላማን እንመልከት፡፡ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ የኢትዮጵያውያን መለያ ናት፡፡ ለዚች ሰንደቅ አላማ ብዙዎች ውድ ሕይወታቸውን ከፍለዋል፡፡ ከእነዚህ ውድ ሕይወታቸውን ከከፈሉ መካከልም የቤተክርስቲያኒቱ አባቶችና ልጆች ይገኙበታል፡፡ ቤተክርስቲያኒቱ ታሪክን ከማቆየት ፤ ባሕልን ከማሻገርና ኢትዮጵያዊነትን ከማስረጽ ሚናዋ አንጻር ሰንደቅ አላማንም በማስከበርና ለትውልድ በማስተላለፍ የበኩሏን ድርሻ ተወጥታለች፡፡
የኢትዮጵያ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ አላማ ከሀገራዊ እሴትነቱ ፤ መስዕዋትነትና ነጻነት ከማንጸባረቁም ፤ ለኢትዮጵያውያን ከደማቸው ጋር የተዋህዶ ልዩ ምልክት ከመሆን አልፎ ግን ጽድቅና ኩነኔ ውስጥ የሚገባ ፤ እርሱን ያልተቀበለ እና ያላደረገ ሰማያዊ ዋጋ የሚቀርበት ፤ ከእርሱ ውጪ ቀለም ያለው ነገር የለበሰና ማህተብ ያሰረ ሃጥያት እንደሰራ ተቆጥሮ ንስሃ የሚገባበት ግን አይደለም፡፡ ከኢትዮጵያ ውጪ ያለ ዜጋ የቤተክርስቲያኒቱ አባል ለመሆን የቤተክርስቲያቱን ዶግማ እና ቀኖና መቀበልን እንጂ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራን መቀበል ግዴታው አይደለም፡፡ በኡጋንዳ ባንዲራ ፤ በአሜሪካ ባንዲራ ፤ በሶማሊያ ባንዲራ አሸብርቆም ቢሆን የኦርዶክስ ተዋሕዶ ልጅ መሆን ይችላል፡፡ አስከ አሁን በቀኖና በሚደነገጉ መጻህፍቶች ውስጥ ሰንደቅ አላማን የተመለከተ ቀኖና የለንም፡፡
በመሆኑም ሰንደቅ አላማችን ከኢትዮጵያዊነታችን ጋር እንጂ ከኦርቶዶክስ እምነታችን ጋር የታሪክ እንጂ የድኅነት ተዛምዶ የለውም፡፡
እንደዚህ አይነት አመለካከቶች የሚያይሉት እንዲሁ አይደለም፡፡ በሕዝቡ ዘንድ ኢትዮጵያዊ ስሜት ደብዝዟል ፤ ለሰንደቅ አላማና ለሀገራ እሴቶች የሚሰጠው ዋጋ ቀንሷል ተብሎ ሲታሰብ ሰንደቅ አላማን የመሰሉ ሀገራዊ እሴቶች ጉልበት ያገኙ ዘንድ ተጨማሪ ሃይማኖታዊ ኃይል ይሰጣቸዋል፡፡ ቤተክርስቲያቱ የሰንደቅ አላማን ክብርና ትርጉም ማስተማርዋ እና በትውልድ ውስጥ ማስረጿ ባልከፋ ፡፡ አስተምህሮ ግን ከሀገራዊ ግዴታ የሚመጣ እንጂ ከሃይማኖታዊ ግዴታ የሚመጣ መሆን የለበትም፡፡ ከሕዝብ እሴቶች እንደ አንዱ ሆኖ እንጂ ከጽድቅና ኩነኔ ጋር መሆን ለበትም፡፡
ምን ይደረግ ?
የሃይማኖት ትምህርት በሚገባ መሰጠት ሲያቆምና ሰዎችም በተደላደለው እምነት መንገድ ላይ በእውቀትና በእምነት እየተመሩ መጓዝ ሳይችሉ ሲቀሩ ‹ባለ ተስፋዎች ይሆናሉ› ቅዱስ ጳውሎስ ለኤፌሶን ሰዎች በላከው መልዕክቱ መጀመሪያ ላይ ‹በኤፌሶን ላሉት ቅዱሳን ፤ በክርስቶስ ኢየሱስ ባሉት ምዕመናን› በማለት የገለጠው አባባል ታላቅ ነገር አለው፡፡ ምእመናኑ በሁለት ዓለም መኖራቸውን እንዳይረሱ ለማድረግ ነው፡፡ ‹በክርስቶስና በኤፌሶን› ክርስቲያችም ምድራዊነታቸውንም ሰማያዊነታቸውንም መርሳት የለባቸውም፡፡ አንዳንድ ጊዜ ግን ምድራዊ ጎዳና ሲያቅተንና ፈተና ሲበዛበት ፤ የኢኮኖሚ የፖለቲካ ሁኔታ አልቃና ሲል ፤ የምናየው የምንሰማው ተስፋ ሲያሳጣን ፤ ምድር ላይ መሆናችንን ፈጽመን ረስተን ኅሊናችን ወደሚፈጥረው ልዩ አለም እንገባለን፡፡ ያንንም እጅግ ከመመኝታችን የተነሳ የደረስንበት ይመስለናል፡፡
በዚህ ጊዜ የሚሰጡ ትምህርቶች ለሰዎች ቀላል የሆኑ ፤ ንባብና ትምህርትን የማይጠይቁ ፤ በቀላሉ የሚተገበሩ ፤ የሚነኩና የሚዳሰሱ ይሆናሉ፡፡ ቡና መጠጣት አለመጠጣት ፤ አረንጓዴ ቢጫ ክር ማሰር አለማሰር ፤ በባዶ እግር መሄድ አለመሄድ ፤ ጸጉርን ማስረዘም አለማስረዘም ፤ መቁጠሪያ አለስርዓቱ ማሰር አለማሰር ፤ ከመምህራን ቃል ይልቅ የሰይጣንን ቃል መቀበልና ማመን እየሰለጡ ይመጣሉ፡፡
ለዚህ ትልቁ መፍትሔው የእምነት ተቋማት የራሳቸውን ሥራ (ወንጌል ማስተማር) ትተው በሰዎች ስራ ውስጥ መግባታቸው ነው፡፡ ስለዚህ ተቋማቱ መጀመሪያ ራሳቸውን ወደ ተልዕኳው መልሰው ፤ የማይጨበጥ ተስፋ የሚዋልለውን ሕዝብንም ወደ ትክክለኛ ኑሮ እና ተስፋ መመለስ አለባቸው፡፡ እዚህ ኤልያስ ነኝ ፤ እዚያ ድንግል ማርያም ነኝ ፤ እዚያ አቡዬ ነኝ የሚሉ በተነሱ ቁጥር ሕዝቡ ስራና ትዳር ፈትቶ ተንከራቶ አይዘልቀውም፡፡ ይህ አዲስ እንቅስቃሴ ለምእመናኑ የተለየ ፋይዳ ይዞ አልመጣም፡፡


የኢትዮጵያውያን ጩኸት ከመካከለኛው ምስራቅ---በሳኡዲ የመን ድንበር የታሰሩ እስረኞች ለመልቀቅ ገንዘብ እየተጠየቁ ነው::

 

በሳኡድ ፖሊሶችዛፍ ላይ  የታሰረው ኢትዮጵያዊ 
በሺዎች የሚቆጠሩ በሳኡዲ የመን እስር ቤት ያሉ ስደተኞች አስፈላጊውን ክፍያ እየከፈሉ እንደሚለቀቁ የየመን የደህንነት ባለስልጣን መሃመድ ነጃድ አስታወቁ::

ሁነታዎችን አደገኛ ያደረገው ባለፈው የካቲት ወር ላይ ኢትዮጵያውያን ለሃገራቸው አደገኛ እና ህገወጥ አስጊ መሆናቸውን የሳኡዲ ሚዲያዎች (  http://www.youtube.com/watch?v=DSS4bAVP-fA  )الكنبه إذا عزمك أثيوبي تروح له ؟ / Couch if your determination Ethiopian his imagination?/ የተላለፈውን ዘገባ ተከትሎ ነው:: ይህን ዘገባ የሰሙ የሳኡዲ እና የየመን ዜጎች በድንበሩ አከባቢ እና በሳኡዲ አረቢያ ውስጥ ህገወጥ ናቸው ያሉዋቸውን ሰዎች እየያዙ ያስረክባሉ ቢባልም እውነታው ግን ከኢትዮጵያውያን ገንዘብ እንዲያመጡ ያስገድዷቸዋል::

በሳ ኡዲ  አሰሪዎቹ የተቃጠለው ኢትዮጵያዊ 
በህገወጥ ደላሎች የተደፈሩ ሴቶች 
በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የኢኮኖሚ ድቀት እና የፖለቲካ አምባገነንነት ሸሽተው ወደየሰዉ አገር የሚሰደዱት ወገኖች
በወጣትነታቸው ሰርተው ራሳቸውን እና ቤተስቦቻቸውን ለመርዳት እንኳን አልታደሉም::ከተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ድርጅት( http://www.un.org/apps/news/story.asp?NewsID=43928&Cr=yemen&Cr1=refugee#.UUiOcDcj8wq ) ባወጣው ዘገባ 84.000 ኢትዮጵያውያን የኤደንን ሰርጥ አቋርጠው በአስፈሪው የውሃ ማዕበል አልፈው ወደ መካከለኛው ምስራቅ ያቋርጣሉ::

አብዛኛው አስቸጋሪውን የባህር ጉዞ የጨረሰው በቀጥታ ወደ የመን ሳኡዲ ድንበር ይሄድ እና በህገወጥ ደላሎች እና ድንበር አሻጋሪዎች ወደ ሳኡዲ ለመግባት ሲሞክር በወሮበሎች በዘራፊዎች በአጭበርባሪዎች ገንዘቡን ይበላል ተይዞ ለፖሊስ ያስረክቡታል ፖሊስም ድጋሚ ገንዘቡን ይነጥቀዋል ::
በቅርብ ጊዜ የወጣ የUNHCR ሪፖርት ( http://www.middle-east-online.com/english/?id=51172 ) እንደሚያመለክተው የየመን እና የሱዲ የድንበር ላይ ባለስልጣናት ስልጣናቸውን መከታ በማድረግ ኢትዮጵያውያንን አስገድደው ይደፍራሉ:ገንዘባቸውን በጉልበት ይነጥቃሉ ይላል::እንዲሁም ከቤተሰቦቻቸው ገንዘብ ይጠይቃሉ ያሌለውን ገድለው አካሉን በጥቁር ገበያ ይሸጡታል:: http://www.youtube.com/watch?v=2zTA4U0W3DI&feature=player_embedded

በሳዑድ ፖሊሶች የተያዙ ኢትዮጵያውያን በመኪና ታስረው በየተራ ሲጎተቱ 
በየመን አደን ባህር ላይ የተገኘች ኢትዮጵያዊ ከነልጇ


ኢትዮጵያውያን ለማህበረሰባችን ትልቅ አደጋ ናቸው::         Suddenly the Ethiopians have become the greatest danger to our society!

Suddenly it is the Ethiopians!

LOCAL VIEWPOINT

Last updated: Wednesday, March 06, 2013 11:12 AM

 

Khalaf Al-Harbi
Okaz

 

 

Suddenly the Ethiopians have become the greatest danger to our society!

The issue of the illegal foreigners has been narrowed down to a single nationality. Nobody asked how the Ethiopians were able to enter our country in such large numbers. Nobody questioned how they were able to stay all these long years in the bottom of the valleys and the backstreets of major towns and cities without being noticed.

Furthermore, over stayers from various nationalities are seen in broad daylight along intersections of major streets and roads in the main cities without any action to curb this phenomenon.

We are, however, very fond of the following scenario: We become angry all of a sudden and then become quiet and pacified. The conditions have remained the same for many years with no one enlightening us with a radical solution.

If I spend three hours in the archives of any newspaper, I will provide you with tens of features, investigative reports, articles and complaints from readers against the increasing phenomenon of illegal workers in various parts of the Kingdom, particularly the southern and western regions.

If I ride a taxi I will come out to you with stories about the fears of taxi drivers to enter certain underdeveloped districts, which are under total control of the illegal foreigners with nobody to deter them. It is obvious that we like to surprise ourselves with unexpected things.

I remember a letter from one of my readers a few years ago suggesting we build a high wall along our southern borders to “preserve the purity of our race”. Of course, I did not like this abominable racist statement but I do not deny that the issue was on my mind for quite a long time because it signaled that we would soon confront a problem that we would not be able to solve.

During the past few years I have been reading news about African infiltrators burning down forests in the south either in revenge against the security campaigns or in search of warmth in cold winters. I was waiting in vain for the declaration of mobilization by the authorities to curb this phenomenon but nothing happened.

I am confident that the “Ethiopian phobia” will diminish in a week or two because all the concerned parties will ignore the problem as if it has never existed. I am, however, still hopeful that a solution to the problem of illegal workers will be found. The first step toward a solution is not to link the phenomenon to a certain nationality because many of the overstayers are from Asian and Arab countries as well.

We should also realize that tightening the restrictions on citizens who are looking for regular workers will only help flourish the market for the illegal workers.

Modern methods should be used to curb infiltrations through our borders. Any prosperous country bordering less affluent countries must be prepared to confront this phenomenon otherwise it will find infiltrators in the very heart of its capital city.

Ethiopia forcing thousands off land to make room for Saudi and Indian investors

Ethiopia is forcing tens of thousands of its poorest people off fertile land earmarked for Saudi Arabian and Indian investors and into villages lacking schools, clinics or clean water, a new report has claimed.

Ethiopia forcing thousands off land to make room for Saudi and Indian investors
Ethiopia is among a clutch of African countries aggressively marketing their fertile land to overseas investors, mostly from the Gulf, South Asia and the Far East, to grow their own crops for export back to domestic markets Photo: MICHAEL TSEGAYE/BLOOMBERG

Already, 20,000 families have moved from areas they have roamed for centuries in a "villagisation" programme that researchers claim international donors including Britain have inadvertently helped fund.

At the same time, Indian, Saudi and Ethiopian companies have moved in to take over more than one million acres of land to grow cash crops in the affected region, Gambella.

A further six million acres of Ethiopia – an area close to the size of Belgium – have already been leased to foreign firms and there are plans to expand this by another five million acres.

Ethiopia's government says that no one has been forced to move and that the villagisation scheme – which will eventually reach 1.5 million Ethiopians – is designed to give people previously scattered across vast areas better access to "social and economic services".

But in interviews with more than 100 people from Gambella, in Ethiopia's west, Human Rights Watch was repeatedly told that they were moved under duress.

"Our research found the process to be far from voluntary," the rights group said in a report published on Tuesday.

"[It] has been accompanied by widespread human rights violations, including forced displacement, arbitrary arrest and detention, beatings, rape, and other sexual violence.

"Residents [said] that any refusal or inquiries were met with beatings, arrests, or intimidation from the army."

The programme bears echoes of the Soviet-inspired mass resettlements of Ethiopia's rural people into work camps under the Marxist Derg government of Mengistu Haile Mariam in the 1970s and 1980s.

Tribes that traditionally moved with their animals have been settled and ordered to plant crops, the report says.

Others that roamed wide areas shifting their cultivation from season to season have been given tiny new plots to raise harvests to feed their families.

One elder told researchers: "We want you to be clear that the government brought us here ... to die. They brought us no food, they gave away our land to the foreigners so we can't even move back.

"On all sides the land is given away, so we will die here in one place."

In several cases, Human Rights Watch said, people had been moved to existing villages where services including health care, education, food aid and clean water was funded through programmes paid for by international aid.

"Through their ongoing budgetary support to regional and local governments, [Ethiopia's foreign donors] are, in part, paying for the construction of schools, health clinics, roads, and water facilities in the new villages," Human Rights Watch said.

"They are also funding agricultural programs directed towards resettled populations and the salaries of the local government officials who are implementing the policy.

"It is almost impossible for donor funds not to be contributing to basic services in new villages."

Andrew Mitchell, the International Development Secretary, said last night that he would be "taking a close look" at the report's findings and would raise concerns "at the highest level".

Ethiopia is given more bilateral British aid than any other country, and is scheduled to receive £1.3 billion between 2010 and 2015.

"The British Government's development assistance in Ethiopia does not encourage or support 'villagisation' and we share HRW's concerns that promises made to communities are not being fulfilled," Mr Mitchell said.

Ethiopia is among a clutch of African countries aggressively marketing their fertile land to overseas investors, mostly from the Gulf, South Asia and the Far East, to grow their own crops for export back to domestic markets.

Bereket Simon, Ethiopia's director of government communications, said that Gambella, and other areas marked for commercial leasing, were "underutilised" or "uninhabited".

"Ethiopia is a country endowed with natural resources and abundant land which is not inhabited by any people," he said.

"We are inviting investors to come to Ethiopia, but we make absolutely sure that they invest for the development of the country."

He dismissed the Human Rights Watch report as a "deliberate and blatant smear campaign" against his country by the New York-based organisation.

"I can assure you that 20,000 families have been relocated voluntarily in the last two years, it was not forced at all, and all the infrastructures are in place for them," he said.

"In fact, we planned to move 15,000 families, but another 5,000 came of their own accord because of the better infrastructure."

الحكومة الإثيوبية سياسة المستمرة

بدر إثيوبيا،
واشنطن DC

قواعد إملاء التضليل أن يتم تجنب القضايا الحقيقية والقضايا ويسلط الضوء على الجانب. القواعد والأنظمة والسياسة العامة للحكومة areEthiopian المستمرة الذم حين مريحة، وحافظت عندما تابعا. ويصور الدراما ويقتصر الحقيقة. ومن المتوقع أن يتم مخيفة والصور ملفقة المعلومات. يتم تحديد آلة الدعاية ويتم استخراج بيانات مستخلصة بالإكراه. وتخويف الجمهور ويبدأ الترويج للخوف. الصورة كاملة عندما خطة الحكومة هي ملموسة.
صورة
الحكومة الإثيوبية المستمرة والمسيئة إضراب تكتيكات المفترسة الخوف في قلوب المواطنين من خلال تلويث باستمرار ومهينة الحركة الجماهيرية السلمية من المسلمين الاثيوبية ومهاجمة بنهم لجنة التحكيم أعضاء المسجونين. تم الكشف عن كامل الجزء الأول من هذه الحلقة الدرامية أمس عندما الفيديو مشوهة بشكل فاضح يسمى "Jihadawi Harekat"، والتي تعني حرفيا "الحركة الجهادية"، بثت على التلفزيون الوطني في إثيوبيا.

Image

الإنتاج الحكومة لهذه الدراما الفيديو وكتابتها الهواة يظهر بوضوح موقف متغطرس والأنا التي لا يمكن اختراقها. وكاميرا الفيديو تشريح وتقطيع نسيج من الصور التقطه من مختلف البلدان والمنسوجة معا للبحث كله واحدة واحدة. لكن الحركة مستمرة من العارضة في إجراء الاستجواب يدعم الاستنتاج بأن قانون الحكومة للنزع احشاء شهادة أحبطت خطتهم الكبرى. كان واضحا أن انتزعت قسرا الكلام الشفوي للمسلمين المسجونين ضارا تحت الإكراه للاستهلاك العام وتقرير إدانة. وعدم الاتساق في البيانات اللفظية التي قدموها وبعض علامات مرئية على سوء المعاملة على جثث السجناء الذين ربما يكونون قد تعرضوا للأساليب الاستجواب القاسية وغير القضائية لانتاج معلومات كاذبة للمواصفات الدقيق للالمحققين ورؤسائهم. طبيعة مشكوك فيها للغاية من اعترافاتهم يضفي مصداقية على زيارتهم للغرفة التعذيب. كان هذا حالة كلاسيكية من المعلومات الخاطئة وحملة التضليل. هذا ينطوي على شعار أن الخوف من كل الأقليات ومعظمها في الهستيريا. شريط الفيديو يوضح بجلاء أن الترهيب والتماس تفوقت طريقة عمل الحكومة. للأسف، فإن تداعيات هذه الكارثة على الفيديو أيضا تداعيات طويلة الأمد لإثيوبيا ومواطنيها.

لحسن الحظ، كان شريط الفيديو الذي ملفقة فوزي وفيلم "وثائقي" تجربة فاشلة لأنها أنتجت مجموع تأثير عكس النتيجة التي كان من المتوقع. تم القبض الحكومة الإثيوبية التي تم يدعي علنا ​​لبعض الوقت أنه يمارس سيادة القانون والالتزام بمبادئ الحكم الديمقراطي عارية القدمين ممارسة على العكس تماما من ذلك المبدأ. هذه لحظة فاصلة للدستور، الذي هو حرفيا مجرد حبر على ورق كقطعة متحف جمع مثقفة. الحكومة تعكف على طريقة استبدادية السلطة المطلقة، التي وصلت ذروتها. حيث هناك حمى، وهم وراء الحق.

يوم أمس علنيا لشريط الفيديو الذي تم متنكرا في زي كان "وثائقي" فيلم مصداقيتها عالميا لمخططاتها مع سبق الإصرار والجاهزة. يبدو متجهة المستعرض العامة للالفيديو من قبل الحكومة، التي تسيطر على جميع وسائل الإعلام، لزرع بذور الكراهية والعداء داخل المجتمع مسلم وكذلك لخلق الانقسام داخل سكان أكبر الإثيوبية. كان ذلك الموظف بفعل ما من شيطنة علنا ​​وتحط السجناء قبل محاكمتهم في محكمة قانونية خادعة ومضللة للغاية. هذا التكتيك شيطنة يلي أيضا قواعد التضليل وقمع الحقيقة. هذا الأسلوب يعمل بشكل جيد خاصة مع الصحافة صامتة، وذلك لأن الطريقة الوحيدة التي يمكن أن تتعلم العامة للحقائق هو من خلال الشائعات. الحكومة تزيد من اتهامات ملفقة ضد "سجناء الضمير"، وذلك تلفيق ثم يتغذى عليه في آلة الدعاية لتجنب مناقشة القضايا الحقيقية للقانون والنظام. ولذلك، فرضت حملة تشويه ضد أعضاء هيئة التحكيم وغيرهم من المسلمين أن يقبعون في السجن هو مناف للعقل ومتحيز، وأنها لن ترى ضوء النهار في المحاكم المشتركة للدول حقا ديمقراطية.

للتأكد من ذلك، إذا كان هذا حال الحقيقي للإرهاب داخل إثيوبيا أو في أي مكان آخر لهذه المسألة، وجميع المسلمين بدر ائق الاثيوبية كان في الخط الأول لندينه ومطاردة عليه للخروج من المدينة. ولكن تلك المصورة على شريط الفيديو الخام بريء حتى تثبت إدانته في محكمة قانونية. تمكنوا من إجراء مظاهرة سلمية جدا ومثالية ضد التعديات على القاسي حقوقهم الأساسية في حرية العبادة. لم يكونوا أبدا تهديدا لإثيوبيا أو الحكومة. كانوا وطنيين حقيقية تعنى حالة من رجالهم البلد زميل والنساء الذين كانوا الخانق من عدم وجود حرية في ممارسة شعائرهم الدينية. كانوا يعملون بجد وأيضا كان لهم دور فعال كشركاء مع الحكومة منذ بضع سنوات للحصول عليه إعادة انتخابه من قبل أغلبية السكان مسلم. ولكن هذه سجناء الرأي بدلا أصبحت أهدافا للألعاب الرماية السياسية القذرة. مرة أخرى، والاقتراض من كتيب التضليل، يمكن للمرء أن يرى بوضوح أن المحتجين المعارضين sidetracking أو مع اسم الدعوة مثل "الإرهابيين" وتسخر من وقتهم كرمت البعثة وصفها بأنها "الجهاديين" الضربات القوية للسجلهم جيدة كرجال دولة وكما المفاوضين السلمية. تم تصميم رسالة الفيديو تحط على جعل الآخرين من تقليص دعمها خوفا من كسب تسمية نفسه، وبالتالي فإن الحكومة تحصل بعيدا مع القذف مرة أخرى عن طريق تجنب التعامل مع القضايا الحقيقية المتعلقة بحرية العبادة و.

محتويات الفيلم تنبع أيضا من الباطل وكانت تهدف الى زرع بذور الانقسام داخل المسلمين وبين التقليدين الدينيين البارزين في إثيوبيا. وهذا يضر أيضا بسمعة إثيوبيا للالتسامح العريقة المثالية والتعايش السلمي بين المسيحيين والمسلمين. في التحليل النهائي، فشل هذا الفيلم الخام والتشهير لتسليم الرسالة إلى أن الدعاة المخصصة لذلك. على العكس، انها تنفر الناس كذلك من الحكومة.

وعلى أية حال، بدر إثيوبيا تدين وتستنكر بشدة بث هذا الفيديو وتصنيع محتوياته. غضب بدر الرسالة التي ترغب في إرسالها إلى أولئك من هذا الشريط ومستاؤون أو بالأسى على حالة الحقير من الرجال رأوا مسلم على شاشة التلفزيون هو: احتفظ بها في دعاء الخاص بك. هذا وسوف تمر الحقيقة سوف تؤتي ثمارها لتضحياتهم. الفيديو ملفقة هو مجرد مضمد النافذة، والتي سوف تنهار من تلقاء نفسها. من فضلك لا تقلق، هذه الدراما يظهر فقط الريح رئيس حملة التشويه الجماعي وتراجع هو علامة على اليأس. يمكنك خداع بعض الناس بعض الوقت ولكنك لا تستطيع ان تخدع كل الناس كل الوقت. تذكر لفصل الغث والسمين. لذلك، كان شريط الفيديو على وظيفة أو الأحقاد حملة تشويه؟ سوف يكون لزاما عليك لالتقاط بعض نقاط انعطاف.

أشرطة الفيديو مفبركة مثل الأخبار تمكنت من السيوف ذو حدين. يمكن للحافة السلس ترفيه من خلال تقديم عرض مسرحي. ولكن يمكن حافة خشنة زيادة الخوف والكراهية من خلال تقديم عرض مخيف. لذلك، أي جانب من القاعة كنت جالسا عند شاهد الفيديو: الجانب أو الجانب الخيالي واقع؟ من فضلك، لا تحرق الشمعة منتصف الليل لاكتشاف الحقيقة.

التجربة هي ما تحصل عليه عندما لا تحصل على ما تريد. المصائب هي دفتر شيكات لحقيقة الإيمان.

مينيليك

የአዲስ አበባ አጉስታ ጽዮን ማርያም ቤተክርስትያን በቃጠሎ ወደመች

 • ትላንትና ከቀኑ 7 ሰዓት በተነሳ እሳት ቤተክርስትያኒቱ ውስጥ ከሚገኙ ታቦታት  ፤ ከመጽፍትና ከመስቀል ውጪ ሙሉ በሙሉ አውድሟታል :: ቤተክርስቲያኒቱ በጠራራ ጸሀይ ፤ በቆርቆሮ የተሰራው ግድግዳ እና ድንገት በተነሳ እሳት በአንድነት በመሆን የደረሰውነ ጉዳት  ከፍ አድርገውታል
 • ትላንትና 70 ሺ ብር ከምዕመኑ መሰብሰብ ተችሏል 
  •  እስከ ዛሬ ከቀኑ 6 ሰዓት ድረስ ከ200 ሺህ ብር በላይ ተሰብስቧል ፤ በአሁኑ ሰዓት በርካታ ምዕመናኖች ቦታው ላይ በመገኝት ቤተክርስቲያኒቱን እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ 
  •      ከትላንት ማታ ጀምሮ የተጀመረው ስራ አሁንም ቀጥሏል ፤ ቤተክርስቲያኒቱ ከተቃጠለች 24 ሰዓት ሳይሞላት ማገር አቆመው የጎን ቆርቆሮ የማልበስ ስራ ተጠናቋል፡፡
   •     አካባቢው ያለው ሰው ስራውን ለሚሰሩት ሰዎች እንጀራ ወጥ ፤ ለስላሳ ውሃ እና አስፈላጊ ነገሮችን በማቅረብ ከ48 ሰዓት በፊት ስራን ለመጨረስ እየተረባረበ ይገኛል
   •                የእሳቱን መነሻ አሁንም እየተጣራ ይገኛል  ; እሳት አደጋ ተደውሎለት በሰዓቱ ባለመምጣቱ አደጋውን የከፋ አድርጎታል 
 • የእመቤታችን የቅዱስ ዮሃንስና የቅዱስ ኡራኤል ታቦቶች ምንም አለመሆናቸው እጅጉን አስገርሟል
 • በርካታ ሰዎች እሳቱን ለማጥፋት ተረባርበው ነበር
 • የአካባቢው ወጣቶች እሳቱን ለማጥፋት ያደረጉት መረባረብ እጅግ ያስገረመ ነበር ፤ አሁንም ቤቷን ለማቆን ያለ እረፍት እየሰሩ ይገኛል ፤

ኦህዴድ በ“መደብ ትግል”   መተላለቅ ጀመረ!

ኦህዴድ በ“መደብ ትግል” መተላለቅ ጀመረ!

junedin abadula kuma

በኦህዴድና በህወሓት መካከል የነገሰው ልዩነት ይፋ የወጣው ዛሬ አይደለም። አርሲ ላይ ማዕከል አድርጎ የተደራጀውን የጁነዲንን ኦህዴድ አባዱላ ሙሉ በሙሉ ከናዱት በኋላ ከፈጣጠሩ ጀምሮ ሰንካ ያልተለየው ራሱ ኦህዴድ ውስጥ ውስጡን ሁለት ቦታ ተገምሶ ቆይቷል።

በዘመነ “ህንፍሽፍሽ” ህወሓት ለሁለት በተሰነጠቀበት ወቅት “በህወሓት የውስጥ ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ በመግባት መግለጫ አናወጣም” በማለታቸው ከድርጅትና ከሃላፊነታቸው ተባርረው በነበሩት ኩማ ደመቅሳ ጠቋሚነት ጨፌ ኦሮሚያ አዳራሽ የኦሮሚያ ፕሬዚዳንት ሆነው በ1997 ዓም የተመረጡት አባዱላ ገመዳ ሥልጣን በያዙ ማግስት የጁነዲንን “አርሲ ተኮር” ካቢኔ ሲንዱት ጁነዲንና ደጋፊዎቻቸው ደስተኛ እንዳልነበሩ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ይናገራሉ።ጁነዲን ስልጣን ባስረከቡ በደቂዎች ውስጥ ከጋዜጠኛ ቀርቦላቸው ለነበረ ጥያቄ “ከስልጣን እንደምወርድ ከሁለት ዓመት በፊት አውቀው ነበር” ብለው መመለሳቸውን በስፍራው የነበሩ ያስታውሳሉ።

በዚሁ ሳቢያ በተፈጠረ መቧደን የነጁነዲን ቡድን አባዱላን ለማሰመታት የተደራጀው በጊዜ ነበር። አባዱላን ለማስወገድ ይቻል ዘንድ ተባራሪው ፕሬዚዳንት ጁነዲን የአባዱላ ምክትል የነበሩትን ሙክታር ከድርን ደጋፊያቸው አደረጉ። ይህ መቧደን በተጋጋለበት ወቅት አባዱላ ከሼኽ መሃመድ አላሙዲ ጋር ከፍተኛ ጸብ ውስጥ ገብተው ነበር። አባዱላ ለበታች አመራሮች አላሙዲ አስፈላጊውን ግብር እንዲከፍሉ፣ ያላለሙትን መሬት እንዲነጠቁና የመሳሰሉትን ርምጃዎች በካቢኔ በማስወሰን ተግባራዊ ያደረጉበት ያ ወቅት አባዱላ በኦሮሚያ ተወዳጅነት ያተረፉበት፣ በተዛማጅ ደግሞ ወንበራቸው መንገዳገድ የጀመረበት ወቅት ስለመሆኑ ሽኩቻውን የሚከታተሉ በስፋት የሚያወሱት ጉዳይ ነው።

የውጥኑ መነሻና መድረሻው የደረሳቸው አባዱላ በኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ግምገማ የሙስና ጉዳይ ከመነሳቱ በፊት  አስቀድመው ሃጢያታቸውን ተናዘዙ። “ይህንን ቤት ይዤ ለመታገል አይመቸኝም” በማለት ጥይት እንዳይበሳው አድርገው ወዳጆቻቸውና “ተጠቃሚዎች” የገነቡላቸውን ዘመናዊ መኖሪያ ቤት ካርታና የባንክ እዳ ለድርጅቱ አበረከቱ። ሌሎቹም ያላቸውን እንዲያስረክቡ ሲጠየቁ ጁነዲን አዳማ ያላቸውን አንድ ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ እሰጣለሁ አሉ። አዲስ አበባና ለገጣፎ ስላላቸው ህንጻ ዝምታ መምረጣቸውም ይፋ ሆነ። እነ ሽፈራው ጃርሶ፣ ግርማ ብሩ ግን የመንግስት ቤት ውስጥ እየኖሩ በዶላር የሚያከራዩትን ቤት ለማስረከብ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀሩ።

ሙክታር ከድር

በወቅቱ የመለስ ድጋፍ የነበራቸው አባዱላ በግምገማው መጨረሻ እነ ሙክታርን ረቱና ከኦሮሚያ አባረሩ። አካባቢያቸውንም አጸዱ።

አባዱላን ለመምታት የሚደረገው ፍትጊያ ቢያይልም አዲሱ ካቢኔ አባዱላን “ጃርሳው” በማለት ተቀበለ። በጉባኤና በግምገማ “አባዱላን የሚነካ ወዮለት” ማለት ጀመረ። አባዱላም “ልማትን አፋጥኑ እንጂ የፈለጋችሁን አላማና አመለካከት መያዝ ትችላላችሁ። እኔ ሃላፊነቱን እወስዳለሁ” በማለት በወጣቶች የገነቡትን ካቢኔ ስሜቱን አጋሙት። በዚህ መካከል 2002 ምርጫ ሲመጣ በድንገት አባዱላ ኦሮሚያ ክልል እንደማይወዳደሩ ከላይ መወሰኑ ተሰማ። ካድሬው፣ ምክርቤቱና ካቢኔው ውሳኔውን “አንቀበልም” አለ።

ብርሃኑ አዴሎ

በቆረጣ ባለሃብቱ (አላሙዲ) ላይ ተንጠላጥሎ በሙስና መሽተቱና የባለሃብቱ ታዛዥ እንደሆነ የሚነገርለት ብርሃኑ አዴሎ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ ሃላፊነት ሲወገድ ሙክታር ከድር ተክተው ተሾሙ። ሹመቱ የባለሃብቱ እጅ እንዳለበት አብነት ገ/መስቀል ሸራተን አዲስ ስም እየጠራ ወሬውን የአልኮል ቁርስ በማድረግ አስቀድሞ ሲናገር የሰሙ ይመሰክራሉ። በድርጅት ከኢህአዴግ ጋር፣ በጽህፈት ቤት ከጠ/ሚኒስትሩ ጋር የቀረቡት ሙክታር ከድር አባዱላ ገመዳን ለመጎሸም አጋጣሚው ተመቻቸላቸው።

አብነት ገ/መስቀል

በዚህ መሃል አባዱላ በድጋሚ ክልሉን እንዲመሩ በኢህአዴግ ምክር ቤት የተወሰነውን ውሳኔ የኦህዴድ ስራ አስፈጻሚ ከጁነዲን፣ ከሙክታር፣ ከሱፊያንና ከሽፈራው ጃርሶ በስተቀር የተቀሩት ተቃወሙ። ምክር ቤቱም አወገዘው። የበታች አመራር ማብራሪያ ጠየቀ። በዚሁ ሳቢያ በረከት ስምኦን አዳማ ወረዱና የኦህዴድን ጠቅላላ ጉባኤ ሰበሰቡ። ካድሬው ሳይፈራ በረከትን ሞገተ። በረከት የድርጅት ውሳኔ መከበር እንዳለበት በማስፈራራት ተናገሩ። ካድሬው አሻፈረኝ አለ። አባዱላ “እባካችሁ” በማለት ተማጸኑ። በሁለት ስብሰባዎች አልበገርም ያለው የካድሬው ተቃውሞ በሶስተኛ ስብሰባ አባዱላ ተማጽኖ አቅርበው፣ ካድሬው አልቅሶና ፈርቶ አባዱላን ለመሸኘት ተስማማ። በረከት ስምዖንና ህወሓት ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ቂም እንደያዙ ስለቆዩ ኦህዴድን ለማጥራት አሁን አጋጣሚው እንደተመቻቸላቸው አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ፡፡

አሁን በኦህዴድ ውስጥ ተፈጠረ የተባለው ቡድን ሲወርድና ሲንከባለል ቆይቶ መለስን በሚተካው አመራር ማንነት ላይ የድርጅቱ ምክር ቤትና ካድሬ ተቃውሞውን በግልጽ አወጣው። ህወሓቶችም በዚህ መልኩ መቀጠል የማይችሉበት ደረጃ ደረሱ። ሁለት ተጻራሪ ቡድኖች የሚያካሂዱት አይነት የመደብ ትግል እየተደረገ መሆኑ ይፋ ሆነ። ለህወሓት ትዕዛዝ እንደቀድሞው መታዘዝ ያቆመው ኦህዴድ ይህንን አቋም ከየት አመጣው?

አዲሱ ኦህዴድ

ቀደም ሲል ከነበረው ኦህዴድ ይልቅ አባዱላ ያደራጁት ኦህዴድ በወጣቶች የተገነባ፣ በካቢኔ ደረጃ አንደኛና ሁለተኛ ዲግሪ ያላቸውና ቀደም ሲል በኦነግ አስተምሮ የበቁ እንደሆኑ ይነገራል። ስለድርጅቱ በቅርበት የሚያውቁ እንደሚሉት አዲሱ ኦህዴድ በማክረር ፖለቲካ የተለከፈ አይደለም። ነገር ግን ኦሮሞ አገሪቱን መምራት አለበት የሚል፣ የመለስ ሂሳብ ባስቀመጠው ስሌት መሰረት ጠ/ሚኒስትርነቱን ያለማቅማማት መረከብ አለብን የሚል አቋም ያራምዳሉ።

አሮጌው ኦህዴድ ኦነግን መታገል ባለመቻሉ አዲሱ ኦህዴድ የኦነግና  የኦሮሞ ብሄራዊ ኮንግረንስ የወጣት ክንፍ አባል የነበሩትን በማስኮብለል አባል ማድረጉ ድርጅቱን እንደበረዘው ጭምጭምታ ይሰማ ነበር። እነ ጁነዲን ድርጅቱን ልቅ በማድረግ ለዚህ አደጋ የዳረጉት አባዱላ እንደሆኑ በተደጋጋሚ ቢያቀርቡም አባዱላ ለህወሓት ባለስልጣኖች፣ ለአዜብ፣ ለመለስ ጠባቂዎች፣ ለደህንነት ሰዎችና አስፈላጊ ናቸው ለሚባሉት ሁሉ የክልሉን መሬት በንግድ ስምና በመኖሪያ ቤት ስም በማደል ስለተወዳጁ፣ በሌላ አነጋገር ስላነካኳቸው ክሱ ተቀባይነት ሳያገኝ ቆየ።

አዲሱ ኦህዴድና አመራሮቹ ሁሉንም አካሄድ ስለሚያውቁና የአባዱላ ውሳኔ አስፈጻሚዎች በመሆናቸው ሌሎች በመሬት ንግድ ገንዘብ ሲያፍሱ “እኛስ” በማለት በጋራ ገንዘብ ወደ ማምረቱ አተኮሩ። የሚፈሩ የነበሩ የህወሓት ባለስልጣናት መሬት ፍለጋ በየማዘጋጃ ቤቱ ደጅ ሲጋፉ መናናቅ ተፈጠረ። ህወሓት ገንዘብ ሲያሳድድ ቀደም ሲል የነበረውን ስም አጣ። ኦህዴዶች በስም እየጠሩ ለህወሓቶች ምጽዋት እንደሚሰጡዋቸው ይናገሩ ጀመር። ቀደም ሲል ከነበረው ፖለቲካ እምነት ጋር ተዳምሮ ህወሓት ተናቀ፤ ተጠላ – በተለይም በኦህዴድ። ኦህዴድ የአመራሩ ባለቤት መሆን እንዳለበት ካድሬው በግልጽ ያወራ ጀመር። በዚሁ ሳቢያ በርካታ አዳዲስ የካቢኔ አባላት በሙስና ስም እንዲታሰሩ ተደረገ። ኩማ ደመቅሳ ቡራዩ በተካሄደ ዝግ ስብሰባ ተልዕኳቸውን አሳኩ። አዲሱ ኦህዴድ አጥብቆ የሚጠላቸው ኩማ መጨረሻቸው ባይታወቅም ከፊት መስመር ሆነው የማስተናበሩን ስራ እየመሩ ነው። አዲሱ ኦህዴድ ከሞላ ጎደል ይህ ነው። በሙስና የሸተተ፣ በአመላካከት የተሻለ፣ ዥንጉርጉር አቋም ያካተተ፡፡

“በአንድ ድርጅት ውስጥ የመደብ ትግል ካለ መተላለቅ ተጀምሯል ማለት ነው”

ኦህዴድ እንደ ድርጅት ሊቀጥል የማይችልበት ደረጃ መድረሱን የሚያመለክቱ መረጃዎች እየወጡ ነው። በአንድ ፓርቲ ውስጥ “የመደብ ትግል” የተባለ ግምገማ መካሄዱን ተከትሎ ከህወሓት መሰንጠቅ ቀጥሎ በኢህአዴግ ታሪክ ትልቅ የተባለ የማጥራት እርምጃ ይወሰዳል ተብሎ ተገምቷል። ጉዳዩን አስመለክቶ ያነጋገርናቸው “የመደብ ትግል ካለ መተላለቅ ተጀምሯል ማለት ነው” ብለዋል።

በልዩ ጥበቃ ካለፈው እሁድ ጀምሮ ለአራት ቀናት በተካሄደው የኦህዴድ ምክር ቤት ግምገማ ድርጅቱ እንደ ድርጅት መቀጠል የማይችልበት ደረጃ መድረሱና፣ ለድርጅቱ የተቀመጠው መስመር መጣሱ በዋናነት የተነሱ የግምገማው መነሻ ጉዳዮች መሆናቸውን የጎልጉል ምንጮች ገልጸዋል።

በየሳምንቱ ረቡዕ የሚታተመው ሰንደቅ የተባለው ጋዜጣ “ የሰላ መደባዊ ትግል” መካሄዱን አስነብቧል። በረከት ስምዖን ከኋላ ሆነው የሚመሩት ሰንደቅ ጋዜጣ “ስርዓቱን ለማኖር ሲባል የድርጅቱን መስመር በርዘው በሚንቀሳቀሱት አመራሮች ላይ የማያዳግም እርምጃ የሚወሰድበት ትግል” ሲል ባልተለመዱ የግምገማ ቃሎች ኦህዴድ ውስጥ የተከሰተውን ችግር ይፋ ያደረገው ዜና ችግሩን ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ሹመት ጋር አያይዞታል።

ጎልጉል የአዲስ አበባ ምንጮች እንደሚሉት ግን ኦህዴድ የጠቅላይ ሚኒስትርነት መቀመጫው እንዲሰጠው አለመጠየቁ ካድሬዎቹን አበሳጭቷል። በበታች አመራሮች አማካይነት የተነሳውን የቆየ ጥያቄ የድርጅቱ ሥራ አስፈጻሚ በኢህአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ ወቅት ያቀርባል ተብሎ ሲጠበቅ አለማቅረቡ አሁን ይፋ ለወጣው “የመደብ” ችግር ዋና መንስዔ ነው።

በኦህዴድ ምክር ቤት ደረጃ አቋም የተያዘበትን ጉዳይ ወደ ጎን በመተው ለሃይለማርያምና ለደመቀ ድምጽ በመስጠት የተመለሰው ሥራ አስፈጻሚ የልዩነት አቋም አራምደዋል በተባሉት በምክርቤቱ አባላት፣ በበታች አመራርና ካድሬዎች ዘንድ ቅሬታ አስነስቷል። በዚሁ ሳቢያ የቆየው ክፍፍልና ቁርሾ ይፋ ሊወጣ ችሏል።

ከሥራ አስፈጻሚው ጀምሮ በተዋረድ ባለው መዋቅር እስከ ቀበሌ የደረሰው የልዩነት ደረጃ በመካረሩ “የመደብ ትግል” የሚል ስያሜ የተሰጠው ግምገማ እንዲካሄድ ምክንያት ሆኗል። ጎልጉል ያነጋገራቸው የፖለቲካ ተንታኝ “በአንድ መስመር ላይ ሆነው በሚሰሩ የአንድ ድርጅት አባላት መካከል የመደብ ልዩነት ሊከሰት አይችልም። ከተከሰተም ልዩነቱ እስከመጫራረስ የሚያደርስ ይሆናል” ሲሉ የግምገማው ውጤት መዘዝ ሊያስከትል እንደሚችል ያስረዳሉ።

“የመደብ ትግል” አሉ አስተያየት ሰጪው “የመደብ ትግል ከሁለት በላይ በሆኑ ተጻራሪ ሃይሎች መካከል የሚካሄድ አሸናፊና ተሸናፊ ያለው ትግል ነው። ኦህዴድ ውስጥ በትክክል የመደብ ትግል የሚባል ግምገማ ከተነሳ ጉዳዩ አሳሳቢ ነው። የመደብ ትግል ብሎ ግምገማ ስለሌለ ድርጅቱ ከፍተኛ አደጋና የህልውና ቀውስ ይገኛል ማለት ነው። ኦህዴድ በመደብ ልዩነት ችግር ከተመታ ፓርቲው እንደ ፓርቲ መቀጠል አይችልም ማለት ነው። ቀውሱ ወደ ሌሎቹም ድርጅቶች የመዛመት ዕድሉ በጣም ከፍተኛ ይሆናል” በማለት አስተያየታቸው ሰጥተዋል።

መለስ የቆፈሩዋቸው ጉድጓዶች በሚል ርዕስ ስማቸው ለጊዜው እንዳይጠቀስ ጠይቀው ከጎልጉል ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት የኢህአዴግ ሰው ከወር በፊት“የወንበር ጥያቄው መነሳቱ አይቀርም። ካድሬውና የበታች አመራሩ ድሮም ጀምሮ ሃሳቡ አለው። ግምገማ እየተባለ በሰርጎ ገቦች እየተሰለሉ እየተወገዱ እንጂ እስከዛሬም አይቆይም ነበር። ያም ሆነ ይህ መለስ ስለሌሉ የወንበር ቡቅሻው የማይቀር ነው። በየድርጅቱ አመራሮች ዘንድ የሌባና ፖሊስ፣ የሃይል ሚዛንና ቅኝት፣ አሰላለፍን የማሳመር ሰልፍ እየታየ ነው። አሁን በዝርዝር የማልናገረው አንዳንድ የመናድ ምልክቶችም አሉ”  በማለት ቅድመ ትንበያቸውን አስቀምጠው ነበር። (የቃለምልልሱን ሙሉ ቃል ለማንበብ እዚህ ይጫኑ)

የግምገማውን ውጤት አስመልክቶ በማስጠንቀቂያ የሚታለፉ፣ በህግ የሚጠየቁ፣ የፖለቲካ ውሳኔ የሚተላለፍባቸው እንደሚኖሩ ይጠበቃል። የበረከት ጋዜጣ ሰንደቅ እንዳለው መሸፋፈንና ማድበስበስ የለውም በተባለለት “እርቅ የሌለው ትግል” ሲጠናቀቅ ያለመከሰስ መብታቸው ተነስቶ ለህግ የሚቀርቡ አሉ። የጎልጉል የመረጃ ምንጮች እንደሚሉት የኦህዴድ ሰዎች በፓርላማና በድርጅት ለመለስ እያጨበጨቡ፣ እያንቀላፉ ባጸደቁት ህግ መቀጣታቸው አይቀሬ ነው።

ከፖለቲካው በተጨማሪ ከሃይማኖት ጋር በተያያዘ “አሸባሪነትን ለሚቀሰቅሱና አገሪቱ በሸሪዓ ህግ እንድትመራ ለመጠየቅ እቅድ ከያዙ ክፍሎች ጋር በማበርና ዓላማቸውን ተግባራዊ እንዲያደርጉ ውስጥ ውስጡን የማሳለጥ ስራ ሲያከናውኑ ነበሩ” የተባሉም አሉ። ምንጮቻችን እንዳሉት ኢህአዴግ የሙስና ፋይል የሚከፍትባቸውም አይታጡም።

ህወሓቶች የሚመሩት የስለላው ሃይል አባላቱ ለሚከሰሱበት ክስ ሰነድ አዘጋጅቶ እንደጨረሰ ያስታወቁት ክፍሎች ከኦህዴድ አመራሮች መካከል ቀደም ሲል በጁነዲን ሳዶ፣ አባዱላ ገመዳና አሁን ደግሞ ኩማ ደመቅሳ መካከል ያለውን አሰላለፍና ልዩነት ሲከታተል ነበር። በዚሁ መሰራት ስም ባይዘረዝሩም እርቅ የሌለበት ግምገማ ሲጠናቀቅ ቀደም ሲል ጀምሮ የነበሩ ጉዳዮች እንደ አዲስ እንደሚነሱ የጎልጉል ምንጮች አስታውቀዋል።

የሕወሓት አብዮት ሰለባዎች.. የአዋሳ ከንቲባ አቶ ሽብቁ እስር ተፈረደባቸው

የሕወሓት አብዮት ሰለባዎች.. የአዋሳ ከንቲባ እስር ተፈረደባቸው
 ከሰሞኑ በደቡብ ክልል ጉራ ፈረዳ ወረዳ የአማራ ክልል ተወላጆች ተባረው መሬታቸው ለሌሎች የስርዓቱ ደጋፊዎችና አባላት በሃራጅ መሸጡን ዘ-ሐበሻ ስትዘግብ ቆይታ ነበር። ከአዲስ አበባ የመንግስት ሚዲያዎች ያስተላለፉት ዜና ደግሞ የሃዋሳ ከተማ ነዋሪ ላልሆኑ ሰዎች መሬት የሸጡ የክልሉ ባለስልጣናት በሙስና ወንጀል ተከሰው እንደተፈረደባቸው ያትታሉ። የሕወሓት/ኢሕአዴግ ሥር ዓት አብዮት ለስልጣኑ ታማኝ ያልሆኑትን በሙስና ሰብብ ሲበላ መቆየቱን ያስታወሱት አስተያየት ሰጪዎች በታምራት ላይኔ ጀምሮ በስዬ አብርሃ ለጥቆ አሁን የጸረ ሙስና ሕጉ የቂም በቀል መወጣጫ ሆኗል ሲሉ ይተቻሉ።
ኃላፊ በነበሩበት ወቅት ስልጣናቸውን አላግባብ በመጠቀም መሬት ለግለሰቦችና ድርጅቶች ሰጥተዋል በሚል የሙስና ወንጀል ተከሰው የነበሩ የቀድሞ የሃዋሳ ከተማ ከንቲባና ሌሎች ስድስት ተከሳሾች በእስራትና በገንዘብ መቀጣታቸውን የመንግስት መገናኛ ብዙሃን እያዳነቁ ዘግበዋል። በማዳነቂያ ዜናቸው ላይ “ግለሰቦቹ ለመኖሪያ ቤት የማይፈቀድን ቦታ ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ፥ የተጻፈውን ዕገዳ በመጣስ የተለያዩ ግለሰቦች እና ጋዜጠኞችን ጨምሮ በሀዋሳ ከተማ ነዋሪ ላልሆኑ ስምንት ሰዎች መሬትበመስጠታቸው ነው የተከሰሱት (የተሰመረበትን ይመልከቱ)ሲሉ ነው የመንግስት ሚድያዎች የዘገቡት።
እነዚሁ ሚዲያዎች ዘገባቸውን ሲያጥናቅር “የደቡብ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው ችሎት የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ የነበሩትን ፥ አቶ ሽብቁ ማጋኔን ጨምሮ 6 ተከሳሾች ላይ ከአንድ እስከ ስምንት ዓመት በሚደርስ እስራትና ከ2 እስከ 20 ሺህ ብር እንዲቀጡ፤ ፍርድ ቤቱ የክልሉ ጸረ ሙስና ኮሚሽን ይግባኝ በጠየቀባቸው ፥ አቶ ሽብቁ ማጋኔ፣ አቶ እንድርያስ ፉላሳ፣ አቶ ጸጋዬ አረጋ፣ አቶ ጉደታ ጉምቤ፣ አቶ አስራት ግቻሞና አቶ ከበደ ካያሞ ላይ የእስራትና ገንዘብ ቅጣቱን የወሰነው የስር ፍርድ ቤቱ የሰጠውን ውሳኔ በመሻር ነው።” ብለዋል። የመንግስት ሚዲያዎቹ “በዚሁ መሰረት በአቶ ሽብቁ ማጋኔ ላይ የአምስት አመት ከስድስት ወር ጽኑ እስራትና በአምስት ሺህ ብር ፣ አቶ እንድሪያስ ፉላሳና ፥ አቶ ጉደታ ጉምቤ እያንዳንዳቸው በ5 ዓመት ከ6 ወር እስራትና በ15 ሺህ ብር እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱ ወስኗል። አቶ አስራት ግቻሞ አንድ አመት ከ2 ወር እስራትና የ2 ሺህ ብር መቀጫ ፣ እንዲሁም አቶ ከበደ ካያሞ በአንድ ዓመት እስራት እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱ ወስኗል። ጉዳያቸው በሌሉበት የታየው አቶ አረጋ ጸጋዬ በስምንት ዓመት ጽኑ እስራትና በ20 ሺህ ብር እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ አስተላልፏል ።” ሲሉ ዘገባቸውን አጠናቀዋል።
የዘ-ሐበሻ አንባቢዎች “በሀዋሳ ከተማ ነዋሪ ላልሆኑ ስምንት ሰዎች መሬት ሰጣችሁ” ተብለው በተፈረደባቸው የሕወሓት አብዮት ሰለባዎች ዙሪያ ምን ትሉ ይሆን? የስልጣን ላይ እንቅልፍ ያሉትስ ነገ በኔ ላይ አይመጣም ብለው ቁጭ ያሉትስ ምን ይሉ ይሆን? አስተያየታችሁን አስቀምጡ።

ገዢው ፓርቲ ዜጎችም ሚቃወሙ ፓርቲዎችና ፖለቲከኞች ይንሸራተታሉ።

ለምን ቢባል? ገዢው ፓርቲ ብቻ አይደለም ወደኋላ የሚንሸራተተው። ዜጎችም ይንሸራተታሉ። ኢህአዴግንስ ወቀስን። ግን፤ ምሁራንና ዜጎች ወይም ኢህአዴግን የሚቃወሙ ፓርቲዎችና ፖለቲከኞችስ? በሂደት ነፃነት እንዲስፋፋና ወደ አሜሪካው አይነት የፖለቲካ ሁኔታ እንድንጓዝ ይመኛሉ? ወይስ በኢህአዴግ ቦታ ሁልጊዜ 99.9% የሚያሸንፍ ሌላ ገናና ፓርቲ ተተክቶ ማየት ነው የሚፈልጉት? ሁሉም ሰው ተቃውሞውንና ድጋፉን በነፃነት የሚገልፅበት ስርዓት እንዲስፋፋ ነው የሚያልሙት? ወይስ፤ ኢህአዴግን ተክተው የነሱ ሃሳብ ብቻ እየተስተጋባ የሌሎች ሰዎች ሃሳብ እንዲታፈን ነው? በአጭሩ የትኛው ይማርካቸዋል - የአሜሪካ ወግ ወይስ የቻይና ወግ?የአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ እንዲህ የኋሊት መንሸራተቱ አያሳዝንም? ከተጨባጩ ሁኔታ ይልቅ ይበልጥ አሳዛኝ የሚሆነው ግን፤ ብዙ ኢትዮጵያውያን ለወደፊት ያላቸው ምኞት ያን ያህልም ብሩህ ሳይሆን ሲቀር ነው።
ከአሜሪካና ከቻይና የፖለቲካ ድግሶች መካከል፤ የአሜሪካው ካላጓጓን፤ ከሁለቱ አገራት ወግ መካከል የአሜሪካው በጣሙን ካልማረከን፤ በእጅጉ ማዘን ይኖርብናል እላለሁ።  ከአስር አመት በፊትኮ፤ የድጋፍም ሆነ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ፤ የአገሪቱ መልካም የፖለቲካ ባሕል ለመሆን እየተቃረበ ነበር። “ይሄውና ዜጎች ሃሳባቸውን በነፃነትና በሰላም የሚገልፁበት እድል እየተስፋፋ ነው” ብለን የምንሟገትለት መልካም ሂደት ዛሬ የለም። አዲስ አበባ ውስጥ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ካየን ሰባት አመት ልንደፍን አይደል! “ይሄውና የግል ጋዜጦች እየተበራከቱና እየተሻሻሉ ነው” ብለን የምንደግፈው የያኔው የፕሬስ ነፃነት ሂደትም፤ ዛሬ ዛሬ የኋሊት የሚጓዝ ሆኗል። የግል ጋዜጦች ቁጥር ተመናምኗል። ዜጎች የድጋፍም ሆነ የተቃውሞ ሃሳባቸውን የሚገልፁበት ነፃነትም እየጠበበ መጥቷል። ዛሬ የመንግስትንና የገዢውን ፓርቲ መመሪያ ለማስፈፀም ነው፤ ዜጎች 1ለ5 ሲደራጁ የምናየው።ከአስር አመት በፊት ከነበረው የፖለቲካ ሁኔታ ይልቅ የዛሬው የተሻለ መሆን አልነበረበትም? ግን አስተውሉ። ዛሬ ከያኔውም ብሶበት የተቃዋሚ ፓርቲዎች ድምፅ እየጠፋ መጥቷል። ሁለት የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትን ብቻ ይዞ የነበረው ፓርላማ፤ በተከታዩ ምርጫ ተሻሽሎ 12 ያህል የተቃዋሚ ፓርቲ ተመራጮችን አስተናግዷል። ከዚያም የፖለቲካ ምርጫዎች ላይ የፓርቲዎች ፉክክር እየተሻሻለ፤ በፓርላማ ውስጥ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ቁጥር ከመቶ በላይ ሲሆን አይተናል። ይሄ ጥሩ ሂደት ነበር። “ይሄው ተመልከቱ፤ በርካታ ፓርቲዎች የሚፎካከሩበት የፖለቲካ ስርዓት እየተስፋፋ ነው” ብለን የምንሟገትለት ሂደት ነበር። ዛሬ ግን፣ “ሂደቱ” ወደ ኋላ ተመልሶ፤ የምርጫ ፉክክር ጠፍቷል። ገዢው ፓርቲ 99.9 በመቶ እያሸነፈ፤ ፓርላማውን ከሞላ ጎደል ተቆጣጥሮታል - ከአንድ የተቃዋሚ ፓርቲ አባል በስተቀር።እውነትም፤ በግለሰብ ነፃነትና መብት ላይ የተመሰረተ የዲሞክራሲ ስርዓት ለማስፈን ጊዜና ጥረት ያስፈልጋል። ነገርዬው የሂደት ጉዳይ ነው። በሂደት ነው፤ የአገራችንን ፖለቲካ የሚሻሻለው። በሂደት ነው፤ ከቻይናው አይነት ፖለቲካ ወደ አሜሪካው አይነት ፖለቲካ መጓዝ ወይም መገስገስ የሚቻለው። አአሳሳቢው ነገር ምን መሰላችሁ? የአገራችን “ሂደት”... ቀስ በቀስ “ሂደትነቱ” እየጠፋ መምጣቱ ነው። ባለበት የሚረግጥ ከሆነ፤ “መሄድ”ን ረስቷል ማለት ነው። ጭራሽ... “ሂደቱ” የኋሊት ማፈግፈግና ተመልሶ ወደ ቻይና መጠጋት ሲጀምርስ? ባለፉት ሰባት አመታት ይህንን ወደ ኋላ የመመለስ አሳዛኝ “ሂደት” የተመለከትነው።“ሂደት”፣ መሄድ አቆመ
ታዲያ፤ ከተለያየ አቅጣጫ አይተን ስንመዝነው፤ የአገራችን ፖለቲካ ወደ ቻይና በእጅጉ የተጠጋ መሆኑ ያከራክራል?  ደግሞስ፤ ከ22 አመታት በፊትኮ፤ የኢትዮጰያ ፖለቲካ ከቻይና የባሰ አልነበር እንዴ! በደርግ የኮሙኒዝም አገዛዝ ወቅት፤ ከገዢው ፓርቲ ውጭ ሌላ ፓርቲ ማቋቋም ወንጀል ነበር። ተቃውሞና ትችት ማሰማት የተከለከለበት፤ የግል ሚዲያ የማይፈቀድበት ዘመን ነበር። ታዲያ፣ ዛሬም የአገራችን ፖለቲካ ከቻይና ጋር ተቀራራቢነት ቢኖረው ምኑ ያስገርማል? ኢህአዴግም ራሱ ከሞላ ጎደል የሚስማማበት ይመስለኛል። “የዲሞክራሲ ግንባታ በርካታ አመታትን የሚፈጅ ሂደት ነው” ይል የለ! አዎ፤ አገራችን ውስጥ ዜጎች በማህበር ሲደራጁና በምርጫ ዘመቻ ላይ ለመሳተፍ ሲንቀሳቀሱ ይታያል። ነገር ግን፤ እንደ አሜሪካ አይደለም። በአገራችን፣ ሁሉም ዜጎች በነፃነት የመንቀሳቀስ እድላቸው ጠባብ ነው፤ ለእስርና ለወከባ ሊዳረጉ እንደሚችሉ ያውቁታላ። ገዢውን ፓርቲ የሚደግፉ ከሆነ ነው ስጋት የማይኖርባቸው - እንደ ቻይና።አዎ፤ በአገራችን ነፃ አስተያየቶችና ዘገባዎች በግል ጋዜጦች ይታተማሉ። ግን ፍርሃትና ስጋት እንዳጠላባቸው ነው የሚታተሙት። መንግስት በማንኛውም ሰዓት የግል ጋዜጦችን ሊዘጋ፣ የግል ሬዲዮ ጣቢያዎችን ሊወርስ እንደሚችል ይታወቃልና። በዚያ ላይ፤ የግል ቴሌቪዥን ጣቢያ ማቋቋም እስካሁን አልተፈቀደም። አገሪቱ ላይ የሚፈነጩት የመንግስት የሬድዮና የቲቪ ስርጭቶች ናቸው - እንደ ቻይና ማለት ነው። በአሜሪካ ግን፤ የመንግስት ጋዜጣ የለም። በሺ የሚቆጠሩ የሬድዮና የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ባጥለቀለቋት አሜሪካ ውስጥ፤ መንግስት የሬድዮና የቴሌቪዥን ጣቢያ የለውም (ከቪኦኤ ጣቢያ በስተቀር)። ለነገሩ፤ በመንግስት የሚተዳደረው የቪኦኤ ሬዲዮ ጣቢያ ፕሮግራሞቹን አሜሪካ ውስጥ እንዲያሰራጭ አይፈቀድለትም። ለምን? መንግስት በአገሩ ውስጥ ፕሮፓጋንዳ የማሰራጨት ስልጣን እንዳይኖረው ለመከልከል ነው። አዎ፤ አገራችን ውስጥ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ማቋቋም ይፈቀዳል፤ በርካታ ተቃዋሚ ፓርቲዎችም አሉ። ነገር ግን፤ እንደ አሜሪካ አይደለም። ከገዢው ፓርቲና ከአጋሮቹ በስተቀር፤ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አባላትን ለማበራከትና ዜጎችን መቀስቀስ በነፃነት የመንቀሳቀስ እድላቸው ጠባብ ነው። አንድ ገዢ ፓርቲ ነው የገነነው - እንደ ቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ። አዎ፤ አገራችን ውስጥ በየአምስት አመቱ በሚዘጋጁ ምርጫዎች የፖለቲካ ፓርቲዎች ይሳተፋሉ። ግን፣ ጠንካራ ፉክክር የለም። ሁሌም ገዢው ፓርቲ ነው ስልጣን የሚይዘው - እንደ ቻይና። “የአገራችን ፖለቲካ፣ ከአሜሪካ ጋር ተቀራራቢ ሆኖ የሚታየን በህልም ነው ወይስ በእውን?” ... ብትሉ አይገርመኝም። በእርግጥ በህልምና በምኞት መቀራረብም ቀላል ነገር አይደለም። ነገር ግን፤ እያወራን ያለነው ስለወደፊቱ ምኞታችን ሳይሆን፤ አሁን በእውን ስላለው ተጨባጭ ሁኔታ ነው። በእውን ደግሞ፤ የአገራችን ፖለቲካ ከአሜሪካ ፖለቲካ ጋር በጣም ይራራቃል። ምናልባት፤ ኢትዮጵያ ውስጥ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ማቋቋም የሚፈቀድ መሆኑንና በርካታ ተቃዋሚ ፓርቲዎች መኖራቸውን በማሳየት፤ “ልክ እንደ አሜሪካ ነው” ብለው ሊያሳምኑን የሚሞክሩ መኖራቸው አይቀርም። በዚያ ላይ በየአምስት አመቱ የፖለቲካ ምርጫዎች እየተዘጋጁ ፓርቲዎች ሲሳተፉ ተመልክተናል። ምርጫ ሲቃረብ፤ ለተወሰኑ ሰዓታት የፓርቲዎች ክርክር በቲቪና በሬድዮ ሲሰራጭ አድምጠናል። በግል ጋዜጦች ነፃ አስተያየቶችና ዘገባዎች እየታተሙ አንብበናል። ዜጎች በማህበርም ሆነ በቡድን የምርጫ ቅስቀሳ ሲያካሂዱ እንዲሁም በምርጫው እለት ድምፅ ሲሰጡም ታዝበናል። ይሄ ሁሉ ሲደማመር፤ የአገራችን ፖለቲካ፣ ከአሜሪካ የፖለቲካ ድግስ ጋር የሚቀራረብ ሆኖ ሊታየን አይችልም? አትስማሙም? ፓርቲዎች፣ ምርጫዎች፣ ጋዜጦች፣ ዜጎች“በሁለቱ አገራት ወግ መካከል የሆነ ቦታ ላይ ነው” የሚባለው የአገራችን ፖለቲካስ፤ ወደየትኛው ይጠጋል? ወደ ቻይና ወይስ ወደ አሜሪካ? በየትኛው አይነት የፖለቲካ ድግስ ወይም የፖለቲካ ድራማ ውስጥ ነን? የአሜሪካው ወይስ የቻይናው አይነት? ያን ያህልም ከባድ ጥያቄ እንዳልሆነ የምንስማማ ይመስለኛል። “ከሁለቱም ይለያል፤ ከሁለቱ መካከል የሆነ ቦታ ላይ ነን” ብሎ መልስ መስጠት ይቻላል። ግን ምን ዋጋ አለው! እንዲህ በደፈናው የሚቀርብ ምላሽ ብዙም አይጠቅምም። ውሃ የሚፈልግ ሰው፤ “ብርጭቆው ባዶ ነው ወይስ ሙሉ?” ብሎ ሲጠይቅ፤ “ብርጭቆው ባዶ ወይም ሙሉ አይደለም፤ የሆነ ያህል ውሃ ይዟል” ብሎ እንደመመለስ ነው። ምን ያህል ውሃ? ወደ ባዶ የተጠጋ? ወይስ ወደ ሙሉ የተጠጋ?... ለየት ያለ ሁለተኛ ጥያቄ ልጨምርላችሁ - “የሁለቱ አገራት ወግ ውስጥ፤ የኛ የዜጎች እንዲሁም የአገራችን የኢትዮጵያ ወቅታዊ ቦታ የቱ ጋ ነው?” ... ይሄ የምኞትና የራዕይ ጉዳይ አይደለም። በእውን የኖርንበትና አሁን የምንኖርበት የፖለቲካ ሁኔታ ምን እንደሚመስል አይቶና መዝኖ የመፍረድ ጥያቄ ነው። ሁለቱ የፖለቲካ ድግሶች፣ በአንድ ፕላኔት በአንድ ሳምንት የተካሄዱ ቢሆኑም፣ ልዩነታቸው ግን የሰማይና የምድር ያህል ነው። በተለያዩ ፕላኔቶችና በተራራቁ የታሪክ ዘመኖች የተካሄዱ ይመስላሉ። ዋናው ጥያቄ፤ “ለመሆኑ ‘ከሁለቱ አገራት ወግ’ ውስጥ፤ የትኛው ይማርከናል?” የሚል ነው። አሜሪካን ወይም ቻይናን የመደገፍ ጉዳይ አይደለም። ነገርዬውን የኛ ጉዳይ እናድርገው። ለራሳችን ወይም ለአገራችን፣ የትኛውን አይነት የፖለቲካ ድግስ እንፈልጋለን? የትኛውን እንመኛለን?... ጥያቄው፣ የምኞትና የፍላጎት አልያም የራዕይና የአላማ ጥያቄ እንደሆነ ልብ በሉ።‘የሁለት አገራት ወግ’
ነገር ግን “መምረጥ አትችልም” ብለው አይተዉትም። እረፍት አይሰጡትም። ሁሉም ቻይናዊ የ”ምርጦቹ”ን ስብሰባና ዲስኩር በቴሌቪዥን የመከታተል ግዴታ አለበት። በትምህርት ቤቶችም ሆነ በሥራ ቦታዎች፤ ተማሪዎችም ሆኑ ሠራተኞች፤ አዳራሽ ውስጥም ሆነ ዛፍ ጥላ ስር፣ ወንበር ከተገኘ ቁጭ ብለው፣ ከሌለም ቆመው ቴሊቪዥን ማየት ግዴታቸው ነው።እነዚሁ ሁለት ሺ “ምርጦች”፤ አገሪቱን ለአስር አመታት የሚገዛ የፓርቲ መሪ ለመሰየም ሰሞኑን ስብሰባ ጀምረዋል። የንጉሥ ዘሮችና የመሳፍንት ቤተሰቦች አይመስሉም? በቃ! እነሱ ናቸው አድራጊ ፈጣሪዎች። በነሱ ስብሰባ ነው ፕሬዚዳንት የሚመረጠው። ከግማሽ ሚሊዮን ቻይናዊያን መካከል አንድ ሰው ብቻ ነው፤ የ”ምርጦቹ” ስብሰባ ውስጥ መግባትና ድምፅ መስጠት የሚችለው። 99.999% ያህሉ የቻይና ዜጋ ድምፅ የመስጠት መብት የለውም። ሁለተኛው የፖለቲካ ድግስ (ድራማ)፤ 1300 ሚሊዮን ህዝብ በያዘችው ቻይና ውስጥ የተሰናዳ ነው። ድግሱ ግን ጥቂቶች የሚታደሙበት መሆኑ ለየት ያደርገዋል። የአገሪቱን ፕሬዚዳንት የመምረጥና ድምፅ የመስጠት መብት ያላቸው የቻይና ዜጎች 2ሺ ብቻ ናቸው። የምርጫ ዘመቻና ፉክክር ብሎ ነገር የለም። አማራጭ ፓርቲዎችና የሃሳብ ክርክሮች በአገሪቱ ውስጥ ለምልክት ያህል እንኳ አይታዩም። መከራከርም ሆነ መተቸት፤ መቃወምም ሆነ ተፎካካሪ ፓርቲ መመስረት አይቻልም። አንድ ገዢ ፓርቲ የነገሰባት አገር ነች - ቻይና። በውርስ የሚተላለፍ “ሥርወ መንግስት” ይመስላል። የፓርቲው መሪዎች ብቻ ናቸው፤ አገሪቱን እየተፈራረቁ የሚገዟት። ሁለት ሺ የሚሆኑ የፓርቲው የበላይ ካድሬዎች (ምርጦች) ናቸው አገሪቱን የሚቆጣጠሯት። በምርጫው የዲሞክራቲክ ፓርቲው ባራክ ኦባማ ለፕሬዚዳንትነት አሸንፈዋል፤ ተፎካካሪያቸው ሚት ሮምኒም በዚያው ምሽት ስልክ ደውለው “እንኳን ደስ ያለህ” ብለዋቸዋል። በምክር ቤት ምርጫ ግን አብዛኛውን የኮንግረስ ወንበር ያሸነፉት የሪፐብሊካን ፓርቲ አባላት ናቸው። ተፎካካሪዎች እለት በእለት በየመድረኩ የሚያቀርቡትን የእርስ በርስ ትችትና አማራጭ ሃሳብ መስማት ብቻ አይደለም - የዜጎች ድርሻ። ተፎካካሪዎች በየደቂቃው በተለያዩ የግል የቴሌቪዥን ጣቢያዎች የሚያስተላልፉት ክርክርና እልፍ ማስታወቂያ መከታተል ብቻ አይደለም - የዜጎች ፋንታ። ዜጎች ራሳቸው፤ ያሻቸውን ተፎካካሪ በመደገፍ ቅስቀሳ ያካሂዳሉ። እንደየዝንባሌያቸውና እንደየፍላጎታቸው ማህበር እያቋቋሙ፣ ከተፎካካሪዎቹ ባልተናነሰ ሁኔታ ማስታወቂያዎችን ያሰራጫሉ። በመጨረሻም ይመርጣሉ። አንደኛው ድግስ፣ ባራክ ኦባማና ሚት ሮምኒ አንገት ለአንገት የተፎካከሩበት የአሜሪካ ምርጫ ነው። የተፎካካሪዎችን ፋታ የማይሰጥ ክርክርና የምርጫ ዘመቻ ሲከታተሉ የከረሙ ከመቶ ሚሊዮን በላይ አሜሪካዊያን፤ ማክሰኞ እለት የምክር ቤት አባላትንና ፕሬዚዳንታቸውን መርጠዋል። ሕፃናትን ሳይጨምር ከአገሪቱ ዜጎች መካከል ቢያንስ 50% ያህሉ በምርጫ ዘመቻ ተዋናይነት ወይም በድምፅ ሰጪነት ተሳትፏል - ያሻውን እየደገፈና እያደነቀ፣ ያሰኘውን እየተቃወመና እየተቸ። አለማችን ዥንጉርጉር ነች። ሰሞኑን እጅግ የተለያዩ ሁለት አይነት የፖለቲካ ድግሶችን አስተናግዳለች።

ግብፆች-የዲፕሎማሲ ጥረት የማይሳካላቸው ከሆነ በጦር ኃይል የኢትዮጵያን ግድቦች የማፈራረስ ዕቅድ

ሰሞኑን ዊኪሊክስ ምሥጋና ይድረሰውና ግብፆች ምን እንዳሰቡ ምስጢራቸውን አሾልኮባቸዋል፡፡ የዲፕሎማሲ ጥረት የማይሳካላቸው ከሆነ በጦር ኃይል የኢትዮጵያን ግድቦች የማፈራረስ ዕቅድ መያዛቸውን ነግሮናል፡፡ ዊኪሊክስ ትክክል ይሁን አይሁን ኢትዮጵያ በግዴለሽነት ልታየው አይገባም እላለሁ፡፡ ጊዜ ለመግዛት ይሁን ለማዘናጋት ግብፆች ሕዝባዊ ዲፕሎማቶች (Public Diplomats) በላኩ ሰሞን በኢትዮጵያ ውስጥ የግብፆች አመለካከት ተቀይሯል የሚል ሐሳብ ደጋግሞ ይነገር ነበር፡፡ ይህን ደግሞ የመንግሥት ብዙኃን መገናኛ ሲያስተጋቡት ነበር፡፡ ምን ማረጋገጫ አለን ብሎ ጥያቄ የሚያነሳም አይሰማም ነበር፡፡

የተለየ ሐሳብ የሚያቀርብና የሚጠይቅ በሚዲያው አይቀርብም፡፡ ሐሳብ ሀብት መሆኑ ቀርቶ ይፈራል፡፡ ግን ሐሳብ በመኖሩ ሰው እንደ ዝንጀሮዎቹ (ሳይንስ ዘመድ ነን ይላል) ከመኖር ወጥቶ አሁን ካለበት ደርሷል፡፡ ሐሳብን እንደ ሀብት የማንቆጥር በመሆናችን እንፈራዋለን፤ እናፍነዋለን፡፡ ለማጥፋትም እንጥራለን፡፡ የተለያዩ ሐሳቦች ሲጠፉ ደግሞ ድንቁርና ይነግስና ባለንበት መርገጥ ከዚያም ወደኋላ መንሸራተት ይሆናል፡፡ እስከመቼ ይሆን በዚህ መልክ የሚቀጠለው? ግብፆች ተስማምተዋል፣ እከሌ የሚባለው ባለሥልጣናቸው ቃል ገብቶልናል፣ እከሌ የሚባለው ደግሞ በጆሯችን ሹክ ብሎናል፣ ጳጳሱና ሼኩ ገዝተዋል በሚል ተስፋና ምኞት ብቻ መኖር አገሪቱን ለአደጋ ማጋለጥ ነው የሚሆነው፡፡ ኃላፊነት የጎደለው ድርጊትም ይሆናል፡፡ ባለፈው በመዘናጋታችን በሻዕቢያ ተወረናል፡፡ ከፍተኛ ዋጋ ከተከፈለ በኋላ ፍርድ ቤቱ ዋሽቶን መሬቱ የእናንተ ተብለን እንደ ፍርድ ቤቱ እኛም መዋሸታችን የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው፡፡

ስምምነቶችና ውሎች አስተማማኝ እንደማይሆኑና እንደማያስጥሉ የአገራችንና የዓለማችን ታሪክ ምስክር ነው፡፡ ለሊግ ኦፍ ኔሽንስ መፍረስ ህያው ምስክር የሆነችውን ኢትዮጵያን ማየት ነው፡፡ ከኢጣሊያ ወረራ አላስጣላትም፡፡ ሒትለር ስምምነቶችን ቀዳዶ ጥሎ ወረራ አካሂዷል፡፡ የዓለምን ሕግ ጉልበተኞች እንደሚመስላቸው እየጠመዘዙ እስከዛሬ ይጠቀሙበታል፣ ስለሆነም አያስጥልም፡፡ ከአውሮፓ ተሰደው ቅኝ ግዛት የመሠረቱት በሄዱበት ክፍለ አኀጉር ሁሉ ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር የገቡትን ቃልና ውል እየሰረዙ አገራቸውን ቀምተዋቸዋል፡፡ እነሱንም እንደ እንስሳት ፓርክ ከተወሰነ ቦታ ላይ አጥረዋቸው ይገኛሉ፡፡

በሰው ደም፣ በንብረትና በፖለቲካ ድጋፍ ትልቅ ውለታ የተሠራለት ሻዕቢያ ለውለታውም ሆነ ለዝምድናው ቦታ ሳይሰጥ ወሮናል፡፡ ከምንም በላይ ደግሞ ስምምነትና ውል ትርጉም እንደሌለው መሪያቸው የተሸወደባቸውን ዘመዶቼ የሚዘፍኑትን ማዳመጥ ከምንም በላይ ስለውልና ስምምነት ያስረዳናል፡፡ ይኼውም ‹‹አያሌው ሞኙ ሰው አማኙ፣ ሰው አማኙ›› ነው፡፡ ስለሆነም ለኢትዮጵያ ደኅንነት ብቸኛውና አስተማማኙ የቅድሚያ መከላከል የሚሊታሪ ዶክትሪን (Deterrance) ወይም ተያይዞ መጥፋትን ‹‹Mutual Assured Destruction (MAD)›› ፖሊሲ መከተልና ለዚህም ማስፈጸሚያ የሚሊታሪ አቅሟንም መገንባትና ዕቅድ ማውጣት አለባት፡፡ ይኸውም ግብፅ የኢትዮጵያን ግድብ በማንኛውም ዓይነት ማለትም በሰላም፣ በተዘዋዋሪም ሆነ በቀጥታ በኃይል አደናቅፋለሁ፣ ጉዳት አደርሳለሁ ብላ ካሰበችና ከተንቀሳቀሰች የኢትዮጵያ የአፀፋ መልስ አስዋን ግድብን ማጥቃት መሆን አለበት፡፡

አስዋን ግድብን በማውደም ከግድቡ የሚያገኙትን የኤሌክትሪክ ኃይል በማጥፋት ወደ ጨለማ ልንከታቸው እንደምንችል፣ ከግድቡ ጋር በተያያዘ የሚያገኙትን የኢኮኖሚ ጥቅም እንደሚያጡ፣ ከአስዋን ግድብ ጀምሮ ያሉት ከተሞቻቸው ከአሥር ሚሊዮን ሕዝብ በላይ የሚኖርባትን ካይሮን ጭምር በጎርፍ ታጥበው ሜዴትሪንያን ባህር ሊቀላቀሉ እንደሚችሉ፣ የሰው ልጅ የሥልጣኔ አሻራና ቅርስ የሆኑት ፒራሚዶቻቸው በጎርፍ ሊጥለቀለቁና ጉዳት ሊደርስባቸው እንደሚችል የሚያስገነዝብ ፖሊሲና ስትራቴጂ ኢትዮጵያ መከተል አለባት፡፡ ይህንም ፖሊሲ ለግብፅና ለዓለም ሕዝብ በግልጽ ማሳወቅ የግድ ነው፡፡ ስለሆነም ግብፆች በኢትዮጵያ ላይ ከሚያደርሱት ውድመት በላይ እንደሚወድሙ ማሳወቅ፡፡ እነሱ ለሚያደርሱት ጥፋት የሚደርስባቸው ድርጊት የከፋና የበለጠ መሆኑን ብቻ ሲገነዘቡና ሲያውቁ በሰላም ተባብሮ መሥራትን ይመርጣሉ፡፡ ከኃይል አማራጭ ወጥተው በሰላም ለጋራ ጥቅም መሥራትን ይመርጣሉ፡፡

ግብፆች በውኃችን ሳንጠቀም ቀርተን በድንቁርና፣ በድህነትና በረሃብ እንድንሞት ከሆነ የሚሰጡን አማራጭ የተሻለው አማራጭ ሀብታችን የሆነውን ውኃችን እየተጠቀምን ከግብፅ ሊመጣ የሚችለውን ሞት መጋፈጥ ይሆናል፡፡ በግብፅም ሆነ በረሃብ መሞት ከሆነ የሚኖረን አማራጭ ከግብፅ የሚመጣውን ሞት መምረጥ ይሻላል፡፡ ምክንያቱም በረሃብ፣ በድንቁርና በድህነት ሊያልቅ ከሚችለው ሕዝብ ጋር ሲነፃፀር ከግብፅ ሊመጣ የሚችለው ሞት በጣም አነስተኛ ከመሆኑም በላይ ፍትሐዊ ሞት ይሆናል፡፡ ኢትዮጵያ የአስዋንን ግድብ ለማጥቃት የሚያስችላት አቅምና ቴክኖሎጂ ገንብታ ዕቅድና ፕላን ይዛ መንቀሳቀስ አለባት፡፡ ለዚህም ሊረዷት የሚችሉ መንግሥታትን፣ በአገርም ውስጥ ሆነ ከአገር ውጭ የሚኖሩትን ኢትዮጵያውያን በሻማ ብርሃን ፈልጋና አስተባብራ አቅም ልትገነባ ይገባል፡፡

ኢትዮጵያ ዘለቄታዊ ሰላም አግኝታ ከድህነት ለመውጣት የምታደርገው ጥረት ሊሳካ የሚችለው እኔ ሰላም ፈላጊና ሰላማዊ ነኝ እያለችና እየሰበከች እጆቿን አጣጥፋ ስለተቀመጠች ሳይሆን፣ ኢትዮጵያን ከነካን የከፋ ኪሳራ ይደርስብናል ብለው እንዲያስቡ ማድረግ ስትችል ነው፡፡ ለዚህም አቅም ገንብቶ በተጠንቀቅ መቆም ያስፈልጋል፡፡ ሱዳንም ከግብፅ ጋር ትብብር አድርጋ ኢትዮጵያን አስጠቅታ ሱዳን የግድቦች፣ የድልድዮችና የወደብ ባለቤት ልትሆን እንደማትችል ኢትዮጵያ ልታስገነዝባት ይገባል፡፡ በኢትዮጵያ ላይ ጉዳት ደርሶ በሰላም መኖር እንደማትችል ማሳወቁ ጊዜአቸውንና ሀብታቸውን ይቆጥብላቸዋል፡፡ ስለሆነም ግብፅና ሱዳን ከኃይል አማራጭ ወጥተው በሰላማዊና በጋራ መተባበር የማይለወጥ አቋም እንዲይዙ፣ የኃይል አማራጩ የማይሠራና የበለጠ ኪሳራ እንደሚያደርስባቸው ማስገንዘብና ለዚህም ማስፈጸሚያ ወታደራዊ አቅም መገንባት ያስፈልጋል፡፡ ይህ ብቻ የኢትዮጵያ ደኅንነት ማስጠበቂያ ዋስትና ይሆናል፡፡ ውልና ስምምነት ላለመሰረዛቸውና ላለመተዋቸው ምንም ማስተማመኛ ተዓምር የለም፡፡

የኃይል ዕርምጃው ለግብፅም ሆነ ለሱዳን የሚያስከትለው ውጤት ኪሳራ ከሆነና ከአማራጭ ውጭ ከተደረገ፣ በጋራ ለዕድገት እንድንጠቀም በሰላም አብሮ መሥራትና የውኃውን ፍሰት የሚጨምሩ በሁሉም የተፋሰስ አገሮች የተደገፉ ፕሮጀክቶች መቅረፅ ያስፈልጋል፡፡ ይህም በድርቅ እየተራቆቱ ያሉትን የኢትዮጵያ ተራሮች በደን መልሶ መሸፈን ማለት ነው፡፡ ከዚያም ተፈጥሮ የራሱን ሥራ እንዲሠራ ማድረግ፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥትም ሆነ ሕዝብ ወደ ሱዳንም ሆነ ወደ ግብፅ ሊሄድ የሚችለው ውኃ ከሚቀንሰው ይልቅ በኢትዮጵያ ላይ የሚከሰተውን የደን ውድመትና በዚህ ምክንያት የሚደርሰው ድርቅ የበለጠ በውኃው መቀነስ ላይ ተፅዕኖ ይኖረዋል፡፡ ስለሆነም ግብፅም ሆነች ሱዳን ኢትዮጵያ በደን እንድትሸፈን በጀት መመደብና መርዳት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህም ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ የሚያደርጉት እንጂ ለኢትዮጵያ ችሮታ አይደለም፡፡ በደን መራቆት ምክንያት ዓባይንና ተከዜን የሚገብሩት ገባር ወንዞች እየተዳከሙ ነው፡፡ ይዘውላቸው ሊሄዱ የሚችሉት ለም አፈርም እየተመናመነ ነው፡፡ ከአሁኑ ካልተሠራበት ለወደፊትም እየከፋ ነው የሚሄደው፡፡

ኢትዮጵያም አሁን ካለው የደን ተከላ የአንድ ሰሞን የዘመቻ አሠራር ወጥታ ቀጣይና ተከታታይ ያለው አሠራር መንደፍ አለባት እላለሁ፡፡ ለዚህ ዓይነት አሠራር ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የነበሩት ፍራክሊን ዲ ሩዝቬልት ያቋቋሙት አገራቸውንና ሕዝባቸውን ከታላቁ የኢኮኖሚ ድቀት (Great Depression) ለማውጣትና ለመታደግ ከነደፉዋቸው ፕሮግራሞች አንዱ ሥራ በመፍጠርና አካባቢን መልሶ በማገገም ትልቅ ሚና የተጫወተው  (Civilian Conservation Corps) ነው፡፡ ፕሮግራሙ በደን ውድመት ተራቁታ የነበረችውን አሜሪካ ታድጓታል፡፡ እስከ 90 በመቶ ደን ወድሞባቸው የነበሩ የአሜሪካ ግዛቶች ዛሬ አረንጓዴ የሆኑት በዚህ ፕሮግራም አማካይነት ነው፡፡ ፕሮግራሙ በመቶ ሺዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች ሥራ ፈጥሮ ነበር፡፡

ለእኛም አገር እንዲህ ዓይነት ፕሮግራም ቢቀረፅ ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ በመቶ ሺዎች ለሚቆጠሩ ዜጎቻችን በተለይም ለጎዳና ተዳዳሪዎች ዜጎቻችን ሥራ ሊፈጥር ይችላል፡፡ አገራችንም ልምላሜዋን እንደገና እንድታገኝ፣ የዱር አራዊቶችም መጠለያ እንዲኖራቸው፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ በቂ ዝናብ እንዲኖረን ይረዳናል፡፡ ለአየር መዛባት መቀነስ የበኩላችንን አስተዋጽኦ እናደርጋለን፡፡ ከዚህ ውጭ ደግሞ የዓባይ ተፋሰስ አገሮች በተለይ ግብፅና ሱዳን ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ ደኑን እንዲሸፍኑ ማስረዳትና ማግባባት ያስፈልጋል፡፡ የዓለም አየር ሙቀት መጨመር የሚያሳስባቸውም ፕሮግራሙን በገንዘብ እንዲደግፉት ማድረግ ይቻላል፡፡

ይህን ፕሮግራም ግብፆች እንዲደግፉት ግን ሌላኛው አማራጫቸው ማለትም በኃይል የኢትዮጵያን ግድብ ለማፍረስ መሞከር የበለጠ ኪሳራ እንደሚያመጣ፣ የአስቀድሞ መከላከል ወይም ለሚያደርሱት ጥፋት የበለጠ ጥቃት እንደሚገጥማቸው ሲገነዘቡ ነው እላለሁ፡፡

ከ’ራስ ክህደት እስከ ሀገር ማፍረስ…..


 ከ’ራስ ክህደት እስከ ሀገር ማፍረስ…..
በመጀመሪያ ‘ራሳቸውን ከዱ፣ ከዚያም በጥላቻ ታውሩ፣ ከዚያም ኢትዮጵያዊነትን ኢትዮጵያን አምርረው ጠሉ፣ ከዚያም በታሪካዊ ጠላቶቻችን እየተመሩና እየታገዙ፣ የገንዛ ወገናቸውን ‘ርስ-በ’ርስ እያበጣበጡና እያለያዩ፣ ኢትዮጵያን እያፈራረሱ፣ ለባዕዳንና ለታሪካዊ ጠላቶቻችን እየቸበቸቡ አሁን ካሉበት ደረጃ ደረሱ። ወያኔ/ኢሕአዴጎች።
የተከበሩት ኔልሰን መንዴላ እንዲህ ይሉናል ”….. ፍቅር አብሮን የተወለደ በተፈጥሮ ያገኘነው ነው። ጥላቻ ግን በትምህርት ያገኘነው ነው። ስለዚህ ጥላቻን በትምህርት ልናስወግደው እንችላለን።….”። ግን በ’ኛ ሀገር ለወያኔ ገዥዎቻችን ጥላቻና ክህደት አብሮ’ቸው የተፈጠረ ይመስላል። ያለፈው አልበቃቸው ብሎ አሁንም የጥላቻንና የዘረኝነትን መርዝ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ በህዝብ ላይ ይረጫሉ። ”ለምን?..” ያለውን ደግሞ ያስራሉ፣ ያሳድዳሉ፣ ይዘርፋሉ፣ ይገላሉ፣ ያስገድላሉ። እንደ’ነሱ ጠበንና አንሰን፣ ሀገራዊነትን አውግዘን፣ ስብእናችን ሁሉ ”ጎጠኝነት” አንዲሆን ሌት ተቀን ይደክማሉ። ለመሆኑ ከዘመናት በፊት ”ዘሬ የሰው ልጅ ነው፤ ሀገሬም ዓለም ነው።” ያለው ደራሲ (ስሙን ማስታወስ ስላልቻልኩ ይቅርታ።) በዚህ ዘመን ወያኔወችን እጅ ቢጥለው ምን ይል ይሆን? እነሱስ ምን ያደርጉት ይሆን?
በቅርቡ የወያኔው ”የበኩር አባት” አቶ ስብሐት ነጋ ”….. ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተሾመው ኢሕአዴግ ዱሮም አስቦበት ወንበሩን ከአማራና ከኦርቶዶክስ አማኞች ለማጽዳት በተዘጋጀበት እቅድ ነበር……..” ሲሉ ተሰምተውል። ይህ በ’ርግጥ የለመደነው ክህደትና ሸፍጥ ነው። ታዲያ አኒህ ሰው ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊያን ያላቸው ጥላቻ ይበልጥ በሽበታቸው ዘመን ስር እየሰደደና እየተባባሰ መምጣቱን ያሳያል። ብዙውን ግዜ በሌሎች ላይ ጥላቻ ያለባቸው ሰዎች ለራሳቸው ከሚሰማቸው የበታቸነት ስሜት የሚመጣ ሲሆን መድረኩንና አጋጣሚወን ሲያገኙ ደግሞ እንደወያኔ ሀገረንና ህዝብን ከማዋረድና ይዘው ከመጥፋት ወደ ኋላ አይሉም።
የአቶ ስብሐት የክህደትና የጥላቻ የበኩር ልጃቸው የሆነው አቶ መለስ ዜናዊ ኢትዮጵያን አፍርሶና ሕዝቦቿ ‘ርስ-በርስ አባልቶ ሳይጨርስና ሳይሳካለት ወደ ማይመለስበት ስለሄደ፤ እሱ ያላያትን ”የፈራረሰች ኢትዮጵያን” እሳቸው ለማየት ካላቸው ጉጉት አንጻር የሚያደርጉትን አ’ተው ግራ ተጋብተዋል። ምክንያቱም ”ታላቋን ትግራይ” የመመስረት “ቅዥት”፣ “ቅዥት” ሆኖ እንደቀረ ሁሉ፣ ኢትዮጵያን የማፈራረሱም እኩይ ምግባራቸው ደግሞ ‘’ቅዥት’’ ሆኖ ሊቀር መሆኑ እንቅልፍ ነስቷቸዋል።
ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን ይ’ች ዓለማችን አስከ አለች ድረስ እንኖራለን። ይህ ሚሊዮን ግዜ ተነግሮ’ል። መነገር ብቻ ሳይሆን እውነተኛ ዜጎቿ መሰዋአትነት ሲከፍሉበት ኑረዋል፤ አሁንም የተፈለገውን ያህል ውጤት ባያመጣም እየከፈሉ ይገኛሉ። ግን የወያኔ ገዥዎች ከልጅነታቸው እስክዚች ሰዓት ድራስ አእምሮ’ቸው በጥላቻና በተንኮል አድጎ፣ በክህደትና በዘረኝነት ጎልምሶ፣ ከሀገራችን ጠላቶች ጋር በማበር የኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን የማጥፋት እኩይ ዓላማ፣ በሽበት ዘመናቸውም ሆነ ”በትምህርት” ሊወገድ አልቻለም። አቶ መለስ ከነ ጥላቻቸውና ከነ ዘረኝነታቸው ሄደውል። ቀሪዎቹ እነ አቶ ስብሐት ደግሞ ”ሌባ ላመሉ ዳቦ ይልሳል!” እንዲሉ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝን እንደ ምክንያት እያደረጉ ያመላቸውን “ዳቦ ይልሳሉ”።
የአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ለጠ/ሚኒስተር ስልጣን መድረስ ዋናው ምክንያት እንደሚከተለው ነው፤….
1/አቶ መለስ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝን ምክትል ጠ/ሚኒስተር ያደረጓቸው ኦሮሞና አማራ ነኝ ባይ ተለጣፊዎን ለማራቅ ነበር። ምክንያቱም በውቅቱ ሁለቱም ተለጣፊዎች የምክትልነቱ ቦታ ይገባናል በማለት ”ከሚስቶቻቸው” ጋር አልጋ ላይ ያንሾካሹኩ ስለነበር ነው። ታዲያ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ከደቡቡ ተለጣፊ ቡድን በመሆናቸው እንደ መፍትሄ የተውሰደ ነው።
2/ አቶ ሃይለማርያም ወያኔን ”እንድ ግል አዳኛቸው” የተቀበሉ በመሆናቸውና አቶ መለስ የተናገሩትን መልሰው እንደ በቀቅን የሚያስተጋቡ ከመሆናቸው በተጨማሪ፤ ምንም አይነት ችግር የማይፈጥሩ ”ተነጅ” መሆናቸውተ ሌላው ምክንያት ነበር። አሁንም ”የመለስ ራእይ” እያሉ እየደነፉብን ነው። ለነገሩ የ’ራሱ ራዕይ ያለው ሰው ከመጀመሪያውም ወያኔ አይሆንም ነበር።
3/ ከአቶ መለስ ሞት በኃላ እነ አቶ ስብሐት አቶ ሃይለማርያምን ጠ/ሚኒስተር ለማድራግ ማቀድ ቀርቶ አልመውተም አያውቁም ነበር። የጠ/ሚኒስተርነቱን ቦታ ለወያኔ ተወላጅ ”ተገዳላይ” ለመስጠት ያልፈነቀሉት ድንጋይ አልነበረም። ነገር ግን የ’ርስ በርስ ሽኩቻው የወያኔን ህልውና እስከመፈታተን ደረሰ። ታዲያ እነ አቶ ስብሐት ”’ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተሾመው ኢሕአዴግ ዱሮም አስቦበት ነው…” ማለታቸውን ስሰማ በልጅነቴ የሰማሁትን ተረት አስታወሱኝ። ተረቱ እንዲህ ነው፤……ሁለት አብረው የሚኖሩ ወንድና ሴት ፍዬሎች ነበሩ። አንድ ቀን ውንድዬው ፍዬል የወይን ዛፍ አየና ወደ ዛፏ አመራ። የወይኑን ፍሬ ለመብላት ቢሞክር ሊደርስበት አልቻለም። እናም ‘ራቅ ብሎ ሄዶ ጋደም አለ። ሴቷ ፍዬል በተረዋ ወደ ወይኗ ዛፍ አዘገመች። የወይን ፍሬውን ለምብላትም ሞከረች። ግን አልቻለችም። ወደላይ ዘለለች። አልቻለችም። የፊት እግሮቿን ተጠቅማ ወደ ወይን ፍሬው ለመድረስ ሞከረች። አልቻለችም። ምንም ማድረግ እንደማትችል ስታውቅ ምራቋን እየዋጠች ወደ ጓደኛዋ ሄደች። እሱም ከርቀት ይከታተላት ነበርና ” እንዴት ነው የወይኑ ፍሬ?” ሲል ጠየቃት። ” እባክህ… ልበላ ፈልጌ ስቀምሰው የወይኑ ፍሬ ይመራል።” አለችው። እሱም ” አይ ያንች ነገር!….. ዘለሽ ..ዘለሽ ሲያቅትሽ ይመራል ትያለሽ።” በማለት መለሰላት። ታዲያ ዛሬ ወያኔዎች ”ዘለው..ዘለው… ሲያቅታቸው፣ የተሻለ ነገር መናገር አይችሉምና “ስልጣኑን ከአማራና ከኦርቶዶክስ ለማጽዳት ነው…” ማለት ሳይብቃቸው ‘’የኢትዮጵያ ህዝብ ለዲሞክራሲ የበቃ አይደለም።” በማለት መዘላበዱን ተያያዙት።
3/ ወያኔዎች አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ሳይፈልጉ ጠ/ሚኒስተር መሆናቸውን አማራጭ አጥተው ሲቀበሉ በ’ርግጥ ቢሳካላቸውም ባይሳካላቸውም ሁለት ነገሮችን እሳቤ ውስጥ አስገብተዋል፤
- የመጀምሪያው ጠ/ ሚኒስሩን ለዚህ ስልጣን የበቁት ባላቸው አፍቅሮ ወያኔ ስለሆነ፤ ከወያኔዎች ፈቃድ ውጭ ምንም የሚያደርጉት ነገር እንደሌለና ላድርግ ቢሉ እንኳ’ በቀላሉ ማስወገድ እንደሚችሉ ስለአመኑ።
- ሁለኛው እስከ ሚቀጥለው ምርጫ ድረስ የ’ርስ በርስ ሽኩቻዎችን ስለሚያስወግዱ ጠ/ ሚኒስሩን እንደ ግዜ መግዥ ሊጠቀሙባቸው በማሰብና በማቀድ ነው።
4/ ሌላው ደግሞ የአቶ መለስ ሞት ያስደነገጣቸው ገዥዎቻችን ግራ ሲገባቸው፤ በሁለት እግራቸው የቆሙ ለመምሰልና ሁሉም ነገር በ’ነሱ ቀጥጥር ስር መሆኑን ለማሳየት ሲሆን፤ የተለመደው አሳፋሪ ፓለቲካ ግን ወያኔ ተወልዶ ያደገበትን የኢትዮጵያን ጥላቻና እርስ-በ’ርስ ህዝብን የማባላት እኩይ የተለመደ ምግባር ለመግለጽ የታሰበ ነው። ክቡር ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም “አቶ ስብሐተና የተነኮል ፓለቲካ” በሚል ርዕስ እንደገለጹት “…..አነጋገሩ በሁለት በኩል ስለት ያለው ቂል የያዘው ሰይፍ ነው።….” ግን ፕሮፌሰር ይህ ስለት ያለው ቂል የያዘው ሰይፍ ላለፉት ዓመታት ወግቶናል! ቆርጦናል! ከፋፍሎናል! አሁንም በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊነት ላይ የተሳለው የቂል ሰይፍ መገዝገዙን ለማስቀጠል ደፋ-ቀና እየተባለ ነው።
ወያኔዎች ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን የማፈራረሱና ትውልድን የማጥፋቱ እኩይ ምግባር ሙሉ በሙሉ አለመሳካቱን ከቀንደኛ መሪያቸው ሞት በኋላ እንኳ’ ለራሳቸው ሲሉ ካለፈው ለመማርም ሆነ ለመጸጸት አለማሰባቸው ፕሮፌሰር እንደሚሉት ”ያሳዝናል” ተብሎ የሚታለፍ ሳይሆን፤ ሀገራችን ለማጥፋትና ለማውደም፤ አስፈላጊ ከሆነም ህዝብን ከመጨረስ በምንም አይነት መንገድ ወደ ኋላ እንደማይሉ ነው ደጋግመው እየነገሩንና እያሰረዱን ያሉት። ይሁን እንጅ ትላንት ዛሬ አይደልም፤ ዛሬም ነገ አይደለም።
…….ይዘገያል እንጅ ታሪክ ውል አይስተም
በሰፈሩት ቁና መሰፈር አይቀርም።……
ምንም ይበሉ ምን፣ ወያኔዎችና ተከታዮቻቸው እየመረራቸውም ቢሆን መዋጥ ያለባቸው ሀቅ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ከየትም ጎሳ ይምጡ፣ ምንም አይነት ሀይማኖት ይኑራቸው፣ ኢትዮጵያዊ አስከሆኑ ድረስ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ የግል ማንነታቸውን ጥያቄ ውስጥ አያስገባውም። መግባትም ሆነ መታሰብም የለበትም። ኢትዮጵያዊነታቸው ከምንም በላይ በቂ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ጥያቄ ብሄራዊ ጥቅማችን ያስጥብቃሉ ወይ? መብታችንና ነጻነታችን ያከብራሉ ወይ? በአጠቃላይ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊያን ክብርና ልዕና መሉ ስልጣናቸውን (በህዝብ ያለተመረጡ ቢሆንም) ተጠቅመውና ሕግን አክብረው ይሰራሉ ወይ? ከወያኒያዊ አመለካከት የጻዳ አስተዳድር ይመሰርታሉ ወይ? በሚለው ላይ ነው ህዝብ ማውገዝም፣ ማወደስና መታገል የሚፈልገው። በ’ርግጥ እስከ አሁን ድረስ እንደታዘብነው ሰውየው ገና ”ከተገዥነትና ከተነጅንት’’ ያለመውጣታቸውን እያረጋገጡ ነው። የ’ኛም ትግል ይቀጥላል።
————-//——-

አሸባሪ ETV ነው !!! አሸባሪ ETV ነው !!!ETV ሌባ !!!

አሸባሪ ETV ነው !!! አሸባሪ ETV ነው !!!አሸባሪ ETV ነው !!!ETV ሌባ !!!ETV ሌባ !!!ETV ሌባ !!!
http://www.youtube.com/watch?v=NhiVVTqAVyk&feature=player_embedded

አልፎ አልፎ ጠዋት የማገኛቸው የማኪያቶ ቡድን አለ፡፡ በፓርላማ ሰለነበረው ውሎ መሠረት አድርገው የግል አሰተያየት ይሰጣሉ በዚህ መሃል አንዱ ምሳሌያዊ ንግግር አደረገ ወደድኩትና ላካፍላችሁ ወደድኩ፡፡ ቁራ ታውቃላችሁ በተለይ መሬት ላይ በእግሯ ስትሄድ አታምርም ይህ ችግር እንዳለባት ታውቃለች፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የእርግብ አካሄድ ይማለርካታል፡፡ አካሄዷን ለማሳመር እንደ እርግብ መሄድ ይኖርብኛል ብላ ወሰነችና ልምምድ ጀመረች፡፡ አስር ዓመት ሙሉ ቤት ዘግታ ስትለማመድ ቆይታ ሳይሳካላት ይቀርና ተስፋ በመቁረጥ አንድ ውሣኔ ላይ ትደርሳለች ቢያስጠላም በራሷ በቀድሞ አካሄድ እንደ ቁራ ለመሄድት ወስናለች፡፡የሚያሳዝነው ነገር ግን የእርግብንም ሳትለምድ የራሷም የቁራ አካሄድ ጠፋባት፡፡
የዚህ ምሳሌ መነሻ የሆኑት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማሪያም ደሳለኝ ናቸው፡፡ በምክር ቤት ውስጥ የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ለመምሰል ሲያደርጉ የነበረውን ሙከራ የትዝብቱ አንድ አካል ነው፡፡ በዚህ ዕይታ ሙሉ በሙሉ ባልስማማም ፍፁም ውሽት ነው ራሳቸውን ነበር የነበሩት ብዬ ልከራከር አልችልም፡፡ እኔም የሆነ ነገር ታይቶኛል፡፡ ስለዚህ ይህ ማሳሰቢያው አቶ ሀይለማሪያም መለስን ላይሆኑ ሀይለማሪያምን እንዳያጡት የተሰጠ ምክር በመሆኑ በበጎ ወስጀዋለሁ፡፡
የተከበሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማሪያም ደሳለኝ በደንብ በሚያውቁት አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ላስረዳ፡፡ መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ ምዕራፍ 17 ዝርዝሩን ማየት ይቻላል በአጭሩ ታሪኩ የጎሊያድና የዳዊት ነው፡፡ ንጉስ ሳኦል ዳዊት ጎልያድን ለመግጠም ይመረጥና ይልከዋል ወደ ፍልሚያው ሊገባ ሲል፤ ሳኦል ለዳዊት እንዲጠቅመው በሚል የንጉሱን ካባና ንጉሱ በጦርነት ጊዜ የሚጠቀምበትን ዋነኛ መዋጊያ የሆነ የናስ ቁር ደፋለት፤ ጥሩርም አለበ ሰው፡፡ የንጉሱን ልብስ ለብሶ መንገድ ሲጀምር አልተመቸውም አውልቁልኝ ብሎ አወለቀው፤ በማስከተልም የተሰጠውን ትጥቅ ይቅርብኝ ብሎ ወንጭፌን አምጡ አለ፡፡ ከዚያም ብዙዎቹ በዚህ አለባበስና በወንጭፍ እንዴት ጎልያድን የሚያክል ግዙፍ ሰው ለማሸነፍ እንደሚችል ሲጠየቅ ጎልያድ እንደምታዩት ትልቅ ነው (የጎልያድ ቁመት ከስድስት ክንድ በላይ ነው) ለኔ ጎልያድን መምታት ሳይሆን መሳት ነው ከባድ ይላቸዋል፡፡ ግጥሚያው ሲጀመርም ዳዊት ጎልያድን በወንጭፍ ግንባሩን ብሎ ጣለው፡፡ እንዳለውም ጎልያድን መምታት ሳይሆን ከባድ መሳት ከባድ መሆኑን አስመሰከረ፡፡ ዳዊት ያደረገው ከንጉሱ ካባ ይልቅ የራሱ ደበሎ፤ ከንጉሱ ዘመናዊ መሳሪያ ይልቅ የራሱ የሚያውቀው ወንጭፍ እንደሚሻል አሰመሰከረ፡፡ እዚህ ጋ ለአቶ ሀይለማሪያም የተላለፈው መልዕክት የንጉሱ ሌጋሲ ማስጠበቅ በሚል ሳይሆን በራሳቸው ደበሎና ወንጭፍ እንዲጠቀሙ ለማሳሰብ ነው፡፡
እነዚህ ሁለት ምሳሌዎች ለአቶ ሀይለማሪያም በጣም ጥሩምሳሌዎች ናቸው፡፡ ምርጫው እንደ ቁራዋ ሌላ ለመሆን ሞክሮ እራሳቸውንም መሆን አቅቶዋቸው ሳይሳከላቸው መቅረት ወይም እንደ ዳዊት የንጉሱን ትተው እራሳቸውን መሆን ነው፡፡ ምርጫው የግል ነው የኛ ጉዳይ መምከር ነው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ እራሳቸውን እንዲሆኑ የምፈልግበት አንድ ሁለት ነጥብ ላንሳላችሁ አንድ የፕሬስ ህግ የመናገርና ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት የንግድ ህግ መሆኑን አናውቅም ነበር፡፡ እነዚህ ድንጋጌዎች በንግድ ህግ ብቻ የሚጠቀሱ ቢሆን ኖሮ በፍትሕ ብሔር ህግ እንጂ በህገመንግስት ውስጥ የሚጠቀሱ አይሆኑም ነበር፡፡ የህገ መንግሰቱን አንቀፅ 29/2 እና ሌሎችም ድንጋጌዎች እንዳይሸራረፉ መጠየቅ በንግድ ህግ እንዲታይ ማለት ተገቢ አይደለም፡፡
ነጋዴዎች የያዙትን የንግድ ቤት በሽያጭ ይተላለፍ የሚል አስተያየት ሲሰጥ ይህ ዓላማው ድሃው እንዲኖርበት ነው ማለት የእውቀት ሳይሆን ጉዳዩ ሌላ ነው ፣ ድሃው የሚኖርበት ቤትም ቢሆን ለድሃ በይዞታነት ይተላለፍ ማለት ይቻላል፡፡ በጥያቄ የቀረበላቸው ግን ነጋዴዎች እየነገዱ ያሉበትን ቤት ባለቤትነት አዛውሩና ገንዘብ ተቀበሉ፡፡ የተቀበላችሁን ገንዘብ ደግሞ ለኢንቨስትመንት አውሉት ማለት ለወዳጅ የተሰጠ ምክር ነው፡፡ ልብ ብለው ያድምጡኝ ይህ ምክር ከተቀናቃኝም ቢሆን ሊታሰብበት የሚገባ ነው፡፡ ለነገሩ ዓላማው እራሱን ችሎ የሚኖር ነጋዴንም ቢሆን በጭሰኝነት መያዝ እንደሆነ ያስታውቃል፡፡ ለነፃነት ስንል ጫካ ገባን የሚል ቡድን የዜጎቸን ነፃነትን ለመገደብ ምንም መንገድ እንደሚጠቀም ማሳያነው፡፡ ይህ ደግሞ ጫካ የመግባታቸው ሚስጥር ለነፃነት ነበር የሚለው ነጭ ውሽት እንደሆነ መረዳት ከበድ አይሆንም፡፡ ነፃነትን የሚያከብር ቡድን በምንም ዓይነት የሌሎችን ነፃነት በቁሳዊ ጉደይ ለመያዝ አይጥርም፡፡ ነፃነት የማያውቅ ነፃ አውጭ የሚለው የሚገልፃችሁ ይመስለኛል፡፡
[email protected]
http://www.abugidainfo.com/amharic/index.php/10119
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማሪያም ደሳለኝ ከቁራና ከዳዊት የቱን ይመርጣሉ? ግርማ ሠይፉ ማሩ

“ለኦርቶዶክስ ወይም ለአማራ ብቻ ተወስኖ የቆውን የኢትዮጵያ መንገስታዊ ስልጣን ለተጨቆነው ህዝብ አስረከብነው” ስብሃት ነጋ፣ በፓልቶክ ክፍል ተጋብዞ ባደረገው ንግግር

 

ስብሃት ነጋ፣ በፓልቶክ ክፍል ተጋብዞ ባደረገው ንግግር፣ “ለኦርቶዶክስ ወይም ለአማራ ብቻ ተወስኖ የቆውን የኢትዮጵያ መንገስታዊ ስልጣን ለተጨቆነው ህዝብ አስረከብነው” ማለቱን አንድ ጓደኛዬ ነገረኝ። ይህን የነገረኝ ጓደኛዬ በስብሃት ንግግር በጣም ተገርሞ ስለነበር፣ “አታስብ! ስብሃት አብሻቂ የንግግር ጠባይ አለው።” ስል ጠቆምኩት። ለነገሩ በሚናገረው ባልስማማም፣ ስብሃት ያመነበትን እንደወረደ ስለሚያፈርጠው ከሌሎቹ እሱ ይሻለኛል። “በዚህች አለም ላይ መጥፎም ይሁን ጥሩ ያመንክበትን ፈፅመህና የልብህን ተናግረህ ማረፍን የመሰለ እርካታ የለም” ይል ነበር መለስ ዜናዊ - ነፍሱን ይማረውና።


ስብሃት ነጋ በርካታ ዝነኛ ያልሆኑ አባባሎች አሉት። ለመጥቀስ ያህል፣ “… ትግሬዎችን ወደመጡበት እንመልሳቸዋለን” የተባለችው የበድሩ አደም ነጠላ ዜማ የተለለቀቀች ሰሞን፣ ስብሃት እንዲህ ሲል መልስ ሰጥቶአል፣ “… እኛ ወደመጣንበት ስንባረር፣ መንዜዎችን ሰሜን ሸዋ አራግፈን ነው የምናልፈው!”

ርግጥ ነው፣ አቦይ ስብሃት ከአማራው ኤሊት ጋር አንድ ችግር ያለበት ይመስላል። ከመንዝ ኦርቶዶክስ የፈለቁት መሪዎች፣ የምኒልክን ቤተመንግስት “ለሰፊው ህዝብ” አስረክበው ከስልጣኑ ገለል ካሉ 40 አመታት ሞልቶአቸዋልና ዛሬ ስማቸውን ማንሳት ተገቢ አልነበረም። ዳሩ ግን ከብሽሽቁ እና ከእልሁ በስተጀርባ ያለው ፖለቲካዊ ይዘት ከቶ ምንድነው?

ኮሎኔል መንግስቱ በርግጥ በእናቱ የሸዋ አማራ ነው። እንደ ህወሓት ሰዎች አባባል ኮሎኔሉ የአማራው ገዢ መደብ አገልጋይ የነበረ ነው። ይሄ በራሱ አከራካሪ ነው። ኮሎኔል መንግስቱንም ሆነ መለስ ዜናዊን የኦርቶዶክስ ኃይማኖት ተከታዮች ማለትም አይቻልም። ሁለቱም ኢ-አማኒ ነበሩ። እና የስብሃት፣ “ከአማራ እና ከኦርቶዶክስ” አባበል ለምን መጣ?

የስብሃትን አባባል ተከትሎ ለኃይለማርያም፣ “ፀረ-ማርያም” እና፣ “ፀረ-አማራ” የተባሉ ቅፅሎች እየተሰጡት ነው። በሶሺያል ሚዲያዎች እና በድረገፆች ጭምር የኃይለማርያም መናፍቅ መሆን እየተሰበከ ይገኛል። በእግረመንገድ ምክትሉ ደመቀ መኮንን እስላም መሆኑ እየተጠቀሰ፣ “የጎንደርን መሬት ለሱዳን የሸጠ” የሚል ካባ ይመረቅለታል። ዋናው የጥቃት ኢላማ ከሆነው ኃይለማርያም ላይ የሚወረወሩት ቦምቦች በአብዛኛው ውሸት ናቸው። ለአብነት ኃይለማርያም ሶስት ጊዜ ኃይማኖት ስለመለዋወጡ የሚፃፈው እውነት አይደለም።

ኃይለማርያም በጴንጤነቱ እና በወላይታነቱ ምክንያት በአማሮች የደረሰበት በደል እንደ መወያያ አጀንዳ ሆኖ ጠረጴዛ ላይ ወድቆአል። እንደ ዘገባው ኃይለማርያም የወያኔ አባል ለመሆን ፍላጎት ያደረበት፣ በዘረኛነት ምክንያት እድል የነፈጉትን አማራ ግለሰቦች ለመበቀል ሲል ነበር። ባለቤት አልባው መጣጥፍ እንደሚጠቅመው ኃይለማርያም ወደፊት “በፀረ-አማራነት አቋሙ” ሊገፋበት ይችላል?

ለመሆኑ እንዲህ ያሉ ያልተረጋገጡ መረጃዎችን የሚለቀው ማነው?

ለምን አላማ?

በርግጥ ኃይለማርያም ፀረ-አማራ አቋም አለው?

ጽሑፎቹ፣ “ትምክህተኞች” በግዴለሽነት የሚበትኗቸው ናቸው ወይስ ህወሓት ሆን ብሎ ለአላማው የሚያሰራጨው? መረጃ ስለሌለኝ አላውቅም። ይህን በመሰሉ ቅስቀሳዎች ግን ወያኔ ይበልጥ ተጠቃሚ ሊሆን እንደሚችል ማሳመን ይቻላል።

የህወሓት ሰዎች ኃይለማርያምን በመሪነት ሲያስቀምጡ፣ ለጊዜው አማራጭ ስለሌላቸው እንጂ፣ ልባቸው ፈቅዶት አይደለም። ብአዴን የተባለውን የስልጣን ተፎካካሪ፣ ገለል ለማድረግ ግን የኃይለማርያምን ሹመት ከማፅደቅ የተሻለ አማራጭ አልነበራቸውም። እንዲህም ሆኖ የብአዴን እና የህወሓት የውስጥ ሽኩቻ ገና መፍትሄ አላገኘም። የብአዴን ሰዎች እንደ መድሃኒት ቤቱ የእባብ አርማ፣ ኃይለማርያም ላይ ተጠምጥመውበታል። ኤልያስ ክፍሌ የጀመረው፣ “ለኃይለማርያም እድል እንስጠው!” ዝንባሌም ለህወሓት አሳሳቢና ራስ ምታት ሊሆን እንደሚችል ማመን ይቻላል። ምክንያቱም ኃይለማርያምን እንደ አባዱላ ጠፍጥፈው እንዳልሰሩት ያውቃሉ። ያነበበ፣ በማንበብ ላይ ያለ እና የተማረ ሰው ነው። የተማረና ያነበበ መሆኑ፣ ብቁ የፖለቲካ መሪ ሊያደርገው ባይችልም፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ቢሮ ሲለማመደው አንጎሉን መጠቀም ሊጀምር ይችላል ብለው ይሰጋሉ። ከኃይለማርያም ሹመት በፊት ተጣድፈው ጄኔራሎቹን መሾማቸው ለዚህ አባባል አንድ ጠቋሚ ምልክት ነው። ኃይለማርያም ከምእራባውያን እና ከህዝብ በሚያገኘው ድጋፍ፣ አሻንጉሊት ላለመሆን ድፍረት ሊሆነውም ይችላል። ኃይለማርያም አንድ ደካማ ግለሰብ ቢሆንም፣ የገባበት ቢሮ ኃይል ሆኖ ሊያበረታው ይችላል። የህወሓት ሰዎች ይህን ያውቃሉ፣ ይህንንም ይገምታሉ።

ከኃይለማርያም በኩል ያጋጥመናል ብለው ከሚሰጉት ነገር ዋናው፣ ከብአዴን ወይም ከተቃዋሚዎች፣ (በተለይ ከአማራ ተቃዋሚዎች) ጋር የአላማ አንድነት ከመሰረተ ህወሓትን ማንሳፈፍ የመቻሉ እውነት ነው። ከወዲሁ ኃይለማርያምን ከአማሮችና ከኦርቶዶክሶች ማጋጨት ይህን አደጋ ይቀንሰው ይሆን? በትክክል ይመስላል። ለኃይለማርያም፣ “ፀረ-አማራ” እና “ፀረ-ኦርቶዶክስ” የተባሉ ቅፅሎችን የመለጠፉ ዘመቻ በማን እንደተጀመረ ባይታወቅም፣ አንድ ስሙን ያልጠቀሰ፣ “የኃይለማርያም ተማሪ ነበርኩ” ባይ ግለሰብ ግን መርዝ የተቀቡ ከረሜላዎችን በነፃ ሲያድል ሰንብቶአል። ይህን ጽሑፍ በመቃወም በጎ አስተዋፅኦ ለማድረግ የሞከረው ዶክተር አባቡ ተክለማርያም ምስጋና ያስፈልገዋል። ከምስጋና ይልቅ ግን፣ “አድርባይ” የተባለ ርግማን ሲወርድበት ነበር የሰነበተው።

እንግዲህ ብእሮች ኃይለማርያም ላይ ማነጣጠራቸው ግድ ነው። ኃይለማርያምን ከፀረ-ማርያምነት እስከ ፀረ-አማራነት ፈርጀነዋል። ከአሻንጉሊትነት እስከ አምባገነንነት መድበነዋል። ከየዋህነቱ እስከ መሰሪነቱ ልቡን እየቆፈርን ተንትነናል። ከጭንቀታምነቱ እስከ ኮስታራነቱ፣ እንደ ሞተር በትነን ገጥመነዋል። ኃይለማርያም ማን መሆኑ እስኪረጋገጥ፣ ወይም ኤልያስ ክፍሌ አጥብቆ እንደጠየቀው፣ “ኃይለማርያም አቋሙን ግልፅ እስኪያደርግ” ግምታዊ ሙገሳ እና ውንጀላው በዚህ መንገድ ለጥቂት ሳምንታት መቀጠሉ ግድ ነው።

ማርያም Mariamተስፋዬ ገብረአብ

Internal feud dismantling EPRDF

Yuri Vladimirovich Andropov was in charge of KGB before he became President of the defunct Union of the Soviet Socialist Republics (USSR) and General Secretary of the Central Committee of the Communist Party of the Soviet Union (CPSU) on 12 November 1982 following the death of Leonid Brezhnev whose era (1964 – 1982) of economic growth nearly came to a standstill due to lack of reforms. His successor Andropov was reported as saying that comrades candidly backbite the shortcomings of CPSU without fear as long as their number is not more than two but otherwise compete in glorifying the Party unanimously in official meetings comprising more than two participants. Is it not true?!

Andropov died on 09 February 1984 after only 15 months in office and the moment of truth came up when internal feud crushed and dismantled the monolithic Central Communist Party and mammoth clumsy government state machinery under the omnipresent tight control of the Party. This is in sharp contrast to cases in a democratic society where individuals are free to voice their free opinion without fear and changes of regimes take place in orderly manner through the verdict of the people casting their votes at the polls.

As a copycat of the Brezhnev era and Stalin-style grip on power, ultimate demise of the exclusive misrule Zenawi’s was never in doubt just like that of his predecessor Mengistu Hailemariam who was advised by Brezhnev himself to follow a policy of mixed economy to be implemented by an inclusive government with broad base.

The powerhouse of EPRDF built according to Stalin’s design is replete with mistrust instilled in it by its architect the late pathological liar. Therefore it would be naïve to expect the new Prime Minister (PM) as an accomplice to the heinous crimes of his former boss to denounce in his acceptance speech the destructive policy of the EPRDF of which he was one of the architects. He didn’t even mention God in taking oath of office.

Champions of liberty freedom and human dignity

The following fall in the category of outstanding individuals, with vision and exceptional acumen of great leaders rallying others with similar vision for the purpose of ending tyranny:-

1.Abraham Lincoln: One of the greatest statesmen in the world known for gallantly leading his divided nation locked in a bloody civil war that culminated in the abolition of slavery in the United States of America. From his famous Gettysburg Address commemorating fallen heroes we often quote: “… that this nation, under God, shall have a new birth of freedom—and that government of the people, by the people, for the people, shall not perish from the earth. He underscored the bedrock principle according to which the USA was founded, thus: “Four score and seven years ago our fathers brought forth on this continent a new nation, conceived in liberty, and dedicated to the proposition that all men are created equal.” Note: Quotes are from the famous President’s Address made on 19 November 1863 (Gettysburg, Pennsylvania).

2.Emperor Menilik II: The victor of the famous Battle of Adwa that beacon of hope of the black people in the Diaspora; a truly beloved Great Leader of His people that dubbed Him Immye Menilik (Mother Menilik). Adwa is our hallowed ground where Ethiopians from all corners converged to defend their liberty by paying incalculable sacrifice in human life, spilt blood, and material resources. The Emperor was a magnanimous great leader who had elevated His captives in the battle fields to enviable top positions in His cabinet.

3.Mahatma Gandhi: Mahatma means “Great Soul”- an accolade given by the people to the Founder of the Indian Nation, the largest democracy in the world. Gandhi developed a method of direct social action based upon the principles courage, nonviolence and truth called Satyagraha. He believed that the way people behave is more important than what they achieve. Satyagraha promoted nonviolence and civil disobedience as the most appropriate methods for obtaining political and social goals. Among the tributes to Gandhi upon his death were these words by the great physicist, Albert Einstein: “Generations to come will scarce believe that such a one as this walked the earth in flesh and blood”. For the purpose of my writing this piece, I would like to add this quote by Gandhi: “Man becomes great exactly in the degree in which he works for the welfare of his fellow-men. “

4. .Martin Luther King: Supreme champion of human rights who gave his life in the struggle for those rights. Here is one of his scores of quotes I chose for my purpose: “Now, I say to you today my friends, even though we face the difficulties of today and tomorrow, I still have a dream. It is a dream deeply rooted in the American dream. I have a dream that one day this nation will rise up and live out the true meaning of its creed: – ‘We hold these truths to be self-evident, that all men are created equal’.”
Nelson Mandela: The only celebrated Statesman of our time who had sacrificed his life for 27 years in prison during the Apartheid era to which he put an end and set up Truth, Peace and Reconciliation Commission to bury the past and lay the foundation for building the Rainbow democratic nation of South Africa.

I should be quick to add that the distinguished exceptional leadership of President Lincoln and Martin Luther King laid the foundation for the minority black people of the USA to hold positions of political power progressively culminating in Mr. Barrack Hussein Obama as the first black African-American. This is a highly commendable act of elevating merit above the ethnic origin, color or creed in electing individuals to high office.

Lincoln, Menilik II, Gandhi, and King dedicated themselves to the noble cause of either fighting aggressors or violators of fundamental human rights so that our common humanity shall be the centerpiece of a democratic and caring society without discrimination based on ethnic origin, creed, gender or political belief. Individual merit should be the sole criterion in public service as was vividly expressed in the Tenesa Teramed (Stand up and stride) rallying song that became popular in the aftermath of the 1974 Ethiopian Revolution. So it matters not to me where the new PM originated from.

Those among the above who held the reigns of political power at the helm did nothing to enrich individuals of their ethnic background because merit was their only yardstick in appointing individuals to higher positions. None are tainted with corruption or abuse of power. All of them fit the template of “Great Leaders” or “Great Statesmen”! Such accolades are validated after a long time and emerge from the masses expressed in various ways such as in poems, music, paintings, folk songs et al – as well as from the chronicles of historians and writings of scholars.

But Zenawi was a cruel despot who tried hard to “make dictatorship work; he is the antithesis of the above supremely stalwart leaders. It is almost certain that Bereket Simon and the EPRDF Party Secretary prepared the acceptance speech in which the accolade of ‘Great Leader’ was inscribed five times and asked the poor new PM to read it. The speech went as far as exalting the tyrant as a leader who cared about the poor of the world. That is how the Stalinist system works!
Giving time to the new PM?

The new PM vowed to retain the legacy of his former boss intact undiminished. One wonders whether it was really out of his own free volition or under duress that he made his acceptance speech given the repugnant legacy left behind by Zenawi, to wit: sellout of Ethiopia’s vital national interests such as active support for the separation of Eritrea; grisly heinous crimes including genocide, victims of torture, incarceration of peaceful protesters en masse; extra judiciary execution of peaceful protesters, the wailing of mothers, the agony of bereaved families, filthy jails in which hundreds of political prisoners are cruelly kept, toiling peasants in serfdom, interethnic hatred, dangerous interference with Orthodox Christian and Muslim religious affairs in violation of the constitution; daylight robbery of votes, pervasive corrupt practices, culture of pathological lies, demised free media, government monopoly of all pillars of democracy, blocked freedom of expression, poor educational standard, forbidden academic freedom in tertiary institutions, a land-locked country, fertile farmland ceded to the Sudan; leasing large chunks of fertile farmlands to unscrupulous foreign investors at tiny price; massive unemployment largely affecting the youth; demoralized youth addicted to psycho-thermal drugs; abject poverty; rampant unemployment; environmental disaster; rampant breach of the constitution; regional instability et al.

Given that the new PM did not make any concession for relaxing the Stalinist policy of the late dictator Zenawi, I oppose the costly traditional “wait and see attitude” and subscribe to the old adage of beating the iron while it is hot. In support of my contention, I provide this quotation by Martin Luther King, which directly applies to the current messy Ethiopian political environment: “This is no time to engage in the luxury of cooling off or to take the tranquilizing drug of gradualism. Now is the time to make real the promises of democracy. Now is the time to rise from the dark and desolate valley of segregation to the sunlit path of racial justice. Now is the time to open the doors of opportunity to all of God’s children. Now is the time to lift our nation from the quicksand of racial injustice to the solid rock of brotherhood”.

Conclusion

The cancerous legacy inherited from tyrant Zenawi that, among other of its atrocious components, relegates Ethiopians to live in divisive ethnic cocoons, and which his successor has vowed to implement, must be categorically rejected. The Amara and Oromo ethnic groups, previously earmarked by Fascist Italy and subsequently by TPLF regime for political extinction, should join forces in self-defense.

This is not the time to relax the struggle against the repressive EPRDF regime particularly when it is engaged in internal feud of the type that dismantled the former USSR and its monolithic CPSU; it is not the time to give it respite at this time when Andualem Aragie, Eskinder Nega, Reyot Alemu, et al are in prison in the face of the vow of the new PM to carry forward the policy of his former boss undiminished.

Four decades of creeping change to democracy has already resulted in incalculable cost in terms of human lives, human sufferings, and wastage of natural resources. The time is now for the Ethiopian people, all opposition forces and civic organizations to deal a heavy blow to the EPRDF while it is in disarray – at this time of internal feud and mistrust is dismantling it. Give no respite to a repressive regime while political prisoners languish in filthy jails and Ethiopia is on the verge of falling apart!

The Almighty God has done His part; he is not going to interfere in the remaining works that we can do in unison as Ethiopians for our own freedom, liberty, dignity, democracy and prosperity.

The legitimate Muslim-Christian joint demand for religious freedom should translate into nationwide peaceful civil disobedience for the sake of securing all liberties enshrined in the Universal Declaration of Human Rights.
President Obama should, in the best longtime interest of his country, reject the EPRDF policy in favor of change to democratic dispensation in Ethiopia that would be a reliable ally in terms of her strategic location particularly at this time of souring relations with Egypt and the Arab world and the rising global political ambition of China. Christianity, Judaism and Islam have lived in relative harmony for centuries in Ethiopia.

LONG LIVE ETHIOPIA!!!

Release all prisoners in Ethiopia including Andualem Aragie, Eskinder Nega, Reyot Alemu, et al
[email protected]

  ኢህአዴግና ፌስቡክ  ሎል !!!!!!!

ኢህአዴግና ፌስቡክ

የኢህአዴግ ካድሬዎች በተለይ ሚዲያው አካባቢ የተሰማሩቱ እንደ ፌስቡክ “አቢዩዝ” ያደረጉት የቴክኖሎጂ ውጤት ያለ አይመስለኝም፡፡ ፌስቡክን አያውቁትም ግን ይፈሩታል፣ ይሸሹታል፣ ተጠቃሚዎቹንም “አብዮተኞች” በሚል ድፍርስ ስም ይጠራሉ፡፡ ስለዚህ ኢህአዴግ በፌስቡክ አማካኝነት ማግኘት የሚገባውን ጥቅም መቶ በመቶ ሳያገኝ ቀርቷል፡፡  ኢህአዴግ የፌስቡክንና የኢትዮጵያን ዝምድና አያውቅም። በዚህም የተነሳ የፌስቡክ አብዮት ይነሳብኛል ብሎ ሰግቶ ነበር፡፡ (የምዕራብ አፍሪካ ህዝባዊ አብዮት የተቀሰቀሰ ሰሞን) በማህበራዊ  ድረ-ገጾች ላይ በጃሚንግ ዘመተ፡፡

በመጨረሻም “የፌስቡክ አብዮተኞች” ሲል አደገኛ ታፔላ ይለጥፏል፡፡ እስቲ በሞቴ ይታያችሁ… ይቺ ሀገር በፌስቡክ አብዮተኞች ኢህአዴግን ከስልጣን ስታባርር? ይሄ ብዥታ እና የእውቀት ማነስ ኢህአዴግን እንደፓርቲ፣ ኢትዮጵያንም እንደ ሃገር ከማህበራዊ ድረ-ገጾች ማግኘት የሚገባቸውን ጥቅም እንዲያጡ አድርጓቸዋል፡፡ (ወይ ነዶ!) እናም ኢህአዴግን ልመክረው እፈልጋለሁ፡፡ ፌስቡክን እንዳይፈራ!

የፌስቡክ አብዮተኞች ከየት?

ይኸውልህ ውዱ መንግስታችን… በፍጹም አትስጋ! ኢትዮጵያውን በፌስቡክ አብዮት ያነሳሉ፣ ጐዳናውን በአመጽ ያሸብሩታል ብለህ በአስቂኝ የቀትር ብርድ እራስህን አትምታ፡፡ “አብዛኛው” የፌስቡክ ተጠቃሚ ኢትዮጵያዊ ያንተ ቢጤ ነው። የፌስቡክን ጥቅም በቅጡ አልተረዳም፡፡ ምናልባትም የጅንጀና አብዮት፣ የሽሙጥ አብዮት፣ የወሲብ አብዮት፣ የስድብ አብዮት ወዘተ ከቀሰቀሰ እንጂ የፖለቲካውንስ ነገር ተወው! (ያውም የኢትዮጵያ?)

ኢህአዴግ… የምሬን ነው የምነግርህ፡፡ ከፈለግህ እገሌ እባላለሁ ብለህ “ቆንጅዬ” የአራዳ ስም ለራስህ ስጥና (ዴቭ፣ ናሂ፣ ኤቢ፣ ጃ፣ . . ምናምል ልትለው ትችላለህ) አካውንት ክፈት። ከዚያም የአንድ ሸበላ ጐረምሳ (ፀጉሩን ፈረዝረዝ ያደረገ) ፎቶ ፈላልግና “ኘሮፋይል ፒክቸር..”ህ አድርገው፡፡ ከዚያ ቢያንስ 1000 ለሚሆኑ የሃገርህ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች .. “ፍሬንድ ሪኩዌስት” ላክላቸው፡፡ ያው ያልተፃፈው የሃገራችን የፌስቡክ  ህግና ደንብ እንደሚያዘው፤ አንድ እንደ አንተ ያለ ሸበላ ኢትዮጵያዊ የፌስቡክ ተጠቃሚ፤ 90 በመቶ ጓደኞቹ ሴቶች መሆን አለባቸው፡፡ እናም “ፍሬንድ ሪኩዌስት” ከምትልክላቸው 1000 ሰዎች 900ዎቹ ሴቶች እንደሚሆኑ አትጠራጠር፡፡ መቶ ወንድ አይበቃህም? (ያውም ከተገኘ ነው) ከዚያ በኋላ በቃ ቻትህን ማጧጧፍ ነው። በተአምረኛው የፌስቡክ መስኮት በኩል ከ20 እና ከ30 የሃገርህ ልጃገረዶች ጋር በአማር-ላቲኖ (በላቲን በሚፃፍ አማርኛ) አሊያም በዝርክርክ እንግሊዝኛ ጨዋታህን ማድራት ነው፡፡ ስልክ ቁጥር መለዋወጥ፣ ኬክ ቤት መቀጣጠር ፣ በሃሜት መቦጫጨቅ፣ ተረብ መወራወር፡፡

ደሞም አትርሳ በሞቀው የቻት ወግህ ከልጃገረዶቹ ጐን ለጐን በሰፊው “ዎል”ህ ላይ ልጆች የሚያስቁ ፎቶዎችን በብዛት ፖስት አድርግ፡፡ ወዲያው መአት ኮሜንቶች ይጐርፉልሃል፡፡ ትደነቃለህ፣ ትሞገሳለህ፡፡ ፖስት ያደረካቸው ፎቶዎች እኮ ምን አይነት መሰሉህ… የአርሰናሉ አሰልጣኝ የሙሽሪትን ቬሎ ለብሰው፣ የማንቼው ደግሞ በሙሉ ሱፍ አጊጠው በሰርግ ሲጋቡ፣ ሮኒ ቫንበርሲን እንደህፃን አዝሎት፣ ቴዲ አፍሮ እጮኛውን ቀና ብሎ ሲያያት ወዘተ… አይነት ናቸው፡፡ ኢህአዴግ ሆይ… ይሄ ትውልድ የትኛውን መንበርህን ይሆን በአብዮት የሚያንቀጠቅጠው?

ግድየለህም ኢህአዴግ እመነኝ አብዛኛው የሃገርህ የፌስቡክ ተጠቃሚ ..አብዮተኛ.. የሚባል ከባድ ስም የሚሰጠው አይነት አይደለም፡፡ ዘርፈ ብዙውን የፌስቡክ ቴክኖሎጂ፣ ሁነኛ የመረጃ እና የእውቀት ማእድ የሆነውን ገበታ፣ ኢትዮጵያውያን ደንበኞቹ እንደ ጉድ እያሰቃዩት ነው፡፡ “አቢዩዝ” እያደረጉት ነው፡፡

ግን ልብ በል ኢህአዴግ!

እስከአሁን የሰነዘርኩት ወቀሳ አብዛኞቹን እንጂ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ የፌስቡክ ደንበኞች አያጠቃልልም፡፡ በፍፁም! ጥቂቶች አሉ- ፌስቡክ የገባቸው፡፡ ድንቅ የመረጃ ምንጭ የሆናቸው፡፡ ለእነዚህ ሰዎች ፌስቡክ እና ሌሎች ማህበራዊ ድረ-ገጾች የእውቀት የመረጃ ገበያ ናቸው፡፡ ይሰጡባቸዋል። ይቀበሉባቸዋል፡፡ ቁምነገረኛ ወዳጅ ያፈሩባቸዋል፡፡ የባህል ማስተዋወቂያ፣ የፍልስፍና መሞገቻ፣ የፖለቲካ መከራከሪያ መድረካቸውም ነው፡፡

እነጊዜሽወርቅ ተሰማ እነማን ናቸው?

ጊዜሽወርቅ ተሰማ ይላል የፌስቡክ አካውንቷ ስም፡፡ ፕሮፋይል ፒክቸሯ ብስል ቀይ፣አፍንጫ ሰልካካ ፣ ደመ ግቡ ሴት መሆኗን ያሳያል፡፡ ሌሎቹ ፎቶዎቿም ተመሳሳይ እውነት አላቸው። “ጊዜ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር” የተሰኘ ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ መሆኗን እና ከ2000 በላይ የፌስቡክ ጓደኞች እንዳሏት ከገጿ ላይ ሰፍሯል፡፡

ከአንድ አመት በፊት ይመስለኛል በሬዲዮ ፋና ቃለመጠይቅ ተደርጐላት ሰምቼ ነው “ፍሬንድ ሪክዌስት” የላኩላት፡፡ ወዲያው ተቀበለችኝ፡፡ ትዝ ይለኛል ሬዲዮ ጣቢያው በስኬታማ  የንግድ ሰውነቷ ነበር እንግዳ ያደረጋት፡፡ ሙዚቃ እየመረጠች ለአድማጮች ተሞክሮዋን አካፈለች፡፡ የምር ሁሉ ነገሯ ቀልብ ይይዝ ነበር፡፡ ጥያቄዎቹን የምትመልስበት መንገድ፣ የምታነሳቸው ሃሳቦች እና ድፍረቷ … የሚማርክ ነበር፡፡ በቃ ምን አለፋችሁ… አሪፍ ሴት ናት። እስከመጨረሻው እየጣፈጠችኝ አዳመጥኳት፡፡  ከሁሉም በላይ ግን ስለማህበራዊ ድረ-ገጾች እና ስለጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ያላትን አመለካከት የገለጸችበት መንገድ ስለማረከኝ ነበር የጓደኝነት ጥያቄ በፍጥነት የላኩላት፡፡

በቃለመጠይቋ ምን አለች መሰላችሁ? “በእረፍት ጊዜ ብቻ አይደለም፤ እንደስራም የተለያዩ ማህበራዊ ድረ-ገጾችን በንቃት እጠቀማለሁ፡፡ ፌስቡክ፣ ትዊተር፣ ሊንክዲን፣ ፓልቶክ”  ወዘተ ሁሉንም በደንብ እጠቀማለሁ፡፡ የሃገሬን ባህል፣ ታሪክ እና ኪነጥበብ በተቻለኝ መጠን አስተዋውቅበታለሁ፡፡ የንግድ እንቅስቃሴዬን አቀላጥፍበታለሁ፣ ወዳጆች አፈራበታለሁ፡፡ ከሁሉ በላይ ግን የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን እንቅስቃሴዎች በሙሉ በንቃት እየተከታተልኩ ለአለም አሳውቅበታለሁ፡፡ ስለጠቅላይ ሚኒስትሩ አዳዲስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን አቀርብበታለሁ፡፡ በተለይም ንግግሮቻቸውን በትኩስነታቸው ከያለበት እየፈለፈልኩ ለፌስቡክ ጓደኞቼ አካፍላለሁ” (ልብ አድርጉ ሙሉ ቃሏን እንደወረደ አላቀረብኩም) “ለምን እንዲህ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ አተኮርሽ?” ጋዜጠኛው ይጠይቃል፡፡ “በጣም ስለምወዳቸው፣ ስለማከብራቸውና ስለምኮራባቸው፡፡ ንግግራቸው በእውቀት የተሞላ ነው፡፡ በሳል መሪ ናቸው፡፡ ብልህ እና ለአገር አሳቢ ናቸው፡፡ እንደውም ባይገርምህ ከ5ሺህ በላይ ከእሳቸው ንግግሮች የተወሰዱ ማራኪ አገላለጾች አሉኝ፡፡”

ጊዜሽወርቅ ማብራሪያዋ ቀጥሏል፡፡ ኢትዮጵያዊያን የማህበራዊ ድረገጾችን ፋይዳ ገና እንዳልተረዱ፣ መንግስትም ድርሻውን እንዳልተወጣ በግልጽ ተናገረች፡፡ በወጉ ከተጠቀምንባቸው እንደ አሪፍ የመረጃ እና የእውቀት ምንጭ ልንገለገልባቸው እንደምንችል በሙዚቃ እያዋዛች ነገረችን፡፡ (ተባረኪ!)

ሴትየዋ እውነቷን ነው!

የፌስቡክ ጓደኛዬ ከሆነች በኋላ ሁሉን ነገር አረጋገጥኩ፡፡ እውነትም ይቺ ሴት በፌስቡክ በገንዘብ የማይለካ ትርፍ እያገኘችም እያስገኘችም ነው፡፡ በገጿ ላይ ..ፖስት.. የምታደርጋቸው ጽሁፎች፣ ኦዲዮ እና ቪዲዮ ክሊፖች፣ ፎቶዎች፣ ስእሎች ወዘተ… ሃገርን የሚያስተዋውቁ ናቸው፡፡ የአቶ መለስ ዜናዊ ፎቶዎችና ንግግሮች በብዛት ይገኙበታል፡፡ በተረፈ ስለሴቶች፣ ሰለህፃናት፣ ስለትምህርት፣ ስለጤና በጠቅላላው  ስለልማት የሚያትቱ መረጃዎች ከገጿ ላይ ሞልተዋል፡፡ ኪነጥበቡ ፣ ስፖርቱ፣ ፖለቲካው፣ ሚዲያው … ብቻ ኢትዮጵያዊ የሆነ ነገር ሁሉ የሴትየዋ የፌስቡክ ገጽ ላይ ሰፊ ቦታ ይሰጠዋል፡፡ ከእያንዳንዱ ፎቶ እና ቪዲዮ ስር በኢትዮጵያዊ ጨዋ ቃላት የተሞሉ መልእክቶችን ታሰፍራለች፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩን እንቅስቃሴዎች ታደንቃለች፣ ትደግፋለች፡፡ የስኮላርሺፕ እድሎችን በብዛት ፖስት ታደርጋለች። ከታላላቅ መጽሃፍ የተወሰዱ እና ለለውጥ የሚያነሳሱ ጥቅሶችን በየሰከንዱ ታስነብበናለች፡፡ ታዲያ ቁጥራቸው እና አይነታቸው ይብዛ እንጂ መልእክቶቹ በሙሉ የሚሰጡት ትርጉም አንድ ነው። “እንዋደድ! በፍቅርና በአንድነት ተጣምረን ሃገራችንን እናሳድግ፤ በእውቀት እንደግፍ! በእውቀት እንቃወም! ኢትዮጵያ ለዘለአለም ትኑር!” (አሜን)

 

እናም ኢህአዴግ ሆይ፤

ከዚች ሴት መማር ያለብህን ትልቅ ጉዳይ አስረግጬ ልንገርህ፡፡ እስቲ… ሴትየዋ ደከመኝ ሰለቸች ሳትል በፌስቡክ የምታስተላልፋቸውን መልእክቶችና አስተያየቶች በጥሞና ለመመልከት ሞክር፡፡ አንዳንድ ዳያስፖራዎች በዘለፋና በጥላቻ ሊያስመርሩህ ይችላሉ፡፡ ቢሆንም ግን ግዴለም አትበሳጭ! ዘለህ “የፌስቡክ አብዮተኞች..” እያልክ ታፔላ አትለጥፍ! እስቲ የሴትየዋን መልሶች የበለጠ ትኩረት ሰጥተህ ተመልከታቸው፡፡ ለማን ምን እንዳለች፣ ለስድቦቹ ምን እንደምትመልስ እየደጋገምክ አንብብ፡፡ ከዚያ  ይገለጥልሃል፡፡ እውቀት እና ቅንነት ምን ያህል  አሸናፊ እንደሆነ ትረዳለህ፡፡ ሴትየዋ እና መሰሎቿ ምን አይነት ትውልድ እየቀረጹ እንደሆኑ ተገንዝበህ ትደነቃለህ፡፡ በአንተ በመንግስት ደረጃ እንኳን ያልተሰራውን ስራ አንዲት ግለሰብ በሃገር ፍቅር ተነሳስታ (ፖለቲከኛ ትሆን እንዴ? ትሁና!) ስትሰራው አይገርምም! አንተ በሩቁ የምትሸሸውን “ዲያስፖራ” እና “የፌስቡክ አማጺ ቡድን” እሷ ፊት ለፊት ስትጋፈጠው ታያታለህ፡፡

እስቲ በሞቴ ስማኝ!

የዚህችን ሴት አይነት ተግባር የሚያከናውኑ 1000 የፌስቡክ ካድሬዎች ብታሰለጥን ምን ሊፈጠር እንደሚችል? (መቼም ከዚህ ሁሉ የልማት ሰራዊት 1000 በእንግሊዘኛ የሚግባባ አይጠፋም አይደል?) በነገርህ ላይ አንድ የምታስቅም የምታናድድም መረጃ ሹክ ልበልህ (ያ ጋዜጠኛ ወዳጄ ነው ያጫወተኝ) ምን መሰለህ… የማታ ተረኛ የሆኑ የኢቴቪ ሰራተኞች እንደቀኑ አይበዙም አይደል! “ግን ምን የሚሆንበት ሁኔታ አለ” መሰለህ? የማታው የሰራተኞች ሰርቪስ ጢም ብሎ ከመሙላቱ የተነሳ ቦታ ሁሉ ይጠፋል አሉ፡፡ ለምን መሰለህ? ያለስራ የሚያመሹ የቀን ሰራተኞች ስላሉ ነው (አሉ ነው) ምን ሲሰሩ በለኛ … ፌስቡክ ላይ ተጐልተው እልሃለኋ! ይሄ “ልማታዊ ጋዜጠኛህ” ሁሉ አንዲት የቢቢሲ ዜና “እንደነገሩ” ተርጉሞልህ፣ በቀጥታ ወደፌስ ቡክ ቺኮቹ ይወረውርልሃል፡፡

ከዚያ እስከ ማታ “ሰርቪስ ሲሄድ ጥሩኝ” እያለ መጀናጀን ነው፡፡ ግራ ከገባቸው ዲያስፖራዎች ጋር አንተኑ ሲያማህ ይውላል፡፡ ለኢሳት መረጃ ልኮ ከኢቴቪ ደሞዝ ይቀበላል፡፡ (መረጃ ነው ስብቀት?)

እሺ ይሁን ልማታዊዎቹን ጋዜጠኞችህን ተዋቸው፡፡ ቆይ ባለስልጣናቱስ ምንድን ነው የሚሰሩት?፡፡

እስቲ በስሙ የፌስቡክ አካውንት ከፍቶ ስለፓርቲው የፖለቲካ አቋም የሚሰብክ፣ የሚሟገት እና ለፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ሥራ የሚሰራ ባለስልጣን ካለህ አስተዋውቀኝ፡፡ የለህም፡፡ ወይም አላገጠመኝም። ግን አትድከም አታገኝም፡፡

እነጊዜሽወርቅ ደሞ አሉልህ … በራሳቸው ወጪ ያንተን ስራ የሚሰሩልህ! ስራችን ነው ብለው ስላመኑ ግን ትጋታቸው ለጉድ ነው፡፡ ኧረ ንቃ ኢህአዴግ!

 

እናም ኢህአዴግ ሆይ እባክህን ምክሬን ተቀበለኝ!

ግብሩ ክፉኛ በተመሳቀለው፣ ፋይዳው ሲበዛ በተንሸዋረረው የኢትዮጵያችን የፌስቡክ ሜዳ ላይ ስድቡን፣ ዘለፋውን፣ ዛቻ እና ማስፈራሪያውን ተቋቁመው ስለዚች ሀገር መልካምነት የሚተጉትን፣ የሚለፉትን እንደ ትምህርት ቤትህ እያቸው፡፡

ተማርባቸው! አይዞህ…ፌስ ቡክ አትፍራ! ድረገፆችን ጃም አታድርግ፡፡ መረጃ ሃይል ነው!!


የመለስ ዜናዊ ፕሮቶኮል ሃላፊ የሃይለማርያምን ሴት ልጅ ለጋብቻ አጫት::

የሃይለማርያም ሴት ልጅ ተጨማሪ ጠባቂዎች እና መኪና ተመደበላት::

 

የመለስ ዜናዊ ፕሮቶኮል ሃላፊ የሃይለማርያምን ሴት ልጅ ለጋብቻ አጫት::የ22 አመትዋ ዮሃና ሃይለማርያም ደሳለኝ ተጨማሪ ጠባቂዎች እና መኪኖች እንደተመደቡላት የቤተመንግስት ምንጮች ገለጹ::

ዮሃና አዲስ አበባ ቦሌአከባቢ በሚገኘው ዳንዱቦሩ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ዉስጥ ተማሪ የነበረች ሲሆን አሁን በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ዉስጥ እየተማረች ስትገኝ አዲስ ጠባቂዎች መመደቡ ከጉዋደኞችዋ እንዳትገናኝ ተጸኖ ፈጥሮባታል::
ልክ እንዳቶ መለስ ልጅ ሰምሃል ተመሳሳይ ጠባቂዎች የተመደቡላት ዮሃና የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ የፕሮቶኮል ሃላፊ ለጋብቻ አጭቱዋታል:;

ጠ/ሚ/ሩ በሙስና “የተለከፉ መስመር እንዲይዙ ይደረጋል” አሉ፡፡


ዛሬ አርብ ልክ ከጠዋቱ 3፡38 ላይ 374 የኢህአዴግ ወኪሎችና ኢህአዴግን እንደሚደግፉ በግልጽ የሚናገሩት አንድ በግል ያሸነፉ የፓርላማ አባል የሚገኙበት የተወካዮች ምክር ቤት አጨበጨበ። ጭብጨባውን ተከትሎ ኢቲቪ የቦሎ ሶሬውን ሰው አመላከተ። ከሃያ አንድ ዓመት በኋላ በሟቹ አቶ መለስ የፓርላማ መቀመጫ ላይ የተሰየሙት አቶ ኃይለማርያም ፈገግታ አሳዩ። አስቀድሞ የተነገረው በትረ ሹመት ስርዓቱን አሟላ። አቶ ኃይለማርያም የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መሆናቸው ታወጀ።
ቀልጠፍ ቀልጠፍ እያደረጉ ስርዓቱን የመሩት አፈ ጉባኤ አባ ዱላ ገመዳ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት የሆኑትን አቶ ተገኔ ጌታነህን ጋበዙ። በሳቸው ትዕዛዝ ኃይለማርያም ቃለ መሃላ ለመፈጸም ቀኝ እጃቸውን አነሱ። ስማቸውን ጠርተው ማሉ።“…ከአገርና ከህዝብ የተጣለብኝን ሃላፊነት በቅንነት፣ በታታሪነት፣ እንዲሁም ህግንና ስርዓትን ለመፈጸም ቃል እገባለሁ” ሲሉ ሲናገሩት ቀላል የሚመስለውን መሃላ በመልካም አስተዳደር፣ በሙስና፣ በድህነት፣ በዴሞክራሲ እጦት፣ በፍትህ ጥማት፣ ቀና መሪ በራበው፣ እስርና ስቃይ ባንገፈገፈው፣ የመሰብሰብና የመናገር መብት በተገፈፈ፣…… ህዝብ አቀረቡ።
3፡38 ላይ ሙሉ ጠ/ሚኒስትር የሆኑት አቶ ኃይለማርያም ከአንድ ደቂቃ በኋላ “ ክቡር ጠ/ሚኒስትር” ተብለው ንግግር እንዲያቀርቡ ተጋበዙ። “የተከበራችሁ የኢትዮጵያ ህዝቦች” በማለት በጠቅላይ ሚኒስትርነት ሙሉ ማዕረግ ንግግራቸውን የጀመሩት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ አስራ ስድስት ደቂቃ በፈጀው ዲስኩራቸው ቅድሚያ የወሰዱት ሹመታቸውን “ታላቅ ዕድል” በማለት ነበር።
አቶ መለስን በማሞካሸት የታጀበው የአዲሱ ጠ/ሚኒስትር ንግግር “… የኔ ድርሻ የአቶ መለስን ሌጋሲ/ውርስ/ ሳይበረዝ ማስቀጠል ነው” በማለት ወ/ሮ አዜብ ባለቤታቸውን በመስቀል አደባባይ ሲሸኙ የተናገሩትን ቃል በቃል አጣቅሷል። እያንዳንዱን ዘርፍ በመዳሰስ መልዕክታቸውን ያስተላለፉት አቶ ኃይለማርያም በእርሻና በመስኖ ልማት የአገር ውስጥ ባለሃብቶችን ለመደገፍ ትልቅ ትኩረት እንደሚሰጡ ባሰመሩበት ንግግራቸው በጥንቀቄ ተዛልፈዋል።
ሹመታቸውን “ታላቅ ዕድል ነው” ያሉት አቶ ኃይለማርያም፤ ሙስናን አስመልክቶ ሲናገሩ በከፍተኛ ደረጃ ኪራይ ሰብሳቢነትና የሙስና ወንጀል የሚፈጸምባቸውን ዘርፎች ዘርዝረዋል። የመሬት አስተዳደር፣ የታክስና ቀረጥ አሰባሰብ፣ የመንግስት ግዢ አሰባሰብናና የፍትህ አሰጣጥ ዘርፍን በዋናነት ነቅሰው በመጥራት “በሙስናና በስነ ምግባር ጉድለት የተለከፉ ሰዎችን በአግባቡ መስመር ማስያዝ ይገባል” ሲሉ አሳስበዋል። ህዝብ ያለማቅማማት ተባባሪ እንዲሆንም ጠይቀዋል።
ፖሊስ፣ አቃቤ ህግ፣ ፍርድ ቤቶች፣ ህዝቡን በማርካት ማገልገል እንደሚኖርባቸው ያሳሰቡት አቶ ኃይለማርይም፤ ምርጫ ቦርድን ጨምሮ ከተለያዩ ተቋማትና ህግን አክብረው ከሚሰሩ ካሉዋቸው የተቃዋሚ ፓርቲዋች ጋር አብረው እንደሚሰሩ ቃል ከመግባት ውጪ መንግስታቸው ተቋማዊ ለውጥ ለማድረግ ስለማሰቡ የተነፈሱት ነገር የለም።
በነጻነት እጦት ስለታፈነው የነጻው ፕሬስ በደምሳሳው አብረን እንሰራለን ከማለት ውጪ በበጎም ሆነ በመልካም ጎኑ ምንም ሳይናገሩ አልፈውታል። የመልካም አስተዳደር ችግር ሮሮ እንዳለ በማውሳት ህዝብን በቀናነት ማገልገል እንደሚገባ ያመለከቱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ መንግስት የሃይማኖት ነጻነትን እንደሚያከብርና ጣልቃ እንደማይገባ አውስተው ማሳሰቢያ ሰጥተዋል።
አቶ መለስን መስለው ባስተላለፉት ማሳሰቢያ በሃይማኖት ስም የሚደረግን ማናቸውም ዓይነት የሽብር ተግባር እንደማይታገሱ በግልጽ አስቀምጠዋል። ተግባሩንም “በቀጥታ ከህገ መንግስት ጋር የሚያላትም ነው” ብለውታል። በማንኛውም ሽብር ነክ ጉዳዮች ላይ መንግስታቸው ህጋዊ ርምጃ እንደሚወስድ ያሳሰቡት አቶ ኃይለማርያም ሽብር ነክ ስላሉዋቸው እንቅስቃሴዎች አላብራሩም። ይልቁኑም ኢትዮጵያን ከማንኛውም አይነት ጥቃት የሚከላከል የመከላከያ ሃይል መገንባቱን በማውሳት “ከህዝባችን ጋር በመሆን ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ሰላማዊና የተረጋጋች አገር መሆኗን አስመስክረን እንቀጥላለን” በማለት የመከላከያ ተቋማት ይበልጥ ሳይንሳዊ የሚሆኑበት አቅጣጫ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው ያስገነዘቡት።
አዲስ ካቢኔ ስለማቋቋማቸው ዝምታን የመረጡት ጠ/ሚ/ሩ “የባንዲራ ፕሮጀክት” በሚል ስያሜ የሚጠራውን የአባይ ግድብ ከተያዘለት እቅድ አስቀድሞ ለመጨረስ ርብርብ እንደሚደረግ ተናግረዋል። ፕሮጀክቱ እንዲቆም ጫና ስለመኖሩና ፕሮጀክቱን ለማስፈጸም ስላጋጠመው የገንዘብ እጥረት ግን ያወሱት ነገር የለም።
የዋጋ ግሽበትን ለማርገብ ከዘንድሮው የምርት ዓመት የተሻለ ምርት እንደሚገኝ በማመልከት መልካም ምኞት ከማስተላለፍ ውጪ ግሽበቱን ለማቃለል በተለይ ስለሚተገበር ጉዳይ ያላብራሩት አቶ ኃይለማርያም በሌላ መልኩ በአገሪቱ ኢንዱስትሪ እንዲስፋፋ ለማድረግና የአገር ውስጥ ባለሃብቶች በእርሻ ስራ እንዲሳተፉ እገዛ እንደሚደረግ አጽንኦት ሰጥተው መናገራቸው በዛሬው ንግግራቸው ውስጥ ታላቁ ቁም ነገር ተብሎላቸል።
የመስኖ እርሻን ስለማስፋፋትና ሰፋፊ እርሳዎች በአገር ተወላጆች እንዲጎለብት ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ የተናገሩት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ለውጪ ባለሃብቶች በሳንቲም እየተቸረቸረ ስላለው አገሪቱ ለም መሬት ጉዳይ አቋማቸውን አላሳወቁም። በርካቶችን እያፈናቀለ ያለው የመሬት ወረራ የደም ዋጋ እያስከፈለ ያለ ከመሆኑም በላይ ምርቱ አገር ውስጥ እንዲውል የሚደረግ አለመሆኑ ከፍተኛ ተቃውሞ ሲሰነዘርበት የቆየና አሁን ድረስ መልስ ያላገኘ ጉዳይ ነው።
ጠ/ሚ/ር ኃይለማርያም ደሳለኝ የብአዴን ሊቀመንበርና የኢህአዴግ ምክትል ሊቀመንበር የሆኑትን አቶ ደመቀ መኮንን ለምክትል ጠ/ሚኒስትርነት አቅርበው አሹመዋል። አቶ ደመቀ ልክ እንደ አቶ ኃይለማርያም ቃለ መህላ ፈጽመው ሹመታቸውን አጽንተዋል። በቀጣይ ከሁለት ወር በኋላ ትግራይ የሚካሄደው የኢህአዴግ ጠቅላላ ጉባኤ ተለዋጭ መሪዎችን ካልመረጠ በስተቀር አቶ ኃይለማርያም በአሁኑ ሰዓት የደህኢዴን ሊቀመንበር፣ የኢህአዴግ ሊቀመንበር፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ የጦርሃይሎች ጠቅላይ አዛዥ፣ የሚኒስትሮች ምክርቤት ሰብሳቢና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን ባለትልቁ ማዕረግ ናቸው። ህወሓት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነቱን ስልጣን ለኦህዴድ በመስጠት የፖለቲካውን ክፍተት ቢሞላው የተሻለ እንደሚሆን አስተያየት እየተሰነዘረ ነው፡፡

ህወሓት የደኅንነት ሞተሩን መሪው አደረገ!

ህወሓት የድርጅቱን መሪዎች መምረጡን ይፋ አድርጓል። በዚሁ መሰረት አቶ አባይ ወልዱ ሊቀመንበር፣ ዶ/ር ደብረጽዮን ወልደ ሚካኤል ምክትል አድርጎ ሰይሟል። ምርጫው የተከናወነው መቀሌ ሳይሆን አዲስ አበባ ነበር። ሴፕቴምበር 19 ይፋ የተደረገውን የህወሓት ምርጫ አስመልክቶ ህወሓት መግለጫ አሰራጭቷል።
ህወሓት በምርጫው ያልተገመቱና አዲስ አመራር ወደ ሃላፊነት አምጥቷል። እርሳቸውም ዶ/ር ደብረጽዮን ወልደ ሚካኤል ናቸው። በሚኒስትር ማዕረግ የኢንፎርሜሽንና ደህንነት ኤጀንሲ ዳይሬክተርና የኢትዮ ቴሌኮም ቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት  ዶ/ር ደብረጽዮን በነባር ታጋዮች ዘንድ እይወደዱም።
ደብረጽዮን ወልደ ሚካኤል በደኅንነቱ የሚከናወኑ ከፍተኛ ጉዳዮችን የሚመሩ፣ ከፍተኛ ውሳኔዎችን የሚወስኑ፣ የአገሪቱን የደኅንነት መዋቅር ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ጎን ለጎን የሚመሩ መሆናቸውን በቅርብ የሚያውቁ ይገልጻሉ። ህወሓት የገነባውን የደህንነት መዋቅር በታማኝነት የሚቆጣጠሩት አዲሱ የህወሓት ምክትል ሊቀመንበር  ህወሓት ለሁለት በተከፈለበት ወቅት አቶ መለስ በአሸናፊነት እንዲወጡ ታላቅ ሚና መጫወታቸውን በብዙዎች ይፋ ያልወጣ ግለ ታሪካቸው ነው።
ለአቶ መለስ እጅግ ቅርብ የሆኑት ደብረጽዮን ህወሓትን ወክለው የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራር እንዲሆኑ በህወሓት በኩል ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለ የጎልጉል የመረጃ ምንጮች አስታውቀዋል።  በዘመነ ህንፍሽፍሽ ህወሓት ለሁለት መሰንጠቁ ይፋ ከመሆኑ በፊት ልዩነቱ ውስጥ ውስጡን በተጋጋመበት ወቅት አቶ ደብረጽዮን ከአቶ መለስ የተቀበሉትን ልዩ ተልዕኮ ለመተግበር ያስችላቸው ዘንድ የሽሬ ምክትል አስተዳዳሪ ተደርገው ተሹመው ነበር። አፈንጋጭ የተባለውን ቡድን ከሚመሩት መካከል ዋና ኃይል አላቸው ተብለው የሚፈሩት አቶ ስዬ አብርሃ በትውልድ መንደራቸው ተምቤን ውስጥ ያላቸውን ሰንሰለት ለመበጣጠስና ለማምከን ልዩ ተልዕኮ ይዘው ወደ ሽሬ ያመሩት ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል ሃላፊነታቸውን በመወጣት ለመለስ አሸናፊነት ጉልህ ሚና መጫወታቸውን ምንጮቹ ጠቅሶ ጎልጉል ዘግቦ ነበር።
http://www.goolgule.com/%E1%88%85%E1%8B%88%E1%88%93%E1%89%B5-%E1%8B%A8%E1%8B%B0%E1%8A%85%E1%8A%95%E1%8A%90%E1%89%B5-%E1%88%9E%E1%89%B0%E1%88%A9%E1%8A%95-%E1%88%98%E1%88%AA%E1%8B%8D-%E1%8A%A0%E1%8B%B0%E1%88%A8%E1%8C%88/

አዲሱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቃለ መሃላ ፈጽሙ ::
ዲሱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቃለ መሃላ ፈጽሙ ::
ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እንደሚገኙ ተገለጸ። ላለፉት ሁለት ዓመታት የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ያገለገሉት ሃይለማሪያም ደሳለኝ እስካሁንም በመንግስት የመገናኛ ብዙሃን የሚጠሩት በዚሁ ማእረግ ነው። በተለይ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩበት ቀን ጀምሮ ሀገሪቷን የመምራት ሃላፊነት ተረክበዋል ቢባልም የመጠሪያቸው ነገር አነጋጋሪ ሆኖ ቆይቷል።

ቃለ መሃላ ፈጽመው ሙሉ ጠቅላይ ሚኒስትር የሚሆኑትም ፓርላማው በመደበኛው ጊዜው በሚያደርገው ስብሰባ እንደሆነ ሲገለጽ መቆየቱ ይታወሳል። አቶ ሃይለማሪያም ፓርላማ ቀርበው ቃለ መሃላ ፈጽመው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ሆነዋል::

የፌደራል ስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን መርማሪዎች አቶ አባይ ጸሃዬን “የመሬት ከበርቴው” የሚል ስም ሰጥተዋቸዋል።


http://www.haqe.org/Abay%20Tsehaye.html

“የመሬት ባላባቱ” ሚኒስትር!! ....ጎልጉል 

 

ምስጢሩን ያጋለጠው መሃንዲስ የት ደረሰ?
አቶ አባይ ጸሀዬ በዘመዶቻቸው ስም በርካታ መሬቶች መውስዳቸው፣ ቦሌ ክፍለ ከተማ ውስጥ ባስቀመጡት ሃላፊ አማካይነት በመሬት ንግድ ከፍተኛ ጥቅም ማግኘታቸው፣ ህጋዊ ሰነድና ካርታ ያለው ቁልፍ ቦታ ከባለቤቱ ተነጥቆ ለእርሳቸው ዘመድ መሰጠቱ ሲረጋገጥ ምርመራው እንዲቆም መታዘዙ ታወቀ። በየክልሉ ተመሳሳይ ንቅዘት አለ።
በህዝብና በቦሌ ክፍለ ከተማ ሰራተኞች፣ እንዲሁም ለአብነት የተጠቀሱት ንብረታቸው የተወሰደባቸው ሴት ወ/ሮ ጉዳያቸውን የትኛውም ቦታ ሲወስዱ መጀመሪያ ቀጠሮ እንደሚሰጣቸው፣ በቀጠሮዋቸው ቀን ሲሄዱ ምን ምላሽ እንደማያገኙ ጠቅሰው  ባቀረቡት አቤቱታ መሰረት የተጀመረው የምርመራ ስራ ይህንን ይመስላል።
ቀደም ሲል ተጠሪነቱ ለአቶ መለስ የነበረው የፌደራል ስነ ምግባርና ጸረ ሙስና  ኮሚሽን መርማሪዎች አቶ አባይ ጸሃዬን “የመሬት ከበርቴው” የሚል ስም ሰጥተዋቸዋል። ስያሜውም የተሰጣቸው በቦሌ ክፍለ ከተማ መሬት ሲነግዱ ስለነበር ነው።
የኮሚሽኑ የጎልጉል ምንጭ እንዳመለከቱት አቶ አባይ ጸሀዬ መሬት ሲነግዱ እንደ ነበር የታወቀው በክፍለ ከተማው በተካሄደ ምርመራ ነው። በክፍለ ከተማው በጠራራ ጸሃይ የግለሰቦችን መሬት ሳይቀር እየቸበቸበ እንደሚገኝ ኮሚሽኑ በደረሰው ተደጋጋሚ ጥቆማ መሰረት የሚመለከተው መምሪያ መነሻ ጥናት ያዘጋጅና ምርመራው እንዲጀምር ይታዘዛል።
በዚሁ መሰረት የኮሚሽኑ መርማሪዎች ስራቸውን ይጀምራሉ። የኮሚሽኑ ባለሙያዎች  ምርመራ እንደጀመሩ መሬት በህገወጥ መንገድ ሲቸበቸብ እንደነበር ይረዱና ከመሬት ጋር የተያያዙ መረጃዎችን ያሽጋሉ። የመሬት ልኬትም ሆነ ከመሬት ጋር የተያያዘ ስራ እንዳይሰራ ያግዳሉ። በተጨማሪም መሬት እየለኩ ሲሰጡ የነበሩ መሃንዲሶች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጎ ምርመራው በጥብቅ እንዲካሄድ ይደረጋል።

ክፍለ ከተማው ክልሉን ወደ ገጠር ቀበሌዎች እያሰፋ መሬት ይከልላል። መሬታቸው የተወሰደባቸው ደካማዎችን ቦሌ ክፍለ ከተማ ካሳ ለመውሰድ ሲንከራተቱ ማየት የተለመደ ነው። አራት ዓመት፣ አምስት ዓመት ከዚያም በላይ ካሳ ሳያገኙ የሚመላለሱ ደካሞች አሁን ድረስ አሉ። ባለንብረት ለንብረቱ ካሳ የሚከፍለው አጥቶ ይንከራተታል፤ መሬት የመንግስት እንደሆነ ያወጀው መንግስት በከፍተኛ ባለስልጣኖቹ አማካይነት መሬት አየር በአየር ይቸበችባል። ይህ የአሰራሩ ግድፈት ሲሆን ለአብነት የተጠቆመው ጉዳይ አስከፊነትና የወንጀሉ ርህራሄ አልባነት እዚህ ላይ ጎልቶ ይታያል።
አሳዛኝ የተባለው የምርመራ ውጤት ታሪክ የሚጀምርው እዚህ ላይ ነው። መሃንዲሶች በሙሉ ታስረው ተመረመሩ። ምርመራው በሙሉ ወደ አንድ ሰው ቢያመላክትም ያንን ሰው ደፍሮ የሚናገር ጠፋ። ይህን ጊዜ “ለምን” የሚል ጥያቄ ተነሳ። የመሬት አስተዳደር ሃላፊውና የክፍለከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ ጉዳዩ የማይመለከታቸው ተደርጎ መወሰዱ፤  መሬት በህገወጥ ስለመቸብቸቡ በቂ መረጃና ማስረጃ በቀረበበት ሁኔታ፣ መሬታቸውን በግፍ ተነጥቀው ለሌላ ሰው የተሰጠባቸው እንዳሉ ተረጋግጦ ሳለ ካርታ ላይ የሚፈርሙትና ለመሃንዲሶች ትዕዛዝ የሚያስተላልፉት የመሬት አስተዳደር እንዲታሰሩና እንዲመረመሩ አለመደረጉ በጓሮ ኮሚሽኑ የሚታማበት ጉዳይ ሆነ። “ጥርስ የሌለው አንበሳና የመለስ አሽከር” የሚለው የኮሚሽኑ ስም በስፋት ተነሳ!!
“ለፀረሙስና ኮሚሽን ሌላ ጸረ ሙስና ኮሚሽን” በሚል የክፍለ ከተማው ሰራተኛ የሆኑ ደብዳቤ በመጻፍ ወቀሳ ሰንዝረው ምርመራው በወጉ እንዲከናወን ጥቆማና አስተያየታቸውን ላኩ። አንዳንድ ስማቸውንና ማንነታቸውን የደበቁ ሰዎች ጉዳዩን ለግል ሚዲያና ለመንግስት መገናኛዎች እንደሚያቀብሉ ዛቱ። ማንም ምን ቢል የሚሰማም የሚደነግጥም ጠፋ።
ምርመራ ከተደረገባቸው ጉዳዮች መካከል ለአብነት የተቀመጠው ዛሬ ህንጻ በብድር ተገነብቶበት ከፍተኛ ኪራይ የሚሰበሰብበት ከመገናኛ ወደ ገርጂ በሚወስደው አዲሱ ጎዳና ዳር ላይ ያለ አንድ ቦታ ጉዳይ ሲጎተት ሚስጥሩን ገለጠው። የመረጃው ምንጭ እንዳስረዱት ምርመራውን የያዘው ባልደረባቸው እንደነገራቸው ምስጢሩ ሲገለጽ ማመን አቅቶት ነበር።
ለክፍለከተማው የመሬት አስተዳደር ሃላፊ ቅርብ ተጠሪ የሆነው መሃንዲስ ምርመራ ሲካሄድበት “እንግዲያውስ እውነቱ ይህ ነው” በማለት አብራራ። በግፍ የተወሰደው ከላይ የተገለጸው ቦታ የተሰጠው ለአቶ አባይ ጸሃዬ ዘመድ መሆኑን ይፋ አደረገ። መሬቱ የቀድሞው ባለቤቶች ለመሆኑ የሚገልጽ በቂ ማስረጃ እንዳለው ቢታወቅም አለቃው አዲስ የባለቤትነት ማስረጃ ቀደም ሲል እንደነበር ተደርጎ እንዲያዘጋጅ ባዘዘው መሰረት የሰው ንብረት አሳልፎ መስጠቱን አስታወቀ። ይህን ጊዜ ምርመራው ባስቸኳይ ወደ ሌላ መርማሪ እንዲዛወር ተደረገ።
የቦሌ ክፍለ ከተማ የመሬት አስተዳደር ሃላፊ አቶ መሠረት የአቶ አባይ ጸሃዬ የቅርብ የስጋ ዘመድ ሲሆኑ፣ በእርሳቸው ትዕዛዝና አጽዳቂነት በክፍለ ከተማው በርካታ ቁልፍ ቦታዎች ለዘመድ አዝማድ በሽርክና፣ ለባለ ገንዘብ በሽያጭ እንዲዘዋወሩ መደረጉ በምርመራ እንደታወቀ አስቸኳይ መመሪያ ተላለፈ።
መመሪያው እስረኛው መሃንዲስ ባስቸኳይ እንዲለቀቅ፣ ምርመራውም እንዲቋረጥ የሚል ነበር። ከፍተኛ የሙስና ወንጀልና የስነምግበር ጉድለት መከሰቱን፣ በግፍ ንብረታቸውን ተቀምተው ባዶ እጃቸውን የቀሩ እንዳሉና፣ በማስፋፊያ ስም ቁልፍ ቦታዎች ከህግ ውጪ መተላለፋቸውን ይፋ ለማድረግ ሰፊ ጊዜ ወስዶ የተሰራው ስራ ሙሉ በሙሉ ይፋ ሳይሆን ተዳፈነ። የተልከሰከሰ የስራ ሪፖርት እንዲቀርብ ተደርጎ ፋይሉ ተዘጋ። ከእስር የተፈታው መሃንዲስም ደብዛ ጠፋ። የአገር ደህንነት ከበርካታ ተመሳሳይ ወንጀሎች ጋር ጉዳዩን እንደያዘው የጎልጉል ዘጋቢ አረጋግጧል።
የድርጊቱ ዋና ተዋናይ የአቶ አባይ ዘመድ እንኳንስ ሊታሰሩ በእድገት የከንቲባ ኩማ ደመቅሳ አማካሪ ሆነው አዲስ አበባ አስተዳደር ተመደቡ። ዋና ስራ አሰፈጻሚው የፌደራል ስራና ከተማ ልማት ሚኒስትር ውስጥ ከፍተኛ ሹመት ተሰጣቸው። በአሁኑ ወቅት የከንቲባው አማካሪ የሆኑት የአባይ ጸሃዬ ዘመድ መሬትን አስመልክተው ኪራይ ሰብሳቢነት ስለመስፋፋቱ ክፍለ ከተሞችን ሰብስበው ይሰብካሉ። ስለ ሙስና አደገኛነት በየመድረኩ እንዲያስተምሩ ተደረገ። ድርጊቱ በርካቶችን አስቆጣ። በርካታ የወቀሳ ደብዳቤ ለኮሚሽኑ ጎረፈለት። በአካል ቀርበው ምስክርነት የሰጡና ኮሚሽኑ ሊመሰርት አቅዶት ለነበረው ክስ ምስክር ለመሆን የተስማሙ ደነገጡ።
ጉዳዩ እንዲዳፈን ስለተደረገበት ምክንያት ሲያስረዱ “በየትኛውም ደረጃ ያሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ በደህንነት ውስጥ ያሉ ባለስልጣናትና መካከለኛ ደረጃ ሃላፊዎች በግልጽ ሙስና ውስጥ መዘፈቃቸው በመረጃ ቢቀርብም ኮሚሽኑ እርምጃ የማይወስደው ሙስና አንዱ የስርዓቱ እድሜ ማራዘሚያ መንገድ በመሆኑ ነው” ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል።
“ኢህአዴግን እያገለገሉ ያሉ ባለስልጣኖች ህወሃትን በሚገባ መከራከር የማይችሉትና በታዛዥነት እያጎበደዱ ለመኖር የሚገደዱት የገቡበትን የሙስና ማጥ ስለሚያውቁት ከተቃወምን እንታሰራለን” በሚል ፍርሃቻ መሆኑን የኮሚሽኑ ባልደረባ ለጎልጉል የአዲስ አበባ ምንጭ ተናግረዋል። ባለሙያው አያይዘውም “በአገሪቱ የተንሰራፋው ሙስና አሳሳቢ ደረጃ ላይ ይገኛል፤ ከላይ እስከታች ተበለሻሽቷል” ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።
“ባለሥልጣናትን በሙስና ማበስበስ” የስርዓቱ ዋንኛ የማኮሰሻና የማዋረጃ ስልት እንደሆነ የተለያዩ ማስረጃዎችን በማጣቀስ “አቶ መለስ የቆፈሩት ጉድጓድ” በሚል ርዕስ ባቀረብነው ቃለ ምልልስ ማስነበባችን ይታወሳል። ኢህአዴግ ለትምህርት ውጪ አገር የላከቸውና ስማቸውን ለጊዜው መግለጽ ያልፈለጉት ተናጋሪ “ስርዓቱ በስብሷል” ባይ ናቸው።
“ባለኝ መረጃ መሰረት የኔ ስጋት እነዚህ ያለቀረጥ የሚነግዱ፣ ገንዘብ የሚያቀባብሉ፣ የገንዘብ ዝውውር ላይ የተሰማሩ፣ ድርጅት ያላቸው፣ በቅጽበት ተመንጥቀው ባለሚሊዮኖች የሆኑ፣ የባንክ ብቸኛ ተጠቃሚዎች፣ ሸቃጮችና አወራራጆች ከትንሽ እስከ ትልቅ ስራውን የሚሰሩት ከባለስልጣናት ጋር ነው። ከመከላከያ አመራሮች ጋር ነው። ከደህንነትና ከዋናው የስልጣን እርከን ጋር በመመሳጠርም ነው” በማለት ቃለ ምልልስ አድራጊው በውል የሚያውቁትን ተናግረዋል። አያይዘውም “ስርዓት ሲበሰብስ ልዩ ምልክቱ ትናንሽ መንግስታት ማቆጥቆጣቸው ነው። በኢህአዴግ መበስበስ አቶ መለስን ጨምሮ በርካቶች ይስማማሉ። ኢህአዴግ መዓዛውን አልቀየረም የሚሉት በአገሪቱ ድፍን ቆዳ ላይ የራሳቸውን መንግስት የተከሉ ተጠቃሚዎች ብቻ ናቸው። እነሱ ክሬሙን እየላሱ ስለሆነ የመበስበስ አደጋ አይታያቸውም። ስለመበስበስ ለማሰብም ጊዜ የላቸውም። የበሰበሰው ነገር ሲናድ የሚበላው ግን አስቀድሞ እነሱን ነው። ምክንያቱም አቶ መለስ የቆፈሩት ጉድጓድ በጣም ትልቅ ነው” በማለት ፍርሃቻቸውን ይገልጻሉ።
የፌዴራል መንግስት የስነ ምግባርና የጸረ ሙስና ኮሚሽን በአገሪቱ የተንሰራፋውን ሙስና በገለልተኛ ወገን አስጠንቶ ያገኘውና ይፋ የተደረገው ውጤት አስደንጋጭ መሆኑ ይታወሳል። በዚሁ ጥናት መሰረት ፖሊስ፣ ፍርድ ቤቶች፣ አጠቃላይ የፍትህ ተቋማትና ራሱ ጸረ ሙስና ኮሚሽን ቀዳሚ ሙስና የተንሰራፋባቸው ተቋማት መሆናቸውን ማረጋገጡ፣ ተቋማቱም በጥናቱ ቅር መሰኘታቸውን በመግለጻቸው በዝርዝር ይቀርባል የተባለው ጥናት እስካሁን ይፋ ሊሆን አለመቻሉም ታውቋል፡፡
የፊታችን አርብ ቃለ መሃላ የሚፈጽሙት አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ እንደ አቶ መለስ የጸረ ሙስና ኮሚሽን ተጠሪነቱ ለእርቸው ስለሆነ አዲስ በሚያቋቁሙት ካቢኔ ውስጥ መካተት የሌለባቸውን የነቀዙ ባለስልጣናት ለመለየት ፋይላቸውን ከኮሚሽኑ መውሰድ እንደሚችሉ ተጠቁሟል።
 

He is responsible for the ethnic cleansing committed in Gambela against Ethiopians (Anuak people). Also ewsponsible for the killings of peaceful protestors in the streets of Addis Ababa, due to his official position as the minister of Federal Affair, which in turn is controls Federal Police Forces


 

 

title

Click to add text, images, and other content

“እንግዲህ ጠቅላይ ሚኒስትሬ ማነው? ኃይለማሪያም አይደለምን…!?” አቤ ቶኪቻው


ሟች ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ (ወይ ጊዜ ድሮ ድሮ አረ የምን ድሮ ከሶስት እና ከአራት ወራት በፊት ብዙዎች መለስን ሲግለፁዋቸው ገዳዩ እና አምባገነኑ እያሉ ነበር። በእርግጥ እኔ እንደዛ ብያቸው አላውቅም። እኔ መለስን ገዳይ ካልኳቸው ግፋ ቢል በሳቅ ይገሉኛል ለማለት ይሆናል እንጂ በግልፅ ይፋ በሆኑ ሪፖርቶች ላይ እንደሚታየው በትንሹ የባድመውን የተሳሳተ ጦርነት ሳይጨምር የሶስት ሺህ ሰዎች ደም በእጃቸው ላይ እያለ ጨክኜ ገዳይ ብያቸው አላውቅም። (በሌላ ቅንፍ ቡቡ እኮ ነኝ!)) የሆነው ሆኖ ጊዜ ደጉ “ገዳይ” ሲባሉ የነበሩትን ሰውዬ “ሟች” እያልን እንድንጠራቸው አድርጎናል። ሞት አይቀርም ከቶ ምንም ታክቱ ምን ቢከተክቱ… ብለን በአዲስ መስመር እንቀጥል።
ሟቹ ጠቅላ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ… በህይወት ዘመናቸው 21 ዓመታት እንዲሁም በአስከሬናቸው ለሶስት ወራት አስተዳድረውን ሲያበቁ አሁን ደግሞ መንፈሳቸው በአዲሱ ሰውዬ ላይ ሆኖ ሊመራን የተዘጋጀ ይመስላል። ትላንት አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትራችን ባደረጉት ንግግር ለትህትና ይሁን የምራቸውን ይሁን እናጃ እንጂ “የኔ ስራ እንደ መለስ ዜናዊ ሆኖ መተወን ነው” አይነት ንግግር ሲናገሩ ሰምተናቸዋል። ይህንን ንግግራቸውን የሰማው የኢሳቱ ደረጄ ሀብተወልድ አንጀት ላይ ጠብ የሚል የአዋቂ ሰው ምክር መክሯቸዋል። ምን አላቸው….?
“ዳዊት ጎልያድን እንዲገጥም ሲላክ የንጉሥ ሳዖልን ካባና ሰይፍ ነበር ያለበሱት። ሆኖም ልኩ አልሆነም።ካባውም ሰፋው፣ሰይፉም መሬት ለመሬት ተጎተተ። በዚያ መልኩ ወደ ጎልያድ ቢሄድ ኖሮ የሚጠብቀው ዕድል ሽንፈት ነበር።ዳዊት ግን -የንጉሥ ካባና ሰይፍ ስለሆነ ብቻ ፤ልኩ ያልሆነን ትጥቅ ታጥቆ ወደ ፍልሚያው መግባት አልፈለገም።ለዚህም ነው የሳዖልን ካባና ሰይፍ አውልቆ በመጣል ወንጭፌን አምጡልኝ!”ያለው።እናም ወንጭፉን አነገተ፤ጠጠር በኮሮጆው ጨመረ። በግ ጠባቂው ዳዊት ራሱን ሆነ። የሚያውቀውንና የተለማመደውን ወንጭፍና ኮሮጆ አንግቶ ጎልያድን ገጠመ።አሸነፈም።”
ደሬ እንዳላቸው አቶ ሃይሌ ከመለስ ካባ እና ሰይፍ ይልቅ የራሳቸውን ወንጭፍ ይዘው ከፊታቸው የሚጠብቋቸውን በርካታ ጎልያዶች ቢሞክሯቸው ይሻላል።
አቶ ኃይለማሪያም ከፊት ለፊታቸው ብዙ ጎልያዶች አሉ። እርሳቸው እና ፓርቲያቸው እንደሚለው ድህነት አንዱ ጎልያድ ነው። የፍትህ ማጣት እንዴት ያለ ጎልያድ እንደሆነ ለማወቅ አንድ ጊዜ ቃሊቲ ወይም ቂሊጦ ኧረ ምን ሩቅ አስኬዳቸው እዝችው ማዕከላዊ ሄድ ብለው ማየት ይበቃቸዋል። ዛሬ በሀገራችን የማንበብ እና የመፃፍ ነፃነት በህገ መንግስቱ ላይ ብቻ ነው ያለው። ይሄም ትልቅ ጎልያድ ነው። መንግስት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም የሚለው የህገ መንግስት ቃል መከበሩን ለማረጋገጥም ወንጭፋቸውን ማሰናዳት አለባቸው። ሙስናም ቢሆን ዋዛ የሚባል ጎልያድ አይደለም።
ዘርዝረን የማንጨርሳቸው በርካታ ጎልያዶች አሉብን እነዚህን ለመፋለም የአቅማቸውን ወንጭፍ ካላዘጋጁ በስተቀር የአቶ መለስን ካባ ለብሰው በአቶ መለስ ሰይፍ ተፋልመው አይችሉትም። ራስዎን መሆን አለብዎ… “ራስን መሆን” የሚል መፅሀፍ ፒያሳ ወይም አራት ሎ አካባቢ አይጠፋም። ከጠፋ ከጠፋ ብሄራዊ እነ ጃፋር ዘንድ መጠየቅ ነው። እንጂ፤ መለስን ለመሆን መሞከር አያዋጣም። እኛም እንጠይቃለን… “እንግዲህ ጠቅላይ ሚኒስትሬ ማነው ኃይለማሪያም አይደለምን!?”

በኢትዮጵያ ላይ እንደ አልቅት ተጣብቆ የህዝቡን ደም እየመጠጠ፣ እየገደለ፣ እያሰቃየና የፈለገውን እያደረገ ለሃያ አንድ ዓመታት በሥልጣን ላይ የቆየው ቅጥረኛው፣ ጎሰኛው፣ አምባገነኑና ዘራፊው የህወሃት አገዘዝ ቁንጮ መለስ ዜናዊ በስልጣን ላይ ቢቆይም ወይም በትረ ስልጣኑን ለሌላ ወያኔ ቢያስተላልፈው፣ አጠቃላዩ የአፈናውና የግፈኛው ሥርዓት ተገርስሶ እስካልወደቀ ደረስ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያመጣው አንዳችም ለውጥ አይኖርም።  ሕወሃቶች ከደደቢት በረሃ ተማምለው የመጡበትን ታላቁንና ለብዙ ዘመናት የኖረውን የኢትዮጵያን ሉዓላዊነቷንና አገራዊ አንድነቷን የማፈራረስና የማዳከም የጥፋት ዓላማቸውን ከሥልጣን እስካልተነቀሉ ድረስ እንደሚቀጥሉበት በሥልጣን ኮርቻ ላይ ከተፈናጠጡበት ጊዜ አንስቶ እየታየ ነው። “ከዝንጅሮ ቆንጆ ምን ይመራርጡ” እንደሚባለው መለስ ዜናዊ በሌላ ወያኔ ቢተካ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያመጣው ምንም ዓይነት ለውጥ አይኖርም።

የህወሃት ቡድን ከመነሻው አንስቶ እስከአሁን ድረስ ከአርባ ዓመታት በላይ የሰራበትን ወደፊትም ለመቀጠል በዕቅድ ይዞ የሚንቀሳቀስበትን መሠረታዊ የኢትዮጵያን ብሔራዊና አገራዊ አንድነት የማፈራረስና የማላላት እኩይ ዓላማ ኢትዮጵያዊያን እስካላስቆሙት ድረስ እንደሚቀጥልበት ምንም ዓይነት ብዥታ ሊኖር አይገባም።  አንዳንድ የዋሆች  የእባቡን የወያኔን ባሕርይ ካለመረዳት እንደሚሉት “መለስ በሌላ ወያኔ ቢተካ የተሻለ ጊዜ ሊመጣ ይችላል” ብለው ሲናገሩ ይደመጣሉ። የወያኔ ድርጅት እንደ ድርጅት አምባገነን፣ ጸረ-ዲምክራሲ፣ አፋኝ፣ ጎሰኛ፣የንጹሃን ደም አፍሳሽና ከሁሉም በላይ ጸረ ኢትዮጵያዊ ነው። ስለሆነም የወያኔን ድርጅት እንደ ድርጅትና ሥርዓት ከኢትዮጵያ ህዝብ ጭንቃ ላይ አወርዶ በማፈራረስ በምትኩ ኢትዮጵያዊ የሆነ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት መተካት እንጅ ወያኔዎችን  አንዱን ወያኔ ከሌላው ወያኔ ጋር በማነጻጸር “እከሌ ከእከሌ” ይሻላል እያሉ ከእውነታው የተለየ ጉንጭ አልፋ ወሬ ማናፈስ፣ ወያኔዎችን መጥቀም እንጅ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ምንም ማለት አይደለም።

በቅርቡ ወያኔመውደቂያው እንደተቃረበ ስላወቀ እንዳበደ ውሻ በመልከፍከፍ  ከፍተኛ ትኩረቱን ያደረገው የሃይማኖት ተቋማትን ማጋየትና ማፈራረስ እንዲሁም ምዕመናንን ማበጣበጥ ላይ ነው። ታሪካዊዎቹን የአሰቦትና የዝቋላ ገዳማት ላይ እሳት በመለኮስ እንዲሁም ጥንታዊውንና ተደፍሮ የማያውቀውን የዋልድባ ገዳምን በመድፈር የመንኮሳትን መካነመቃብር በትራክተር በማረስና ቤተመቅደሶችን በማፈራረስ እኩይ ተገባር ላይ ተሰማርቶ ይገኛል። ሙስሊም ኢትዮጵያዊያንን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥሩ ስር ለማስገባት ወያኔ እንደ ሸቀጥ ከውጭ ባስመጣው “አህባሽ”  በሚባለው የተጭበረበር አስትምህሮት ሐይማታቸውን ለመበረዝና ለመከለስ እንዲሁም የሀገር ፍቅራቸውንና አንድነታቸውን ለማናጋት የሚያደርግባቸውን   ደባ ለማክሸፍ ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን የሕይወት መስዋዕትነት ጭምር እየከፈሉ ይገኛል። ወያኔ ይህ ብቻ ሳይበቃው ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን የሃይማኖታቸውን አስተዳዳሪዎችን እራሳቸው በመስጊዶቻቸው መምረጥ ሲገባቸው ሰርጎ ገብ ካድሬዎችን በማሰማራት ሐይማኖታቸውን በሰላም እንዳያካሂዱ እንቅፋት በመፍጠር ላይ ይገኛል። ሆኖም ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን በአንድ ቃልና ድምጽ በሙስሊምነታቸውና በኢትዮጵያዊነታቸው ወያኔ የሚያደርስባቸውን ግፍና በደል ተጋፍጠው በመመከት ላይ ይገኛሉ። ይህ ሙስሊሞች መብታቸውን ለማስከበር በሰላማዊና ህጋዊ ሁኔታ በማድረግ ላይ ያሉት እንቅስቃሴ ወያኔን  በከፍተኛ ሁኔታ ፍርሃትና መርበትበት ውስጥ ጥሎታል። የሙስሊሞች ጥያቄ ወያኔን እንዲህ ሊያንዘፈዝፈውና ሊያወራጨው  የቻለው ሙስሊሞች እንደ ሙስሊምነታቸውንና እንደ ኢትዮጵያዊነታቸው አንድ  ሆነው በመነሳታቸውና የወያኔን የጎሳ አጥር ሰበረው በመውጣታቸው ነው። ሙስሊሞች እንደ ኢትዮጵያዊ ሆነው ጥያቄያቸውን በአንድነት ባያቅርቡና በተበታተነ ሁኔታ ቆመው ቢሆን ኖሮ ወያኔ “የኦሮሞ ሙሲሞች እንዲህ አሉ” ወይም “የአፋር ሙስሊሞች እንዲያ አሉ” ወይም የጉራጌ ሙስሊሞች ይህንን ጠየቁ ወዘተ” እያለ  እንደለመደው ከፋፍሎ ለመግዛት በሚችልበት ህኔታ ሊያላግጥበትና ለራሱ መጠቀሚያ ሊያደርገው በቻለ ነበር። ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን በዚህ ተጋድሏቸው የኢትዮጵያን ሕዝብ አንድነትና በጎሳ አለመለያየት ለወያኔ ብቻ ላይሆን ለመላው ዓለምም አረጋገጠዋል።ይህም የትግል ሥልት ለወደፊቱ በተጠናከረና በተቀላጠፈ ሁኔታ ሊቀጠልበት የሚገባ በፍጥነት ውጤት የሚያመጣ የትግል ዘዴ ነው።

ኢትዮጵያውያኖች በሙሉ በአሁኑ ሰዓት ጎሳና ሃይማኖት ሳይለዩ ከወያኔ ጋር ከፍተኛ ትንንቅና ፍልሚያ የገቡበትና የሚደርሳባቸውን ጭቆናና የግፍ አገዛዝ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ የህይወት መሰዋዕትነትን ጭምር እየከፈሉ የሚገኙበት ወሳኝ ወቅት ነው። ስለሆነም ኢትዮጵያዊያን ይህንን በኢትዮጵያዊነት የጀመሩትን አንድነት አጠናክረው በመቀጠል ይህንን የበሰበሰ አምባገነንና ፈላጭ ቆራጭ፤ ከላይ እስከ ታች ድረስ ድረስ በምዝበራ፣ በጉቦና በዝርፊያ የተጨማለቀ የባዕዳን ተላላኪ የወያኔን አገዛዝ አሽቀጥረው የሚጥሉበት ጊዜ ቅርብ እንጅ እሩቅ እንደማይሆን ሳይታለም የተፈታ ነው።

ያዲሳባ ባለሥልጣናትና ቀምጣላ ካድሬዎች--ዝግ ቤቶች

ጎልጉል

September 19, 2012 08:28 pm By Editor
“በሬ ለምኔ” የፍየል ቁርጥና ጥብስ መለያ ማስታወቂያ ነው። ከኦሎምፒያ ወደ መስቀልፍላወር በሚወስደው መንገድ ላፓሬዚን አለፍ እንዳሉ ወደ ግራ ሲታጠፉ ያገኙታል። ለጉዳዬ የሚመቸኝን በሬ ለምኔ ላመላክት እንጂ ብዙ “በሬ ለምኔ” ቤቶች አዲስ አበባ ተከፍተዋል። ያዲሳባ ቀምጣላ ካድሬዎች፣ ልማታዊ ባለሀብቶች፣ አቀባባዮችና ባለጊዜዎችና አጫፋሪዎቻቸው እድሜ ለማራዘም ፍየል ይመገቡና ማታ ልቅ የግብረ ስጋ ለማድራት አይጨነቁም።
የሚዘጋባቸው ህጻናት – ዝግ ቤቶችእጠቆምኩት ቤት ስትገቡ ፍየል የሚያገላብጡት የሚታወቁ ባለሥልጣናትና ታዋቂ ካድሬዎች ናቸው። ፍየል ከገባ በኋላ መኪና ተረክ እያደረጉ እዛው ሰፈር፣ ብዙም ሳይርቅ ወይም ቦሌ መሃል፣ ዝግ ቤቶች ይሰየማሉ። አንዱን “ሮዚና” ዝግ ቤት ላስተዋውቃችሁ። ሮዚና ዝግ ቤት ማንም ዘው ብሎ አይገባም። ሮዚና ሲደርሱ እንደ መኖሪያ ቤት ጥሩምባ አሰምተው ከተንበሪውን የሚያስከፍቱ ደንበኞች ብቻ ናቸው። “ደንበኞች” ስል እንግባባለን ብዬ አስባለሁ።
ሮዚና ወገቧ ሸንቃጣ፣ አንጀት የሚባል ነገር ያልሰራባት፣ ዳሌዋ ሰፊና ክብ፣ ሽክ ያለች፣ አንገቷ ውድ ነገሮች የሚቀመጡበት፣ ሽታዋ የሚያውድ፣ ዓይነ ርግቧ በቀለም እንደ ስዕል የሚዋብ፣ ሳሳ ያለ ልብስ የምትለብስ፣ እንግዳዎቿን በምትዘጋባቸው ቤት እየተዘዋወረች የምትቀበል አራዳ ነች። አስተናጋጆቿ በጣም ትንንሽ ልጆች ሲሆኑ ጸሃይ አይነካቸውም። ስራቸው ለሮዚና እንግዶች መስተንግዶ ሳይስተጓጎል መስጠት ነው – የሚጠጣ ያቀርባሉ፤ ፍም እሳት አዘጋጅተው ቡና ያፈላሉ፤ ለማሟሟቂያ የቡናው ስነ ስርዓት በየክፍሎቹ ከተከናወነ በኋላ የጫቱ ሙቀት እየጨመረ ሲሄድ ሺሻ ይለኮሳል። ህጻናቱ ሺሻ እያሞቁ ደንበኞቹን ለማስተናገድ ከቡና ማፍያው በርጩማ ተነስተው ፍራሹ ላይ ሲወርዱ ከአባታቸው ጋር በሰንበት የሚጫወቱ እንጂ የስራ ግንኙነት ያላቸው አይመስሉም። ጫት እየቀነጠሱ፣ ሺሻ እያሞቁ ደንበኛቸውን ባፍ ባፉ መከደም ዋና ስራቸው ስለሆነ ተክነውበታል።
ተጋብዤ የተመለከትኩት ክፍል የነበረችው ልጅ ሪታ ትባላለች። ንግግሯ የቀምጣላ ልጆች አይነት ነው። ስትስቅ አማርኛ አይመስልም። ጠይም ቀለሟ የጸዳ፣ ለጋ ነች። እንደ ጋባዤ አገላለጽ “ጥፍሯ ይበላል”፤ ዕድሜዋ ከአስራ አምስት አይበልጥም። ቡና እንደጨረሰች ስስ ነገር ለብሳ ደንበኛዬ ጎን ቁብ አለች። መቃም ትችልበታለች። ጫት ላኪዎች በትዕዛዝ የሚልኩትን ጫት ትጠጣዋለች። ያለ ምንም ማጋነን የቅጠል አበላሏን ፍየል ብታየው በቅናት ምላሷን ትቆርጠዋለች። ምን አደከማችሁ ቅማ ታቃቅማለች። አልፎ አልፎ ሮዚና ለጉብኝት ብቅ ብላ ስትመለስ ቤቱን ታውደዋለች።
ምርቃናው ሲጨምር ወዳጄ ቀስ በቀስ ከልጅቷ ጋር ተጣበቀ። እጆቹም ሁለመናውም እሷ ላይ ሆነ። በቃ ደረቱ ላይ ጣላት። ደረቱ ላይ አንጋሏት ሺሻውን ይምጋል። ብቸኝነቱ ሊውጠኝ ሲደርስ መሄድ አለብኝ ብዬ ተነሳሁ። ፒኮክ እንደምጠብቀው ነገርኩትና ተለየሁት። ህጻኗን ልጅ ደረቱ ላይ አንጋሏት ስመለከት ልጄን አቅፌ ሳስገሳው ትዝ አለኝ። የሚያስገሳት እንጂ የሚዳራት አይመስልም። እንዲህ ያሉትን ትውልድ አምካኝ ቤቶች ማጥፋት ቀላል ነው። ግን ተጠቃሚዎቹ ህግ አስከባሪና ህግ አወጪዎቹ በመሆናቸው አይታሰብም። አንዳንድ ዝግ ቤቶች በሲቪል ጠባቂዎች የሚጠበቁ ናቸው። አንዳንዴ ቤተመንግስቱንና ሟቹን የቤተመንግስት ነዋሪ ይጠብቁ የነበሩት በፈረቃ ይታደማሉ። ዝግ ቤቶች…
ፒኮክ አፕሬቲቩ ይጥማል። በጫት የጦዙ ማገዶ ላለመጨረስ አፕሬቲቭ ይወጋሉ። መኪና ውስጥ ሆነው የተጣመዱም ይወጋሉ። “ያራዳ ልጅ” በማለት ሳንቲም የሚለምኑ፣ ሎተሪ የሚያዞሩ የጎጃም ጉብሎች፣ የመንገድ ላይ ነዋሪዎች፣ ቀበሌና አድራሻ የሌላቸው ወንድምና እህቶች፣ ኑሮ ያዞራቸው የኑሮ ሰለባዎች ይታያሉ። አዲስ አበባ ሁሉን ተሸክማ እየመሸላት ይነጋል።
አፕሬቲቬን እየቀነደብኩ ስለ ሮዚ ቤት እያሰብኩ ቆዘምኩ። ቤቱ ውስጥ ያሉት ህጻናት የተመረጡ ናቸው። መልምሎ የሚያመጣቸውና ስልጠና የሚሰጣቸው አለ። በህጻንነታቸው ተከትበው ሺሻ ስር ሲርመጠመጡ በዛው ሱስ ይዟቸው ገደል የከተታቸው፣ ኖረውም ተስፋ ያጡ፣ ታመው የፈረደባት እናት እጅ የወደቁ አሉ። አገሩ እንዲህ ሆኗል። የኢትዮጵያ ህዳሴና የኢኮኖሚ እድገት ያተረፈው እንዲህ ያሉትን ዜጎች ነው። በርግጥ አገሪቱ ኢኮኖሚዋ አድጓል። ያደገው ግን ለዝግ ቤት ተጠቃሚዎች እንጂ ለሌሎች አይመስልም። እድገቱ የሚታያቸው በዝግ ቤትና ቤታቸውን ለሌሎች ዘግተው አገሪቱን እያለቡ ላሉት ይመስላል።
በሃሳብ እየቀባጠርኩ፣ አፕሬቲቬን እየሳብኩ ቆየሁ። ወዳጄ ተመችቶታል መሰል አልመለስ አለኝ። ፒኮክ ስለሰለቸኝ ደወልኩለትና እንስራ እንገናኝ አለኝ። ወደ እንስራ አመራሁ። እንስራ ደግሞ ሌላ ትዕይንት አለ።
እንደምን ከረማችሁ… ። አሁን እንስራ ነኝ። እንስራ ለማታውቁ ላስተዋውቃችሁ። እንስራ ቦሌ ቴሌ አካባቢ የሚገኝ የምሽት ንዳድ ቤት ነው። በመለስ ሞት ምክንያት ተፋዞ ከርሞ ነበር። እንስራ ሲገቡ በጡንቸኞች ይዳብሳሉ። ፍተሻ መሆኑ ነው። እንስራ በር ላይ ተዳብሰው ሲዘልቁ ቀለሙ አይን ይወጋል። የደም ጢስ የሚጨስበት ይመስላል። እንስራ ውስጡ በዲጄ ይናጋል፤ ይነዳል። በምድር ቤት ውስጥ የሚደለቀው ሙዚቃ ከተለያዩ አቅጣጫ ከሚፈሰው የተደበላለቀ ቀለም ጋር አንድ ላይ ተዳምሮ የሲኦል ቤተ ሙከራ ይመስላል። መድረኩ ላይ እየተገመዱ የሚላቀቁት ተዋንያኖች እንግዳ ያስደነግጣሉ። ቁመታቸው ረጃጅም የሆኑ እንስቶች የተጠና ዳንስ ይተውናሉ።
እርቃናቸውን ያለ ልብስ የሚናጡት እንስቶች ሃፍረታቸው ላይ የቻይና ማራገቢያ የምትመስል አነፍናፊት ከመለጠፋቸው ውጪ ሁሉም ነገር እንደ አዳምና ሄዋን እንደ ድሮው፣ እንደ ጥንቱ ነው። እርቃን!! ዳንሱ “ብልግና ተኮር” ይባላል። ወገብና መቀመጫን በማላመጥ ሲወዘውዙት ማየት ይመስጣል። “ኮረኮንች” የሚባለው ምንነቱ የማይታወቀውን አልኮል በሉት ዊስኪ እየተጋቱ አብረው የሚያውካኩትን ለተመለከተ አገራችን ውስጥ ችግር በቃል ደረጃም የሚታወቅ አይመስልም።
ከየአቅጣጫው የሚወርደው ባለቀለም ጨረር የሰውነታቸውን ቀለም እንደ እስስት ይቀያይረዋል። እየነደደ ወርዶ የሚቀንሰው ብርሃን ውስጥ ኮሮኮንች ያሳበዳቸው ይዘላሉ። አንዳንዶች መድረኩ ላይ ሳያስቡት ደርሰውበት ዓይናቸውን ከእምብርት በታች ቸክለው ይቅበዘበዛሉ። አንዳንዶች ጥንድ ሆነው መጥተው ብቻቸውን ያሉ ይመስል በሜዳ ላይ ወሲብ መሰል ዳንስ ተማርከው ዓይናቸው ሲቅበዘበዝ አለመስማማት የሚፈጠርበት አጋጣሚ አለ።
ስድስት የሚሆኑት ዳንሰኞች አጎንብሰው መቀመጫቸውን ሲወዘውዙት፣ ተሸብርከው “እንካ፣ አምጣ” ሲሉ፣ ሙዚቃው ሲያቃጥር “የኮረኮንቹ” ኮታ ሳይታወቅ ይበረታል። ከቦሌ አካባቢና ከዩኒቨርሲቲ መንደር የሚዝናኑ መስለው የሚነግዱ በተመሳሳይ ራቁታቸውን ከጊዜያዊ ጓደኞቻቸው ጋር ያስነኩታል። የዩኒቨርሲቲ ጉዳይ ካነሳሁ አንዴ ወደ አንጋፋው የዝሙት ገበያ ናዝሬት ፔንሲዮን ላምራችሁ።
ናዝሬት ፔኒስዮን እንደ ዛሬው ሳይሆን “ሻሞ” የሚባልበት ለሞት መጣደፊያ አልኮል መቸርቸሪያ ባር ነው። ናዝሬት ፔንሲዮን አካባቢው የጫት መቃሚያና የድለላ ስራ እምብርት በመሆኑ ሰው ስፍሩ ነው። ናዝሬት ፔንሲዮን በብዛት የንግድ ስራ ኮሌጅ ተማሪዎች እንደሚታደሙበት አንድ ወቅት መረጃዎች በይፋ ተሰራጭተው ነበር።
በተለይ ከክፍለሃገር የሚመጡ ተማሪዎች ከመንግስት የሚሰጣቸው ወርሃዊ ድጎማ ለቀለብና ለማደሪያ ስለማይበቃቸው ናዝሬት ፔንሲዮን ለስራ መሰማራታቸው ያደባባይ ወሬ ነበር። “ይሞታል ወይ?” ያለች ተማሪም ነበረች። ውዱ መሪያችን፣ ነብሳቸውን ይማረውና፣ ስጋቸውን እየሸጡ የሚማሩ ተማሪዎችን አስተዋውቀውናል። እኚህ መሪያችን ናቸው “ልማታዊ ሴቶችን አፈሩ፣ ለሴቶች ልዩ ትኩረት አዘነቡ” የሚባሉት፣ እየተባሉ ያሉት። የኮሜርስ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በተለይ ወደ ሀዋሳና አርባ ምንጭ ችግሩ ያስከተለው ቀውስ ቤተሰብን አንገት ማስደፋት የደረሰበት ደረጃ ደርሷል።
ቤተሰብ ልጄ ተምራ ተመረቀች ብለው ሲጠብቁ አጅሬው የቀሰፋቸው ጥቂት አይደሉም። ሃዋሳ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና የቡና ቤት ኮማሪቶች በ”ገበያዬን” ወሰድሽብኝ ከፍተኛ ጸብ ውስጥ ሲገቡ ማየት የተለመደ እንደሆነ ሀዋሳ በነበርኩበት ወቅት ያስተዋልኩትና ያረጋገጥኩት ጉዳይ ነው። አንዴ እኔው ራሴ አብራኝ እንድትጠጣ ለጋበዝኳት ልጅ ይህንን ጥያቄ አቅርቤላት “ገበያችንን ዘጉት” በማለት የስድብ ናዳ እያወረደች ነበር ሁሉንም ያጫወተችኝ – ተማሪዎቹን ማለቷ ነበር። የሴቶች ተሳታፊነት አደገ ይሏል እንዲህ ነው። ነብስ ይማር።
ወደ እንስራ ልመልሳችሁ። እንስራ ጥቂት እንደቆየሁ ወዳጄ ያችኑ ልጅ አንጠልጥሎ መጣ። መጨለጥ ቀጠለ። አስቀድሞም ሲጠጣ ስለቆየ ለመስማት ጊዜ አልወሰደም። እንደውም እንደ አዲስ ጀበና መንተክተክ ጀመረ። ህጻኗን ከፊትለፊቱ ወትፏት በቁሙ እንደውሻ ይቀነዝራል። መብራቱ ስለሚመች ስጋት የለም። በቁሟ በዳንስ እያስመሰለ ፈትጎ ሊገላት ምንም አልቀረም። ይህ ሰው ያለውን ኃላፊነት እዚህ ከሚያደርገው ተግባሩ ጋር በማገናዘብ ሳስበው አመመኝ። እንዲህ ያሉ ብዙ “ትልልቅ ሰዎች” ይመሩናል። በችጋር ይጠብሱናል። ሲሞቱ በደቦ ያስለቀሱናል። በጀት ከልክለው በረሃብ ያቃጥሉናል። ሲሞቱ ደግሞ በጀት መድበው ደረት ያስመቱናል። “ያገራችሁን ህዳሴ ከእኛ ጠብቁ” እያሉ ያለ ሃፍረት ይሰብኩናል። አጽማቸውን እናመልክ ዘንድ ይመኛሉ። ከወዳጄ ጋር የትና እንዴት እንደተገናኘን አስታውቃለሁና ተረጋጉ። አሁን በፈጣሪ እጅ ላይ ሆኖ እየኖረ እንደሆነ፣ ከቤቱም እንደማይወጣ ሰምቻለሁ። ሮዚ አራዳዋ አለች እንዳማረባት። ህጻናቱ ግን … ።

ከ2ዐዐ2 ምርጫ ዋዜማ ጀምሮ አሁንም ድረስ ያልበረደ የምርጫ ሥነ-ምግባር ደንበ (ለነገሩ ህግ ነው) ለምን አትፈርሙም ከኢህአዴግ የሚቀርብ ያልተቋረጠ ጥያቄ ነው፡፡ ይህንን እንከን የለሽ የምርጫ ሥነ- ምግባር ደንብ ካልፈረማችሁ ንግግር ብሎ ነገር የለም በማለት በፓርላማ ቀርበው ጠቅላየ ሚኒ&

ከ2ዐዐ2 ምርጫ ዋዜማ ጀምሮ አሁንም ድረስ ያልበረደ የምርጫ ሥነ-ምግባር ደንበ (ለነገሩ ህግ ነው) ለምን አትፈርሙም ከኢህአዴግ የሚቀርብ ያልተቋረጠ ጥያቄ ነው፡፡ ይህንን እንከን የለሽ የምርጫ ሥነ- ምግባር ደንብ ካልፈረማችሁ ንግግር ብሎ ነገር የለም በማለት በፓርላማ ቀርበው ጠቅላየ ሚኒስትር መለስ ዜናዊም ተናግረዋል፡፡ አሁንም ሌሎች እየነገሩን ያሉት ቃል በቃል ይህንኑ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትራችን ከመድረክ ጋር ላለመደራደር፣ ላለመወያየት ይህ ምክንያት እስካለ ድረስ ሌላ መፈለግ አይጠበቅባቸውም፡፡ ስለዚህ ጉዳይ ለሕዝብ ዝርዝሩን ማሳወቅ ተገቢ ስለሆነ ዘሬ በዚህ ጽሑፍ ለመዳሰስ ተሞክሯል፡፡

ለመነሻነት ግን ስለ ምርጫ ሥነ-ምግባሩ ደንብ አጠር ያለ አስተያየት ቢሰጥ ጠቃሚ ይሆናል፡፡ እርግጥ ነው የምርጫ ሥነ-ምግባሩ የተዘጋጀው ሲውዲን አገር በሚገኘው International Institute for Democracy and Electoral Assistance በአጭሩ International IDEA በሚለው ድርጅት ነው፡፡ ሰነዱ የተሟላ ይሆን ዘንድ ሁለት ክፍሎች ይጎሉታል፡፡ አንዱ Code of Conduct for the Ethical and Professional Observation of Election (የምርጫ ታዛቢዎች የሥነ-ምግባር ደንብ) ሲሆን ሌላው ደግሞ Code of Conduct for the Ethical and Professional Administration of Elections (የምርጫ አስተዳደር የሥነ ምግባር ደንብ) የሚሉ ናቸው፡፡ ሦስት ክፍሎች ከአሉት ሰነድ አንዱን ብቻ ለይቶ ፈርሙ ማለት በራሱ ገና ከመነሻው ችግር ያለበትና እንከን እንዳለው በግልጽ የማያሳይ ነው፡፡ ለምርጫው ነፃና ፍትሓዊ መሆን ሦስቱም ክፍሎች ከፍተኛ ሚና አላቸው፡፡ በተለይም ያልተካተቱ ሁለት ክፍሎች ከምርጫ ሥነ ምግባሩ በተሻለ ሁኔታ ለምረጫው ፍትሓዊነት አስተዋጽኦ ያደርጋሉ፡፡ ኢህአዴግ እንደ ፓርቲ ሁለቱን ሰነዶች ትቶ በአንዱ ላየ ብቻ እንፈራረም የማለት መብት የለውም፡፡ ሊኖረውም አይገባም፡፡

በመሠረቱ መድረክ በሥነ-ምግባር ደንቡ ላይ አልነጋገርም አልፈርምም አላለም፡፡ ተደራዳሪ ስለነበርኩ ጉዳዩን ጠንቅቄ አውቀዋለሁ፡፡ የሥነ ምግባርን ደንብ መፈረም የሚጠቀም ከሆነ ዋናው ተጠቃሚ መድረክ ነው፡፡ ምክንያቱም በጽሑፍ ደረጀ ከሆነ የምርጫ ሥነ ምግባሩ ዋና ዓላማ ምርጫው ግልጽ፣ ነፃ ሠላማዊ ህጋዊና ዴሞክሪሱያዊ ሆኖ በሕዘብ ተቀባይነት እነዲያገኝ ለማስቻል ነው ስለሚል፡፡ ታደያ ነገሩ ሁሉ የእውነት ከሆነ መድረክ ከዚህ ሰነድ መፈረምና በተግባር መተርጎም በላይ የሚፈልገውና የሚያስደስተው ምን ነገር ሊያገኘ ነው አልፈርምም የሚለው? መድረክ ከምርጫ 2ዐዐ2 በፊት ጀምሮ በተደጋጋሚ ከኢህአዴግ ጋር ለመደራደር ጥያቄ አቅርቧል፡፡ በተለይም የኡትዮጵያ አጋር ቡድን (Ethiopian Partners Group) ከተባለው የበርካታ አገሮች ዲፕሎማቶች ስብስብ ጋር በዚህ አጀንዳ ዙሪያ ተደጋጋሚ ውይይቶች አካሂዷል፡፡ የመድረክ ጥያቄ ግልጽና አጭር ነበር፡፡ ከምርጫ ሥነ-ምግባሩ በተጨማሪ የ2ዐዐ2 ዓም ምርጫን ነፃና ፍትሓዊና ተአማኒ ሊያደርጉ በሚችሉ ሌሎች ወሳኝ ጉዳዮች ላይም እንደራደር ነው ያለው፡፡ የጉዳዮቹን ዝርዝር መድረክ ነሐሴ 22 ቀን 2ዐዐ1 ዓም ጳግሜ 4 ቀን 2ዐዐ1 ዓም መስከረም 25 ቀን 2ዐዐ2 ዓም ለኢህአዴግ በፃፈው ደብዳቤ ግልጽ አድርጓል፡፡ ኢህአዴግ ግን እንደ ፓርቲ ከሌለው ሥልጣን ውጭ እኔ ካቀረብኩት አጀንዳና ከያዝኩት የድርድር ስልትና አካሄድ ውጭ መነጋገር አይቻልም አለ፡፡ ታማኝ ተቃዋሚዎችና የተቃዋሚዎች ተቃሚዎችን ይዞ መድረክን አግሎ የምርጫ ሥነ-ምግባሩ ተፈረመ፡፡ ቆየት ብሎም የሥነ ምግባሩ ደንብ በፓርላማ ፀድቆ አዋጅ ሆኖ በነጋሪት ጋዜጣ ወጣ፡፡ በማንኛውም መመዘኛ የሥነ ምግባር ደንቡን ፈርሙ ድራማ እዚህ ላይ መቆም ነበረበት፡፡ ምክንያቱም መደረክ ሆነ አባል ፓርቲዎች እንደ ሕጋዊና ሠላማዊ ድርጅቶች የአገሪቱን ሕግ ተቀብለውና አክብረው ነውና የሚንቀሳቀሱት፡፡ አምርረን የምንቃወማቸውንም ፀረ-ሽብርተኛ ሕግ፣ የሚዲያና የመረጃ ነፃነት ሕግ፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሕግ ሆኑ ሌሎች ሕጎችን የምንታገለው በሕገ መንግሥቱ ማዕቀፍ ውስጥ ነው፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የአገሪቱ ሕገ ሆኖ በወጣ ሕግ ላይ የመፈረም መብትም ግዴታም የለባቸውም፡፡ ፈርሙ ከተባለ ደግሞ ለምን በሌቹ በፖርላማ ፀድቀው በሚወጡ ሕጎች ላይ እንዲፈርሙ አልተጠየቁም፡፡ ጉዳዩ መድረክን የማንበርከክ የአሸናፊነት ሥነ ልቦና ስሌት ነው፡፡ ድርድር ግን የጋራ ተጠቃሚነት (Win-Win) ስሌት ነው፡፡

ስለ የምርጫ ሥነ-ምግባሩ ደንብ ስንነጋገር ሌሎችም መነሳት ያለባቸው ነጥቦችም አሉ፡፡

አዋጅ ቁጥር 532/1999 አንቀጽ 1ዐ5 ለምርጫ ቦርድ የሚሰጠው መብት በግልጽ ተቀምጧል፡፡ ‹‹ቦርዱ የሚመለከታቸውን አካላት በማማከር ነፃና ፍትሓዊ ምርጫ ማከናወን የሚያስችሉ ሁኔታዎችን የሚያመቻች ተጨማሪ ዝርዝር የምርጫ ደንብ ሊያወጣ ይችላል›› ይላል፡፡ በመሆኑም ኢህአዴግ በምርጫ ሥነ-ምግባሩ ዝግጅተ ወቅት የፈፀመው ተግባር የምርጫ ቦርድ ሥራን መንጠቅ ነው፡፡ ለዚህም ነው ደንብ ተብሎ የተዘጋጀውን አዋጅ አድርጎ በም/ቤት ማፀደቅ ያስፈለገው፡፡ ይህም የሚያሳየው ዘግይቶም ቢሆን ለአቀደው ድብቅ ዓላማው ማስፈፀሚያ ሲል የተጠቀመበት አካሄድ መሆኑ ነው፡፡ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድም እንደተለመደው ሁሉ በሕግ የተሰጠውን ሥልጣን በአግባቡ ባለመጠቁሙ የዋነኛ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ችግር አባብሶታል፡፡ ለነገሩማ ተጋኖ የሚነገርለት የምርጫ ሥነ-ምግባሩ ደንብ ሲታይ ምርጫ ቦርድ በምርጫ ሕጉ አንቀጽ 1ዐ1 እስከ 1ዐ5 ባሉት የምርጫ ሥነ ምግባር መርሆዎች ከአስፈረውና ለፓርቲዎች ካሰራጨው ሰነድ ብዙም የተለዬ ቁም ነገሮችን ያልያዘ ነው፡፡
International IDEA የተሰኘው ድርጅት የምረጫ ሥነ-ምግባሩን ደንብ የሚመለከተው በተለያየ ሁኔታ ነው፡፡ የሥነ-ምግባሩ ደንብ በምርጫ ወቀት ብቻ ሊያገለግል የሚችል ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል፡፡ በአማራጭ ከምርጫው ቅስቀሳ ጀምሮ ውጤቱ እስከሚገለጽበት ጊዜ ብቻም ሊሆን ይችላል፡፡ በጊዜ ገደበ የሚያለግል ማለት ነው፡፡ የአገሪቱ የመርጫ ህግ አካል ሆኖም ሊወጣ ይችላል፡፡ በምርጫ ሥነ ምግባሩ የሚጠቀሱት ጥፋቶች በአገሪቱ በወጡ የተለያዩ ሕጎች አማካኝነትም ሊዳኙ ይችላሉ፡፡
የምርጫ ሥነ-ምግባሩ ደንብ በዋናነት የሚያተኩረው ለምርጫ ዘመቻ ጥቅም ላይ ስለሚውል ቋንቋ ይዘት፣ ስለ ማስፈራራትና አመጽ ስለመቀስቀስ፣ ስለ ፓርቲዎች ምልክቶች፤ ለመራጭ መደለያ ስለመስጠት፣ አለመግባባቶች ስለሚፈቱበትና ስለ አቤቱታዎች አቀራረብ ወዘተ ነው፡፡ ስለሆነም ኢህአዴግ ልዩ ቦታና አቅም ያለው የሚያስመስለው የሥነ-ምግባር ደንብ በጣም የተጋነነ ከመሆኑም ባሻገር ይህ ነው የሚባል ትርጉም የሚሰጠው አይደለም፡፡ አጀንዳ ለማስለወጥ ካልሆነ በስተቀር፡፡
የምርጫ ሥነ-ምግባሩ አመጣጥ ይዘት ጠቀሜታና ሕግ ሆኖ በአዋጅ መውጣቱን ስንመለከት አንድ ተገቢ፣ አሳሳቢና መሠረታዊ ጥያቄ ለመጠየቅ እንገደዳለን፡፡ ለመሆኑ ኢህአዳግና በአሱ የሚመራው መንግሥት መድረክን የሥነ-ምግባሩን ደንብ ካልፈረማችሁ አንደራደርም አንወያይም የጋራ ጉዳይም የለንም የሚለው ለምንድ ነው? የሚለውን ማለት ነው፡፡
የዚህ ጥያቄ መልስ ቀላልም ግልጽም ነው፡፡ ለመሻነት ግን ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ‘’ African Development: Dead Ends and New Beginnings’’ በተባለው ጽሑፋቸው ያሰፈሩትን መመልከት ይገባል፡፡

‘’Developmental Policy is unlikely to transform a poor country into a developed one within the time frame of the typical election cycle. There has to be continuity of policy if there is to be sustained and accelerated economic growth. In democratic polity uncertainty about the continuity of policy is unavoidable. More damagingly for development, politicians will be unable to think beyond the next election e.t.c it is argued therefore that the developmental state will have to be undemocratic in order to stay in power long enough to carry out successful development’’ (ሰረዝ የራሴ) ትርጉሙም በግርድፉ የልማት ፖሊሲዎች በአንድ የምርጫ ዘመን ውስጥ ደሀ አገርን ወደ ሀብታም አገር ሊለውጥ አይችልም፡፡ የተፋጠነና ዘላቂ የኢኮኖሚ እድገት ለማምጣት የፖለሲዎች ቀጣይነት አሰፈላጊ ነው፡፡ በዴሞክራሲያዊ አስተዳደር የፖሊሲዎች ቀጣይነት ማጣት ደግሞ የሚያስወግዱት ነገር አይደለም፡፡ ለልማት ትልቁ አደጋና ጥፋት ደግሞ የፖለቲከኞች ከሚቀጥለው የምርጫ ዘመነ በአሻገር መመልከት አለመቻላቸው ነው፡፡ ስለዚህ አንዱ ክርክር ልማታዊ መንግሥት የተሳካ እድገት ለማምጣት ይችል ዘንድ ኢ-ዴሞክራሲያዊ በመሆን የተፈለገውን የተሳካ ልማት ለማምጣት እስከሚያስችለው ጊዜ ድረስ በሥልጣን ላይ መቆየት ያስፈልጋል የሚል ነው፡፡ (ሰረዝ የራሴ)፡፡

ዋናው መመሪያና አቋም ይህና አብዮታዊ ዴሞክራሲ ሆኖ ሳለ ታዲያ ከምን ሥነ-አመክንዮ (logic) ወይም ምክንያት ተነስቶ ነው ኢህአዴግ የምርጫ ሥነ ምግባሩን ፈርሙ የሚለው፡፡ እረ እንዲያውም ምርጫ ማካሄድስ ለምን ያስፈልጋልል? እዚህ ላይ ተረስተው ከሆነ ማስታወስ ያለብን ቁም ነገሮች አሉ፡፡ በ1997 ዓም ምርጫ ወቅት እኮ በኢህአዳግና በተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል የምርጫ ሥነ ምግባር ሰነድ ተፈርሞ ነበር፡፡ ምርጫውን በፍፃሜው ከታየው ቀውስ አላዳነውም እንጂ፡፡ በ2ዐዐ2 ዓም ምርጫ ወቀትም የሥነ ምግባሩን ደንብ ከፈረሙት ፓርቲዎች መካከል ዘግይቶም ቢሆን ደንቡን መፈረሙ ከችግር ስለአላዳነው መኢአድም ከስምምነቱ እራሱን ማግለሉ ይታወቃል፡፡ እንዲያው ለነገሩ ሁለትን አጋጣሚዎች አነሳሁ እንጂ የአገሪቱ ሕጎች ሁሉ የበላይ የሆነው ሕገ መንግሥት ላለፉት ሃያ ዓመታት እንደተፈለገው እየተጣሰ አይደለም ወይ? በቅን መንፈስ (in-good-faith) ለአገር፣ ለሕዝብ፣ ለታሪክ ታምነን ካልሰራን በስተቀር በአሁኑ ጊዜ ምንም ዓይነት ሰነዶች ቢፈረሙ ከኢህአዴግ ጥቃት ያድናሉ ማለት ሞኘነት ብቻ ሳይሆን ኢህአዴግንም አለማወቅ ማለት ነው፡፡

የምርጫ ሥነ-ምግባሩን ፈርሙ ጥያቄን በብዙ መልኩ ማየት ይቻላል፡፡ በአንድ መልኩ ሲታይ ኢህአዴግ ከ1997 ዓም ምርጫ በኋላ በግልጽና በጉልበት ሲመቸውም በስልት የሚያካሄደው የመድብለ ፓርቲ ዴሞክሪሱ ቅልበሳ አካል ነው፡፡ ለሠላማዊ ሕጋዊ ፖለቲካና ለመድብለ ፓርቲ ፖለቲካ ግንባታ ያለው ከፍተኛ ጥላቻ አካልም ነው፡፡ በአጠቃላይ መድረክን አስፈላጊ መስሎ ሲያገኘው አባል ፓርቲዎችን ነጥሎ ፀረ-ሠላም፣ ፀረ-ሕዝብ ሽብርተኞች፣ የሻዕቢያ ተላላኪ ወዘተ ብሎ የማጥቂያ ስልቱ አካል ነው፡፡ በመርህ ደረጃ ተቃዋሚ ፓርቲን መፍቀድ በተግባር ግን ለኢህአዴግ አስጊ የሚባሉ ፓርቲዎች ውጤት አልባ እንዲሆኑ የማኮላሸት አካሄድ አካል ነው፡፡ ወዳጆቻችን ይህንን ስትረዱት ጠ/ሚኒስትሩም ሌላ ምክንያት ማዘጋጀት የግድ ይላቸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአንድ ወቅት እንደተናገሩት ‹‹ተቃዋሚዎች እግር እስኪያወጡ እንጠብቃለን እግር ሲያወጡ ግን አንቆርጣለን›› ያሉት አነጋገር አካል ነው፡፡ ሀቀኛ ተቃዋሚዎችን ተቀባይነትና ተደማጭነት የማሳጣትና ከሕዝብ የመነጠል ድርጊት አካል ነው፡፡

በሌላ በኩልም ሁኔታው ከአብዮታዊ ዴሞክራሲ መርህ አንፃርም ይታያል፡፡ በምርጫ ላይ የተመሠረተ አምባገነናዊ ሥርዓት (Electoral Authoritarian) የመፈጠር መርህ አካል ነው፡፡ አብዮታዊ ዴሞክራሲ የይስሙላ ደሞክራሲ ነው፡፡ ለመኖር የሚፈቀድላቸው ፓርቲዎች የአጋርነት ሚና ወይም የማስመሰል ሚና የሚጫወቱ የምርጫ ጨዋታዎችን የሚያሳምሩ ሕልውና የሌላቸው አሻንጉሊቶች ብቻ ናቸው፡፡ የአውራ ፓርቲ አገልጋይ መሆን አለባቸው፡፡ ጠንካራነትና ተቀናቃኝነትን አይፈቅድም፡፡ ድርጊቱ በተግባር የአንድ ፓርቲ ሥርዐት የመፍጠር እንቅስቃሴ አካል ነው፡፡ እስከአሁን ካልተፈጠረ ማለት ነው፡፡ የኢህአዴግ አብዮታዊ ዴሞክራሲ የዴሞክራሲ አዋላጅ ዋና መሣሪያ የሆነውን ነፃና ፍትሓዊ ምርጫን አይቀበልም፡፡ በአፍሪካ ተሞክሮ ላይ ጥናት ያካሄዱ ዲያመራድ የተባሉ ምሁር ፍሪደም ሀውስ (Freedom House) በተባለው ተቋም ጥናት ላይ በመመርኮዝ የአፍሪካን መንግሥታት አራት ቦታ ላይ ይመድቧቸዋል፡፡ እኚሁ ምሁር ኢትዮጵያን የመደቡት በይስሙላ ዴሞክራሲ (Pseudo-Democracy) ምድብ ውስጥ ነው፡፡ ዓለም አቀፍ ደረጃን ያልጠበቁ የመድብለ ፓርቲ ምርጫዎችን ለይስሙላ የሚያካሂዱ ማለት ነው፡፡ ዋና ዓላማውም አንድን አምባገነን ፓርቲን ለረጅም ጊዜ ሥልጣን ላይ እንዲቆዩ ለማድረግ ሲሆን በሌላ በኩልም ፈላጭ ቆራጭ አገዛዞች በዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ፊት ተቀባይነት እንዲያኙና የተሻለም ገጽታ እንዲኖርራቸው ለማድረግ ነው፡፡ ‘’Index Politics ’’ በ2ዐ1ዐ ባወጣው የዴሞክሪሱ ደረጃ Democracy index-The Economist Intelligence unit 60 መመዘኛዎችን ተጠቅሞ ኢትዮጵያን በአምባገነንነት ሥርዓት ውስጥ ያለች አገር ብሎ መድቧታል፡፡

በሌላ በኩል ሲታይም ኢህአዴግ አንዳንዴ በግልጽ ሌላ ጊዜ በተዘዋዋሪ ልማትንና የዴሞክራሲን ትስስርና ቁርኝት ለማደብዘዝ እንዲያውም ለመለያየት የሚያደርገው እንቅስቃሴ አካልም ነው፡፡ እራሱን ልማታዊ መንግሥት ብሎ በመሰየም ዋናው የአገራችን ችግር የልማት፣ የዳቦ ጥያቄ ነው የሚለው አካሄድ አካል ነው፡፡ ይህም ዴሞክራሲን ለማኮላሽት የሚቀጠምበት ስልቱ አካል ነው፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ግን ዓመታት የፈጁ ስለ ዴሞክራሲ የተደረጉ በርካታ ጥናቶች የሚያሳዩት እውነታዎች አሉ፡፡ በዴሞክራሲያዊ የፖለቲካ ሥርዓትና የኢኮኖሚ እድገትና ልማት መካከል ቀጥታ ግንኙነት አለ፡፡ እንደያውም ሁለቱ አይለያዩም ማለት ይቀላል፡፡ ዴሞክራሲ ልማትን ያሳድጋል ሲባል ምን ማለት እንደሆነ ግልጽ መሆን አለበት፡፡ ዴሞክራሲ ለኢኮኖሚ እድገትና ለልማት የሚያስፈልጉ የፖለቲካ ተቋማት በጥሩ ሁኔታ እንዲሰሩ ያደርጋል ማለት ነው፡፡ የሕግ የበላይነት ይከበራል፣ የግለሰቦች ሰብዓዊና የሲቪል መብቶችና ነፃነቶች ይከበራሉ፣ መልካም አስተዳደርን ያሰፍናል፡፡ የነፃ ገበያ ሥርዓትን ያረጋግጣል፣ ሙስናን ይከላከላል ማለት ነው፡፡ የሕግ የበላይነት መከበር ለእድገትና ልማት ወሳኝና ቁልፍ ጉዳይ ነው፡፡ የሕግ የበላይነት መሠረቱ ደግሞ የዴሞክራሲያዊ ተቋማት መኖር ነው፡፡ ይህም መድበለ ፓርቲ ሥርዓትን፣ ነፃና ፍትሓዊ ምርጫን፣ ነፃ የብዙሃን መገናኛዎችን መኖርና በብቃት መስራትን ያካትታል፡፡

በሌላ አንፃር ሲታየ ደግሞ አምባገነናዊ ሥርዓት ለንብረት ባለቤትነት አደገኘነት አለው፡፡ ኪራይ ሰብሳቢነት (በኢህአዴግ ትንታኔ) የተወጠናወተው ነው፡፡ የሕግ የበላይነትን አያሰፍንም፡፡ አምባገነኖች በታሪክም ሆነ ዛሬ የሚታወቁት የመንግሥት ሥልጣን ጠቅልሎ በመያዝና ከዚህም የሚመነጨውን ጥቅማ ጥቅሞች ለራሳቸውና ደጋፊዎቻቸው በተለይም በሥልጣን ላይ እንዲቆዩ የሚረዱዋቸውን በማበልፀግ ነው፡፡ ሙስና የተንሰራፈበት ሥርዓት ነው፡፡ የነፃ ገበያን ያዛባሉ በመሆኑም ለልማትና ለእድገት አመቺ አይደለሙ ብቻ ሳይሆን ፀር ናቸው ማለት ይቻላል፡፡ ታዲያ በልማታዊ መንግሥት ስም እየተፈፀመ ያለው ፀረ-ልማትና እድገት ሥራዎች ናቸው፡፡ ልማትና እድገት ያመጣ መንግሥት ወይም ገዢ ፓርቲ ምርጫን ለማሸነፍ ሕዝብን ማስፈራራት፣ ሕዝብን በአንድ ለአምስት መጠርነፍ፣ ተቃዋሚ ፓርቲዎችንና አባሎቻቸውን ማሰር ማዋከብ፣ ሕዝባዊ ስብሰባዎች በስልትና በዘዴ መከልከል፣ የምርጫን ሥርዓት ሚሰጥራዊነት ለማሳጣትና የቡድን ሥራ ማድረግ አያስፈልገውም ነበር፡፡

በአጠቃላይ የምርጫ ሥነ-ምግባር ደንብ ፈርሙ ድራማ ምክንያቱ ግለጽ ነው፡፡ ኢህአዴግ ሥልጣን ላይ ለመቆየት (ስንት ዓመት እንደሆነም የሚታወቅ አይመስልም)

ኢ-ዴሞክራሲያዊና ኢ-ሕገ-መንግሥታዊ አሠራር የመጠቀም ስልቱ አካል ነው፡፡ ጽሑፌን በቀድሞ የአሜሪካን ፕሬዚደንት ጆን.ኤፍ.ኬኔዲ አነጋገር አጠቃልላለሁ፡፡ ‘’Those who make peaceful revolution impossible will make violent revolution inevitable’’ ከሞላ ጎደል ሲተረጎም ሠላማዊ ለውጥን የማይቻል የሚያደርጉ ሰዎች የአመጽ ለውጥን የማይቀር ያደርጉታል ማለት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሁኔታ ሲታይ ደግሞ የሚያስፈልጋት ሠላማዊና ሕጋዊ ለውጥ ነው፡፡ አገራችን ደግሞ በብዙ ችግሮች የተተበተበች ናት፡፡ ስለዚህ መፍትሔው የምርጫ ሥነ-ምግባር ፈረሙ አይደለም፡፡ ጉዳዩ ከምርጫ በላይ ነው፡፡ ጉዳዩ ከሥልጣን በላይ ነው፡፡ ጉዳዩ የአገርና የሕዝብ ጉዳይ ነው፡፡ ጉዳዩ የታሪክም የሕግም ተጠያቂነት የሚያስከትል ነው፡፡ ስለሆነም ዛሬም ከረፈደም ቢሆን ኢህአዴግና እሱ የሚመራው መንግሥት በሰከነ አዕምሮና ኃላፊነት በተሞላበት ሁኔታ የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባናል ከሚሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎችና ሌሎች ባለድረሻ አካላት ጋር ቅድመ ሁኔታ የሌለው ድርድርና ውይይት ማድረግ አለበት እላለሁ፡፡ ወይም ከሥነ ምግባር ደንቡ የተለየ በቂ ምከነያት መፈለግ ይኖርበታል፡፡ የሚያገናኘን፣ የሚያወያየን የጋራ አጀንዳ የለንም ማለት ጠቃሚም ተገቢም አይደለም፡፡ የጋራ አገር አለን፣ የሕግ የበላይነትና የመልካም አስተዳደር ከፍተኛ ችግር አለብን፣ አብዛኛው ሕዝብ በድህነት እየማቀቀ ጥቂቶች የሚበለጽጉባት፣ የሚንደላቀቁባት አገር ውስጥ ነን ያለነው፣ የሰብዓዊና የዴሞክራሲ መብቶች ጥሰት ተንሰራፍቷል፣ የብዙሃን መገናኛ አውታሮች የአንድ ፓርቲ መገልገያዎች ሆኗል፡፡ ነፃ ፕሬስ በሞት አፋፍ ላይ ነው፣ ቅድመ ሳንሱር በጓሮ በር እየመጣ ነው፣ የአሜሪካ ድምጽና የጀርመኝ ሬዲዮኖች እየታፈኑ ነው፡፡ የቡድኖች የመጨቆን ስሜት የመከፋት ስሜት እየጨመረ ነው፣ ሙስና ተንሠራፍቷል፡፡ ወ.ዘ.ተእነዚህ ጉዳዮች እንድንወያይ፣ እንድንነጋገር ካነሱ ሊያወያዩን የሚችሉ ጉዳዩች ምን ሊሆኑ ይችላሉ? አገራዊ መግባባትና እርቀ ሠላም መፈጠር አለበት፡፡ ይህ ሳይሆን ቀርቶ ኢህአዴግ በለመደው የግትርነት አቋሙ ቀጥሎ እንደ ሁልጊዜው ሁሉ ‹‹ ሁለም ነገር የሚከለሰው፣ የሚለወጠው፣ በመቃብሬ ላይ ነው›› የሚል ከሆነ ይህው ይፈፀም ዘንድ የግድ ይሆናል፡፡

(ከአስራት ጣሴ የአንድነት ዋና ፀሐፊ)

በፍትሕ ጋዜጣ ሰኔ 22 ቀን 2ዐዐ4 ዓም የወጣ ጽሁፍ

ኢትዮጵያን እግዚአብሔር ይባርካት! ይጠብቃትም !

title

Click to add text, images, and other content

#Ethiopia, #StopCensorship: ሳንሱር እና ሕግ፡ ከትናንት እስከዛሬ--

ዘላለም ክብረት

 

 

 

የሰው ልጅ ሐሳቡን ለሌላው መግለጽ መጀመሩ ሰዎች የጋራ ባሕርያትን ይዘው ወደ አዲስ ስልጣኔ፤ ወደ አዲስ ሕይወት እንዲወጣ አድርጎታል፡፡ ነገር ግን የዚህ ትስስር ድንበር የለሽ መሆን ጉዳት አለው በማለት፤ በተለያዩ ወቅቶች በተለያዩ ምክንያቶች መረጃን የመለዋወጡ ሂደት ገደብ እንዲኖረው ይደረጋል፡፡ ገደብ እንዲደረግ የሚያስገድዱት ዋነኛ ምክንያቶች ሦስቱን ዋነኛ ተቋማት መጠበቅ በሚል ሐሳብ ስር ይጠቃለል፡፡

 

እነዚህም ተቋማት ቤተሰብ፣ ቤተ እምነት እና ቤተ መንግሥት ናቸው፡፡ ቤተሰብን መጠበቅ ስንል ቤተሰብ የኅብረተሰብ መሠረት በመሆኑ ቤተሰብን እና ስርዓቱን የሚጎዱ ነገሮች (Obscene) በአደባባይ እንዳይኖሩ ማድረግ ማለታችን ነው፡፡ ቤተ እምነትን የሚያጎድፉ ነገሮችም (Blasphemous) እንዲሁ:: እንዲሁም በሦስተኝነት በሕግ የተዘረጋውን ስርዓት ለመጠበቅ ሲባል ሲሆን  ይሄም የግደባ ሂደት ሳንሱር (Censorship) ይባላል፡፡

 

የሕግ ማዕቀፉ እና ልምዱ ምን ይላል?

 

ከላይ የጠቀስናቸውን ሦስት ተቋማት ከመጠበቅ አንፃር የተለያዩ ሀገሮች የተለያየ የህግ ማዕቀፍ ዘርግተው ጥበቃ ያደርጋሉ፡፡ ከጥንታዊቷ ሮም እስከ የዘመናችን ነጻ እና ለዘብተኛ (Liberal) ሀገሮች ድረስ በተለያዩ ምክንያቶች በመነሳት የሐሳብ ዝውውርን በሕግ ሲገድቡ ነበር፤ አሁንም ይገድባሉ፡፡ ነገር ግን የሕግ ገደቡ ያለ አግባብ ተለጥጦ የግለሰቦችን መብት መግፈፍ ሲጀምር ያኔ የገደቡ ስህተት ይጀምራል፡፡ ለምሳሌ የሮማን ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ከመካከለኛው ዘመን መጀመሪያ ጀምሮ ለተከታዮቹ 500 ዓመታት፤ አብዛኛውን የሳይንስት አስተምህሮቶች (የጋሊሊዮን መሬት በፀሐይ ዙሪያ ትሽከረከራለችን የሚል እሳቤን ጨምሮ) እንደ የኑፋቄ ትምህርት (Heresy) በመቁጠር፤ በኅብረተሰቡ ውስጥ ምንም ዓይነት ስርጭት እንዳይደረግ በማለት በሕግ ገድባ ቆይታለች፤ ሕጉንም የተላለፉትን ከእስራት እስከሞት ትቀጣ ነበር፡፡ ይሄም የተደረገው የሕግ ገደብ የሳይንሱን ዕድገት አቀጭጮት ነበር፡፡ በጥቅሉ አሁን ባለው አለም አቀፍ እሳቤ ሕሳብን ማሰራጨት ሙሉ ለሙሉ የተፈቀደ መብት (Absolute Right) እንዳልሆነ ጥቅል ስምምነት ቢኖርም፤ ገደቡ ከየት ይጀምር የሚለው ግን አከራካሪ ነው፡፡

 

ምኑ ይገደብ? 

 

ከላይ ለመጥቀስ እንደተሞከረው ሊገደብ የሚገባው መብት የትኛው መሆን አለበት የሚለው ሐሳብ ስምምነት  ላይ ያልተደረሰበት ጉዳይ ነው፡፡ ነገር ግን እንደ ኀልዮት ሊቃውንት የተለያየ ሐሳብ ይሰነዝራሉ፡፡ መንግሥት ራሱን እንደ ጠባቂ እና ሁሉን አድራጊ (state as Big Brother) በማድረግ ይህ የተፈቀደ ነው፤ ይህ ደግሞ የተከለከለ ነው የሚል ከሆነ የዜጎችን መብት ሊያቀጭጭ ይችላል የሚለው እሳቤ አንዱ ነው፡፡ ይህም - ይሄን ብትናገር፣ ብትጽፍ፣ ብታሰራጭ ዋ! - ማለት ሳንሱር በማስፈራራት (Censorship through intimidation) የሚለው ሐሳብ ነው፡፡ ሊቃውንቱም ይህ መሆን የሌለበት ነገር ነው ይላሉ፡፡

 

በሌላ በኩል ደግሞ መንግሥት እንደ የኅብረተሰቡ ተወካይነቱ (As agent of the Society) ኅብረተሰቡ የማይቀበላቸውን ነገሮች በሕግ መገደቡ ተገቢ ነው የሚለውን ሐሳብ እናገኛለን፡፡ ይህም ማለት መንግሥት እና ኅብረተሰቡ በሚገደበው ነገር ላይ ስምምነት አላቸው እንደማለት ነው - Censorship through consensus፡፡ ይሄም የኅብረተሰቡን የሞራል እሴቶች የሚፃረሩ ጉዳዮች ላይ ገደብ መጣሉ ተገቢ ነው ወደሚለው ሐሳብ ያደርሰናል፡፡

 

ስንጠቀልለውም በቀዳሚነት (As a Rule) ሐሳብን የመግለጽ ገደብ አይኑር፤ ነገር ግን ኅብረተሰቡ ላይ ጉዳት ሊያመጡ የሚችሉ ነገሮች ላይ ገደብ ማድረግ ይገባል ወደሚለው ድምዳሜ እንደርሳለን፡፡

 

ገደብ በኢትዮጵያ (Censorship In Ethiopia) 

 

የተጻፈ ሕግ በሀገራችን መተግበር ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በጣሊያን ወረራ ጭምር በፖለቲካ ቢሮ አማካኝነት ቁጥጥር የነበረ ቢሆንም  ሐሳብን የመግለጽ ነፃነት ላይ ገደብ በማድረግ ቀዳሚነቱን የያዘው፤ የ1935ት ዓመተ ምህረቱ “የቴአትርና የሲኒማ አደራረግን ስለመመርመር” የወጣው አዋጅ ቁጥር 37/1935 ነው፡፡

 

በርግጥ ነገር ግን ለሳንሱር መሠረት የሆነው የሕግ ማዕቀፍ የተዘረጋው ከወረራው መቀልበስ በኋላ በወጣው አዋጅ ነው፡፡ በዚህ ‹ልዩ ልዩ ጨዋታዎችን ለመመርመር በወጣ አዋጅ› አንቀጽ 4 መሰረት፡ ‹‹ማንኛውንም ፊልም፣ ቲያትር እና ሪቪው ይህንም የመሰለ የልዩ ልዩ ጨዋታ ሁሉ የጨዋታ መርማሪ ሳይመረምራቸው ለሕዝብ እንዲታዩ ማቅረብ አይቻልም›› በማለት ይደነግግ ነበር፡፡ አስከትሎም አንቀጽ 7 ላይ ‹‹የጨዋታ መርማሪው ‹‹ማንኛውንም ፊልም፣ ቲያትር እና ሪቪው ይህንም የመሰለ የልዩ ልዩ ጨዋታ ሕዝብ ይየው ወይም አይየው ብሎ የሚወስን የሕዝብን ፀጥታና ንፅህና (ብልግና የሌለበት መሆኑን) አይቶ ነው፡፡›› በማለት የገደቡ ምክንያት ደህንነት እና ንፅህናን መጠበቅ እንደሆነ ቢነግረንም፤ ስርዓቱን የሚያስኮርፉ ማናቸውም ድምፆችን ለመገደብ እንደ መሳሪያ ተደርጎ ይሠራበት ነበር፡፡ ይህ ሕግ  ንጉሡ ከሥልጣን እስከ ወረዱበት ዘመን ድረስ ዘልቆ ከስርዓቱ ጋር አብሮ ከሰመ፡፡

 

ደርግ ወደስልጣን በመጣበት የመጀመሪያ የሽኩቻ ዓመታት ገደቦቹ ላልተው ነበሩ ቢሆንም፤ ስልጣኑን አጥብቆ ሲይዝ ግን የበለጠ አክርሮ የተለያዩ አዋጆችን እና ደንቦችን እያከታተለ ያወጣ ጀመር፡፡ ኅብረተሰባዊነትን ይቃወማሉ ያላቸውን ሐሳቦችም በኅብረተሰባዊነት ስም እየማለ ሲያሻው በሕግ አሊያም በጉልበት ‹ሐሳብ የሚታሰብ እንጅ የሚነገር አይደለም› (You can thought anything but, you can’t express it) በሚል ብሂል ሳንሱርን አክርሮ ይሰራበት ነበር፡፡

 

በንጉሡ እና በወታደራዊው መንግሥት ስርዓቶች ወቅት የነበረውን ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ከሎሬት ፀጋዬ ገብረመድኅን ግፍ የበለጠ የሚነግረን የለም፡፡ ሎሬት ፀጋየ እንዲህ ይላሉ፡-

 

“ከፃፍኳቸው 41 ቴአትሮች ውስጥ (ከተረጐምኳቸውና በእንግሊዝኛም ከፃፍኳቸው ጭምር)፣ ዐሥራ ሁለቱን ሳንሱር ሙሉ በሙሉ አግዶብኛል፡፡ ሃያ አንዱን ቆራርጦብኛል፡፡ ሦስቱን ግማሽ ለግማሽ ጐራርዶብኛል፡፡ አራቱ ግን ገና ለመድረክ [አልቀረቡም] ከሦስቱ የሥነ ግጥም መጻሕፍቶቼ ውስጥ (ሁለቱ ገና አልታተሙም)፣ በሠላሳ ሰባት ነጠላ ዝርዝር ግጥሞቼ ምክንያት፣ የሳንሱር ቢሮ፣ የፀጥታው ክፍል ቢሮና የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቴ ቢሮ ከፍተኛ ሹማምንት ገስፀውኛል፡፡ ቀጥተውኛል፡፡ ዝተውብኛል፡፡ በአንዲት “ጆሮ ገድፍ” በምትባል ትንሽ ቴአትር ምክንያት የጃንሆይ መንግሥት ፀጥታ ቢሮ፣ ለሃያ አራት ሰዓት በቁጥጥር ስር አውሎኛል”

 

‹ሳንሱር ደህና ሰንብች›

 

የደርግ ስርዓት መገርሰስ ካመጣቸው መሠረታዊ ለውጦች አንዱ ሐሳብን በነጻነት የመግለጻ መብት መከበሩ ነው፡፡ የሳንሱር ቢሮም መዘጋቱ፡፡ ለዚህም መብት የመጀመሪያ ከለላ የሆነው የ1983 ዓ.ም የኢትዮጵያ የሽግግር ወቅት ቻርተር ነው፡፡ ቻርተሩ በአንቀጽ አንድ ዓለም አቀፉ የሰብኣዊ መብት ደንጋጌ (Universal Declaration of Human Right) ያለምንም ገደብ ለኢትዮጵያዊያን ተግባራዊ የሚደረግ ሰነድ መሆኑን ከደነገገ በኋላ በተለይም እያንዳንዱ ግለሰብ የእምነት፣ ሐሳብን መግለጽ፣ የመደራጀት መብት አለው›› በማለት ይደነግጋል፡፡ ይሄንም ተከትሎ 1985ቱ የፕሬስ ሕግ መውጣት ሀገሪቱ ሐሳብን የመግለጽ መብትን ያለገደብ ለማክበር ቆርጣ መነሳቷን አመላካች ሆነ፡፡

 

ለዚህ ነጻነት ሕገ መንግሥታዊ ድጋፍ ለመስጠት በማሰብም በ1987 ዓ.ም በወጣው የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊት ሕገ መንግሥት አንቀጽ 29 ንዑስ አንቀጽ 1 ላይ፡ ‹‹ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት የመሰለውን አመለካከት ለመያዝ ይችላል፡፡›› በማለት በአመለካከት ደረጃ ምንም ዓይነት ገደብ እንደሌለ አስረግጦ ሲያበቃ፤ በተመሳሳይ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2 ላይ ደግሞ ‹‹ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት ሐሳቡን የመግለጽ ነጻነት አለው፡፡ ይህ ነጻነት በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ ወሰን ሳይደረግበት በቃልም ሆነ በጽሑፍ ወይም በሕትመት፣ በሥነ ጥበብ መልክ ወይም በመረጠው በማንኛውም የማሰራጫ ዘዴ፣ ማንኛውንም ዓይነት መረጃና ሐሳብ የመሰብሰብ፣ የመቀበልና የማሰራጨት ነጻነቶችን የካትታል፡፡›› ብሎ መብቱን ያሰፋዋል፡፡ እንዲሁም በዚሁ አንቀፅ ንዑስ ቁጥር 3 ላይ ‹‹የቅድሚያ ምርመራ በማንኛውም መልኩ የተከለከለ ነው፡፡›› በማለት ነፃነትን በሰፊው ያውጃል፡፡ ነገር ግን ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት በሕግ ገደብ ሊደረግበት እንደሚችል አንቀፁ ያትታል፡፡

 

‹ሳንሱር እንደገና›!?

 

እነዚህ ሁሉ መብቶች በሰፊው በሕግ ከለላ ማግኝታቸው ኢሕአዴግ ሥልጣን በያዘበት የመጀመሪያው ዐሥር ዓመት ጊዜ ውስጥ እንደ ትልቅ እምርታ የሚታይ ሲሆን ይሄንም ተከትሎ በሀገሪቱ ውስጥ የፕሬስ መስፋፋት እንዲሁም ሐሳብ መግለጫ ሜዳው መስፋት አሳይቷል፡፡ የተለያዩ መጽሔቶች ጋዜጦች እና የስነጽሑፍ ሥራዎች (መጽሐፍትን ጨምሮ) ስርጭትም በሚታይ ሁኔታ መስፋፋት ጀመረ፡፡ ይህ ሁኔታ ያልሰከነ በመሆኑ የሚታማውን የቅድመ 97 የፕሬስ ዘመን የሚጨምር ሲሆን ለዓመታት በቋሚነት የቆዩትን እንደነ ጦቢያና ጦማር የመሳሰሉትን የሕትመት ውጤቶችን ይዞ ዘልቋል፡፡  የምርጫ 97 ውጤት ደም አፋሳሽ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ መንግሥት በጉዳዩ ላይ የፕሬስ ተቋማት ሰራተኞችን እና ጋዜጠኞችን ማሰሩን አስከትሎ ጠበቅ ያለ አቋም መያዝ ጀመረ፡፡

 

አዋጆቹ

ከምርጫ 97 በሁዋላ ምንም እንኳን የወንጀል ሕጉ ሐሳብን ከመግለጽ ጋር ተያይዞ ሊከሰቱ የሚችሉ ወንጀሎች እንደሚያስቀጡ ቢደነግግም ከዚህ በተጨማሪ ጋዜጠኞችን የሚጫኑ ቅጣቶችን በማከል ከብዙ አተካራ በኋላ የመገናኛ ብዙኃን እና የመረጃ ነጻነት አዋጅ ሕግን አፀደቀ፡፡ ከብዙ አካላትም በዋነኛነት ከጋዜጠኖች ሕጉ አፋኝ  እና ሕገ መንግሥቱንም የሚፃረር መሆኑን በመግለጽ ተቃውሞ መሰማት ጀመረ፡፡

 

በማስከተልም አወዛጋቢው የፀረ-ሽብር ሕግ ለፓርላማ ቀርቦ ፀደቀ፡፡ የመገናኛ ብዙኃን እና የመረጃ ነጻነት አዋጅ እንዲሁም የፀረ-ሽብር ሕጉ ሐሳብን ከመገደብ (Censorship) ጋር ያላቸው ተዛምዶ በዋነኛነት ተዘዋዋሪ ነው፡፡ ይሄም ማለት የመገናኛ ብዙኃን እና የመረጃ ነጻነት አዋጅ ያስቀመጠው እስከ አንድ መቶ ሽሕ ብር የሚደርስ ቅጣት አቅመ ደካማውን ፕሬስ በአንዴ ከገበያ ውጭ ሊያደርገው ስለሚችል ጋዜጠኞች ራሳቸውን እንዲገድቡ (Self Censorship) የሚያስችል መሆኑ፤ እንዲሁም የፀረ-ሽብር ሕጉ ግልጽ ያልሆኑ እንቅስቃሴዎችን ጭምር በሽብር ተግባርነት የሚፈርጅ መሆኑ ዜጎች ራሳቸውን እንዲገድቡ እና ሕገ መንግሥታዊ መብታቸውን አሳልፈው እንዲሰጡ ማድረጉ ነው፡፡ ይሄም በሕግ ቋንቋ ‹Chilling Effect› ወይም ‹ስጋት ለበስ ቅልበሳ› የሚባለው ነው፡፡ ይህም ማለት ዜጎች ቅጣትን በመፍራት ሕገ መንግሥታዊ መብታቸውን ከመጠቀም ወደኋላ ማድረግ (discouragement of the legitimate exercise of a constitutional right) ነው፡፡

 

እነዚህ ቀጥተኛ ያልሁኑ የራስን ግደባ ሁኔታዎች እንዳሉ ሆነው፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ መንግሥታዊ ተቋማት ‹የሥራ ውል› በሚል መጠሪያ፤ ለሕትመት የሚበቁ ጽሑፎችን በመርማሪ አስመርምረን ነው የምናትመው ማለታቸው፤ ጉዳዩን ከማባስም አልፎ በሕገ መንግሥት በግልጽ የተከለከለውን ሳንሱር በእጅ አዙር እየመጣ ነው እንዴ? ብለን እንድንጠይቅ ያስገድደናል፡፡

 

ከነዚህ ሕጎች እና ደንቦች በተጨማሪ እያደገ የመጣውን የድረ-ገጽ ተጠቃሚ ቁጥር መሠረት በሚያደርግ መልኩ ከምርጫ 97 ወዲህ ትክክለኛ ቁጥራቸውን ማወቅ የማንችላቸው ድረገጾች በኢትዮጵያ ብቸኛ የቴሌኮምኒኬሽን አገልግሎት አቅራቢ በሆነው በኢትዮቴሌኮም ሰርቨር እንዳይታዩ የሆኑ ሲሆን፤ ይሄም እገዳ (Censorship) ከአረቡ ዓለም መነቃቃት በኋላ እጅግ ተባብሶ በመቀጠል እንደ አልጀዚራ ያሉትን ዓለማቀፍ የዜና አውታሮችን ከማገድ ጀምሮ፤ የግለሰቦችን የማኅበራዊ ድረ-ገጽ አድራሻ እስከማፈን ቀጥሏል፡፡ (ከዚህ ጋር ተያይዞ የዞን 9ኝን የጦማሮች ምን ጻፉ ጽሁፍ እዚህ ይመልከቱ) መንግሥት ለዚህ እና ከእገዳ ጋር ለተያያዙ ጥያቄዎች የሚሰጠው ምላሽ፤ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮን መንግሥታቸው ሀገሪቱን ከማረጋጋት አኳያ ማፈኑን እና የአፈና አቅማችን እያጠናከርን ነው ከማለታቸው በስተቀር፤ በደፈናው ‹እኔ  አላገድኩም› የሚል  ነው ፡፡(በተለይ የተለያዩ የፊስቡክ ገጾች እና ጦማሮችን የመዝጋት ልምድ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተባባሰ መጥቶ የአቤ ቶክቻው የግል ፊስቡክ ገጽ፣ የዞን ዘጠኝ የፌስ ቡክ ገጽ እና ጦማር፣ ድምጻችን ይሰማ እንዲሁም በቀዳሚነት የተዘጋው የቀድሞው አዲስ ነገር ጋዜጣ የፌስ ቡክ ገጽ ይታወሳሉ፡፡)

 

ስናጠቃልልም የኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት በግልጽ እገዳን እና አፈናን (Censorship) ከመከልከሉም በተጨማሪ፤ ኢትዮጵያዊያን መረጃ የማግኝት መብታቸው በሰፊው የተከበረላቸው መሆኑን ያትታል፤ ነገር ግን በተለይም ከምርጫ 97 ማግስት ጀምሮ መንግሥት በሚያወጣቸው ሕጎች እንዲሁም ከሕግ ውጭ በሆኑ አካሄዶች እነዚህን መብቶች እያጠበባቸው እና እየገፋቸው እንደሆነ እውነታዎች ያሳያሉ፡፡ ይሄም በሀገሪቱ አንድ ዓይነት አስተሳሰብ (Singular Discourse) እንዲኖር መፈለጉም የዜጎችን በሕገ መንግሥት የተሰጠ መብት፤ በአዋጅ መንጠቅና ግፋም ሲል በጉልበት ወደመቀማት እየመራው ነው የሚለውን እሳቤ አጉልቶታል፡፡ ነገር ግን የBen Shahn ፖስተር “You have not converted a man because you have silenced him." ይለናል፡፡

----

የዚህ ጦማር ዋና ቅጂ በኢትዮጵያ እንዳይነበብ በታገደው የዞን ዘጠኝ ጦማር ላይ ይገኛል፡፡

title

Click to add text, images, and other content

title

Click to add text, images, and other content

title

Click to add text, images, and other content

title

Click to add text, images, and other content

title

Click to add text, images, and other content

title

Click to add text, images, and other content

title

Click to add text, images, and other content